ETHIO12.COM

ኦርቶዶክስ ግልጽ ምላሽ ተጠየቀች፤ አማራውን ለማስጨረስ በአማራው ስም ሃብት የሚሰበስበው ማን ነው?

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስም ORTHODOX TEWAHDO AGAINST GENOCIDE IN ETHIOPIA /O.T.A.G.E “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የዘር እልቂት መከላከል” በሚል የተቋቋመ ህገወጥ ድርጅት በገሃድ ገንዘብ እየሰበሰበ መሆኑ እየታየ ቤተክርስቲያን ዝምታ መምረጧ እያነጋገረ ነው። የሚሰበሰብው ገንዘብ በቀጥታ አቶ ይልማ ወልደመድህን Yilma Woldemedhen የሚባሉ የትግራይ ተወላጅ ናቸው።

በጎ ፈንድ ሚ ከኖቬምበር 8 ቀን 2020 ጀምሮ ” አደራጅ” በተባለውና ከላይ በተጠቀሰው ህገወጥ ድርጅት ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ይህ እስከተጻፈ ድረስ 390 ሺህ ዶላር ወይም ከ10 ሚሊዮን ብር ገደማ ደርሷል። በአማራ ላይ ዘርን መሰረት አድርጎ እየተፈጸመ ላለው ግድያ ጠበቃ መስሎ የተከፈተው የእርዳታ ሃብት ” ተጠቃሚ” ተብለው ለተገለጹት አቶ ይልማ ወልደመድህን የሚሰጥ መሆኑ እየታወቀ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለምን ዝም እንዳለች ግልጽ አልሆነም።

አክቲቪስት ስዩም ተሾመ መረጃውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የአዲስ አበባ ተባባሪያችን የሲኖዶስ ጽህፈት ቤትን በስልክ አናግሮ ” የምናወቀው ነገር የለም” የሚል ምላሽ አግኝቷል።

ኢትዮጵያን በመክዳት፣ ረሃብ ከሚያቃጥላቸው ዜጎች ጉሮሮ ላይ በአደባባይ በመዝረፍ፣ ከባዕድ አገራት የስለላ ተቋማት ጋር በመሆን ሆን ተብሎ እንዲከሽፍ የተዘጋጀ መፈንቅለ መንግስት በመምራት እውቅ የጦር መኮንኖችን በማስፈጀትና አሁን ደግሞ አማራና ኦሮሞ እንዲጫረሱ ” ከወለጋ እስከ ኤሊባቡር የማራ ግዛት ነው” በሚል አዲስ የልዩነት አጀንዳ እያነሱ ነው የሚባሉት ሻለቃ ዳዊት ከዚህ ድርጅት ጀርባ እንዳሉ እየተነገረ ነው።

ይህ በቀጥታ ህወሃት ደጋፊ ቋት ይገባል የተባለው እርዳታ ” አማራን በአማራ ተቆርቋሪነት ስም ማስጨረስ ማለት ነው” ሲሉ አስተያየት የሚሰጡ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባስቸኳይ ገንዘቡ ወጪ ሳይሆን ማሳገድ እንዳለባት ይጠይቃሉ። ይህን ድርጅት ከጀርባ ሆነው የሚመሩ ስውር እጆች ካሉም ቤተ ክርስቲያን ልታጋልጥ እንደሚገባ ያሳስባሉ።

ቤት ንብረቱ ዓመድ ሆኖ የተበተነ ዜጋ እያለ ለትህነግ በተዘዋዋሪ ማዋጣት አስገራሚ እንደሆነባቸው የሚናገሩ፣ በተከፈተው የጎ ፈንድ ስር 10 ሺህ ዶላር የሰጠ የአማራ ድርጅት መኖሩን ጠቁመዋል። ሌሎችም በግለሰብ ደረጃ ተታለው ህወሃትን እየደጎሙ መሆኑንን ገልጸዋል።

ሙሉ መረጃውን እዚህ ላይ ይመልከቱ

https://www.gofundme.com/f/orthodox-tewahdo-against-genocide-in-ethiopia/donate የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይህንን ድርጅት እንደማታውቅ፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል ባሉ አካሎቿ ዘንድም የሚታወቅ ህጋዊ አግባብነት ያለው መዋቅር እንደሌለ በጉዳዩ ዙሪያ በገሃድ ምላሽ ለመስጠት አግባብነት እንደሌላቸው የጠቆሙ የሲኖዶስ ካህን በግረውናል።

መንግስት በሃይማኖት፣ በባለሃብቶች፣ በአክቲቪስትና በሚዲያዎች በመዋቅር ተያይዞ የሚፈጸም የነውጥ ሃይል ከነ ሙሉ እቅዱ መያዙን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ እንቅስቃሴ የዚያ አካል ይሁን ማረጋገጥ አልተቻለም። እትዮ 12


Exit mobile version