Site icon ETHIO12.COM

በቶማስ ሳንካራ ግድያ የቀድሞው የቡሪኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ብሌይስ ኮምፓኦሬ ክስ ተመሰረተባቸው

የቡሪኪና ፋሶ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ተወዳጅ በነበሩት እና ሀገሪቱን ለተወሰኑ ጊዜያት ከመሩት ቶማስ ሳንካራ ግድያ ጋር ተያይዞ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ብሌይስ ኮምፓኦሬ ላይ በሌሉበት ክስ መሰረተ።

በፈረንጆቹ 1983 ስልጣን ይዞው እስከ 1987 ቡሪኪና ፋሶን የመሩት ቶማስ ሳንካራ በወቅቱ የቅርብ ወዳጃቸው በነበሩት ብሌይስ ኮምፓኦሬ  መፈንቅለ መንግስት ተካሂዶባቸው በ37 ዓመታቸው ከ12 ሌሎች ባለስልጣናት ጋር መገደላቸው የሚታወቅ ነው።

ፍርድ ቤቱም ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱን እስከ ፈረንጆቹ 2014 የመሩትን ብሌይስ ኮምፓኦሬ በግድያ እና በመንግስት የፀጥታ አካላት ጥቃት በመፈፅም ክስ መስርቷል። ኮምፓኦሬ በ2014 ስልጣናቸውን ለማራዘም ሲንቀሳቀሱ በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን ተወግደው በኮት ዲቫር ጥገኝነት ጠይቀው እንደሚገኙ ይነገራል።

ቡሪኪና ፋሶን ለ27 ዓመታት ከመሩት ኮምፓኦሬ በተጨማሪ የቀኝ እጃቸው ጊልቤርት ዴንዴር እና የደህንነት አለቃ የነበሩትን ጨምሮ 13 ባለስልጣናት ክስ ተመስርቶባቸዋል። የቶማስ ሳንካራ ቤተሰቦችን የወከሉት ጠበቃም ሁኔታውን ድል እና በትክክለኛ አቅጣጫ መጓዝ ነው ሲሉ መግለፃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። በርካታ የቡሪኪና ፋሶ ዜጎች ቶማስ ሳንካራን ብሄራዊ ጅግናቸው መሆኑን የሚገልጹ ሲሆን ታዋቂ የፓን አፍሪካዊነት አቀንቃኝ ነበር።

በአንድንድ ወገኖች የአፍሪካ አህጉር ቼ ጉቬራ ተብሎ በሚጠራው ቼ ጉቬራ ግድያ ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ባሻገር ምዕራባውያን ሀገራት ይጠረጠራሉ። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- FBC


Exit mobile version