በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ነው – የኮቪድ-19 ክትባት ቅዳሜ ይጀምራል

በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በኢትዮጵያ የ12 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ  ማሳየቱን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ። ይህ በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ  2 በመቶ፣ በአፍሪካ 10 በመቶ መጨመሩን ገለጸ።  በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ከፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀምር የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ነው  ሲልም  አስጠንቅቋል። ባሳለፍነው ሳምንትም ከየካቲት 22 እስከ 28 ቀን 2013  ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር የ2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በአፍሪካም በዚሁ ሳምንት በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ በ10 በመቶ የጨመረ ሲሆን በተለይ በኢትዮጵያ ደግሞ ከዚህም አልፎ በ12 ነጥብ 8 በመቶ አድጓል፡፡ በትናንትናው ዕለት የኮቪድ-19 የላቦራቶሪ ምርመራ ካደረጉ 7 ሺህ 819 ሰዎች መካከል 1 ሺህ 543ቱ የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች 20 ያህሉ ወይም 20 በመቶ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም  ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለው የፅኑ ሕሙማን ቁጥርም ትናንት 438 ደርሷል፡፡ ይህ ቁጥር ኮቪድ-19 ወደ አገሪቱ ከገባ ጀምሮ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በትናንትናው እለት ብቻ 15 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን የሟቾች አጠቃላይ ቁጥር 2 ሺህ 446 ደርሷል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በፍጥነት እና በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተዛመተ መሆኑን  ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ማስክ በመልበስ እንዲሁም አካላዊ ርቀታቸውን እና የእጃቸውን ንጽህና በመጠበቅ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በጋራ እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

 በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ከፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀምር የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ክትባቱ በሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት እንደሚሰጥም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

ጤና ሚኒስቴር ክትባቱን ለመጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡

እስካሁን ስልጠና መስጠት፣ ክትባቱን ማሰራጨትና ክትባቱን መውሰድ የሚገባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የመለየቱ ተግባርና ሌሎችም ዝግጅቶች በስፋት ማከናወኑንም አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት በኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት መረከቧ ይታወሳል፡፡

በመጀመሪያ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው ከፍ ያሉ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል፡፡

FBC

Related posts:

ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”

Leave a Reply