ETHIO12.COM

አዳነች አቤቤ የላቀ/ የአርበኛነት የአመራር ሽልማት እንደሚሸለሙ የአፍሪካ የልማት ተማሪዎች ሊግ አስታወቀ

የአፍሪካ ልማት ተማሪዎች ሊግ 32ኛዋን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ከፍተና ያለውን የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት እንደሚቸልም ይፋ አደረገ። ነገ በስካይ ላይን ሆቴል በሚደረገው ሽልማት አዳኔች አቤቤ የአፍሪካ ለማት ተማሪዎች ሊግ የማራር ብቃት / አርበኝነት ሽልማት LEADS AFRICA’S PATRIOTIC LEADERSHIP AMAZON ይበረከትላቸዋል።

የሊጉ ዋና ጸሃፊ ሚር ኦሲሲዮጉ ኦስሊክኒየ  በስልክ ለኢትዮ 12 እንዳስታወቁት የአዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ ለዚህ ሽልማት የበቁት በተለያዩ የሃላፊነት መደብ ላይ ሆነው ” አርበኛነት የተላበሰ የአመራር ብቃት በማሳየታቸው ነው”ብለዋል። አያይዘውም ለዚህ የላቀ የአመራር ስብ ዕናቸው የድርጅታቸውን LEADS AFRICA’S PATRIOTIC LEADERSHIP AMAZON ሽልማት እንዲያገኙ መወሰኑንን የሚያበስሩት በታላቅ ኩራት እንደሆነ አመልክተዋል።

በቆፍጣናነታቸው በአገር ውስጥ የሚታወቁትና ቀደም ባሉት ዓመታት በነበሩባቸው ሃላፊተቶች ከአገልግሎት ፈላጊዎች፣ ከስራ ባልደረቦቻቸውና ከመንግስት ከፍተኛ አለቆቻቸው ምስጋና የሚቀድምላቸው አዳነች አቤቤ ሲቶችን ወደ አመራር ለማምጣት እያደረጉ ያለው እንቅስቃሴም የሊድስ አመራሮችን ቀልብ ስቧል። ሃምሳ ከመቶ ካቢኔዎቿን ሴት ያደረገችው ኢትዮጵያ እንደ አዳንች አቤቤ ባሉ የአመራር አርበኞች ይበልጥ ሴቶች ወደ አመራር ይመጣሉ የሚልም ተስፋ አለ።አዳነችም እሳቸውን የሚመሳሰሉ አመራሮችን ስለሚፈጥሩ ይህ የአመራር አርበኛነት ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ከስልክ ምልልሱ ለመረዳት ተችሏል።

የወ/ሮ አዳነች አቤቤን የአምራር ብቃት በገቢዎችና ጉምሩክ፣ እንዲሁም በጠቅላይ አቃቤ ህግ መንበራቸው ላይ በብቃት የታየ መሆኑንን ያመከቱት የሊድስ ዋና ጸሃፊ በዚህ ሁሉ የሃላፊነት መንገዳቸው የላቀ አመራር ባለቤት በመሆናቸው ጥንታዊቷን ከተማ ለመምራት ብቁ ሆነው እንዲመረጡ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። አያይዘውም ” ይህ ለአፍሪካ ሴቶች ኩራት ነው። ከፍተኛ የማጣቀሻ ምንጭም ያደርጋቸዋል” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።

ወይዘሮ አዳነችን ላበረከቱት ተግብራና ተነሳሽነት እውቅና ለመስጠት ሽልማቱ እንድተዘጋጀላቸው ያስታወቁት ጸሓፊው “ ወ/ሮ አዳነች አቅሙና ችሎታው ስላላቸው ሴቶችን ከማብቃት አንጻር፣ ለአህጉራችንም ሆነ ለኢትዮጵያ ሰፊ ስራ እንደሚሰሩ እናምናለን” ሲሉ ለወድፊቱ ስራቸው በክፈተኛ ደረጃ ሊበረታቱ ይገባል የሚል እምነት መያዙን ገልጸዋል።

ሊድስ እንዳሳወቀው ምክትል ከንቲባ አዳነች ነገ ማርች 28 በስካይ ላይን ሆቴል የአመራር ብቃት እውቅና ሽልማታቸውን ይወስዳሉ።


Exit mobile version