ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በፅኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ -19 ምላሽ ግብረ-ሃይሎች አስተባባሪ ዶክተር ሚዛን ኪሮስ አስታወቁ። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ምጣቱን አመለከቱ።
ዶክተር ሚዛን ኪሮስ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ፣ ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በጽኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሀገሪቱ የኮቪድ -19 ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡
በሽታው ያለባቸው እና በጽኑ ህክምና ላይ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በየጊዜው እየጨመረ መምጣት የበሽታው ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ፡፡ ይህም የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቋሚ ነው ብለዋል፡፡
የምርመራ ውጤቶች ከቀን ቀን የሚሊያዩ ቢሆንም ባለፉት ሶስት ሳምንታት በተለይ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡን አመልክተው፣ በሚፈለገው ልክ ምርመራዎች እየተካሄዱ ባለመሆናቸው እንጂ በሌሎች ክልሎችም የበሸታው ስርጭት እየጨመረ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ምልክቶች እንዳሉ አመልክተዋል። የቫይረሱን አጠቃላይ ትክክለኛ ስርጭት ለማወቅም በቅርቡ ሰፊ ሀገራዊ ጥናት እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡
(ኢ ፕ ድ)
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት