ከ15 ወራት በላይ ስጋት ሆኖ የዘለቀው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ 36 የጤና ባለሙያዎችን ህይወት እንደነጠቀ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።በቫይረሱ 3 ሺህ 329 የጤና ባለሙያዎች ተይዘው እንደነበር እና ከነዚህም ውስጥ 36ቱ ህይወታቸው ማለፉን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለሁ አባይነህ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስከ ሰኔ ሶስት ባለው ጊዜ በቫይረሱ ምክንያት 4 ሺህ 226 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት የጤና ሚኒስቴር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሐገራዊ የወረርሽኙን ስርጭት የሚያመላክተቱ ጥናቶች የሚቀርቡበት መድረክ ላይ ነው።
ወረርሽኙ ከባድ ጫና በሀገር ላይ ፈጥሯል ያሉት አቶ አባይነህ፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተወሰዱ እርምጃዎች በቫይረሱ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የሞት መጠን መቀነስ እንዳስቻለም ጠቁመዋል።ምክትል ዳይክተሩ ወረርሽኙ ሲጀምር ምንም አይነት የመርመሪያ መሳሪያ ያልነበረ ሲሆን አሁን ላይ 82 የመንግስትንና የግል የላብራቶሪ ተቋማት የኮቪድ ምርመራ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ተናግረዋል።
የምርመራ ኪትም በሀገር ውስጥ እየተመረተ እንዳለ እና ይህም በውጭ ምንዛሬ እጥረት ይስተጓጎል የነበረውን የግዥ ሒደት ማስቀረት እንዳስቻለ ተነግሯል።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ሙሉ ነጋ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እያገዙ መሆናቸውን ተናግረዋል።በቀጣይም በወረርሽኙ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ ይገባል ተብሏል።
ኢቢሲ ዜና
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ።… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”