Site icon ETHIO12.COM

በአማራ ክልል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ መጠን ጨመረ- ሆስፒታሎችም ህሙማንን ማስተናገድ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን አስታውቀዋል

በአማራ ክልል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣቱ ተገለፀ::ሆስፒታሎችም የወረርሽኙን መስፋፋት ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ህሙማንን ለማስተናገድ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን በተለይ ለኢቲቪ አስታውቀዋል።


በአማራ ክልል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣቱን የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በአማራ ክልል የሚገኙ ሆስፒታሎችም የወረርሽኙን መስፋፋት ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ህሙማንን ለማስተናገድ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን በተለይ ለኢቲቪ አስታውቀዋል።

የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ በደብረታቦር ከተማ የምክክር መድረክ አካሄዷል

በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑት የደብረብርሃን ኮምፕሬንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አስማረ ሳሙኤል በሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የኮሮና ህሙማንን ለማስታመም አልጋዎች በመሙላታቸው በረንዳ ላይ ሁሉ ለማስታመም ተገደናል ብለዋል።

በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥበበ ግዮን እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና አግልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ዘበናይ ቢተው በበኩላቸው ለኮቪድ ህሙማንን አስፈላጊ የህክምና ግብዐት እጥረት ስለገጠመን ህሙማንን ለማስተናገድ እየተቸገርን ነው ብለዋል።

የኮሮና ክትባትን በተመለከተ የጤና ባለሞያዎች መከተብ ከሚጠበቅባቸው ከግማሽ በታች መከተባቸውን ተነግሯል።

በክልሉ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያያዙ ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ የደረሰ ሲሆን ከ218 በላይ የሚሆት ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸው ማለፉን የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ ገልጸዋል።
በክልሉ በኮሮና ቫይረስ ያለው የሞት ምጣኔ 2.18 ሲሆን ይህም ከሀገር አቀፉ የሞት ምጣኔ የበለጠ ነው ብለዋል ።

የኮሮና ክትባት እድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑና ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው ሰዎች እተሰጠ ሲሆን እስካሁንም 6በመቶ ደርሷል።

ሆስፒታሎች የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት አየሰሩት ባለው ስራ እያጋጠማቸው ያለውን ያለውን የግብዓት እጥረት ለመቅረፍ የክልሉ እየሰራ ነው ብለዋል።

በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ የመጣው ከዚህ ቀደም ይደረግ የነበረው የቅድመ ጥንቃቄ ትግበራዎች መቀነስና መዘናጋት በምክንያትነት ተጠቅሷል።

በሰለሞን ፀጋዬ

EBC

Exit mobile version