ETHIO12.COM

የኮሚሽነር አበረ ህልፈት “በነጋዴዎች” እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ

ለኮሚሽነሩ ህልፈተ ህይወት ዋናው ምክንያት የልባቸው ጉዳይ ቢሆንም በወቅቱ ወደ ሆስፒታል ሲመጡም የስኳር መጠናቸው ከ400 በላይ ደርሶ እንደነበር ዶክተር ሀብታሙ ገልፀዋል።

ኮሚሽነር አበረ ህይወታቸው ማለፉ መደረጉን ተከትሎ ” አንድ ጠላት ተቀነሰ” ሲሉ የትህነግ ደጋፊዎች ሰሜታቸውን በደስታ እየገለጹ ነው።  በተመሳሳይ ” ነጋዴዎች” አጋጣሚውን በመጠቀም ገና ከሃዘን ያላገገመውን የአማራ ክልል ለማተራመስ የሚተጉ ” አዲስ አበባ ሄደው ተመርዘው ሞቱ” ሲሉ እየቀሰቀሱ ነው። 360 የሚባለው የዩቲዩብ አውድ ደግሞ ምንጮች እንደነገሩት ጠቁሞ ኮሚሽነሩ በሰው እጅ እንደሞቱ ዘግቧል። ሃኪም ግን ዋናውን ምክንያት ይፋ አድርጓል።

በህግ ማስከበሩ ማግስት ስለ አማራ ልዩ ሃይል ኦፕሬሽንና ጀግንነት አድነቀው ማብራሪያ ሲሰጡ ያልተወደዱት ኮሚሽነር አበረ መሞታቸው ሲሰማ የትህነግ ደጋፊዎች እርስ በርስ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕት ሶለዋወጡ ለማስተዋል ተችሏል።360 የሚባለው የዩቲዩብ አውድ በተለይም ከአማራ ክልል መረጃ እንደሚያገኝ ገልጾ በፌስ ቡክ ገጹ እንዳስነበበው የአበረ አዳሙ  ህልፈት ከጀርባው የመንግስት እጅ እንዳለበት አመልክቷል።

No description available.
360 ፌስ ቡክ ዜና

በድሪም ኬር ጠቅላላ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሀብታሙ በልብ ጡንቻ መጎዳት ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን መግለጻቸው በሃኪሙ አንደበት በግልጽ እየተነገረ ኩኔታውን “ግድያው” እያለ የሚጠራው 360 የተሰኘው ሚዲያ፤ ይህ ከሆነ በሁዋላም ዜናውን አላስተባበለም። ይልቁኑም

” የዛሬ ምናለ የቀጥታ ስርጭቱ ” የኮሚሽነር አበረ አዳሙ ህልፈተ ህይወትና ያስነሳው ውዝግብ ” በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይቱን ያደርጋል።የኢትዮ 360 ዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ፣ላይክና ሼር በማድረግ እንዲሁም ስቲከሮችን በመግዛት እንደሁልጊዜው አብራችሁን ሁኑ የሚለው የዘወትር የአክብሮት ግብዣችን ነው” አስቀድሞ ማስታወቂያ ያሰራጨ ሲሆን ገጹን ላይክና ሰብስክራይብ እንዲያደርጉም ጠይቋል።”

“ተገደሉ” ሲል 360 ዜናውን ባወጀበት ወቅት ከሰሜን ሸዋ ዞንና የኦሮሞ ዞን ላይ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ደስት አቢቹ አካባቢው አሁን መረጋጋቱን አመልክተው ” በርካታ እጆች ከጀርባው አሉበት” ሲሉ ተናግረዋል። የውጭ እጅ፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሚዲያዎች፣ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሃይሎች ስላሉበት በጥብቅ ምርመራ ጉዳዩን እየተጣራ መሆኑንን አመልክተዋል። ምርመራውን አስመልክቶ ሙሉ መረጃ እንደሚሰጥም አመክተዋል።

ኮሚሽነር አበረ ከሰሜን ሸዋው እልቂትና ውድመት በሁዋላ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ከመገለጹ ውጪ በገሃድ የቀረበባቸው ክስም ሆነ ወቀሳ ህይወታቸው እስካለፈ ድረስ የለም። እንደ ተቋም ግን ” ይህ ሁሉ እስኪሆን የት ነበር” በሚል እሳቸው የሚመሩት ልዩ ሃይል ተውቅሷል። ጉዳይም በጥልቀት እንደሚመረመር ብቻ ነው የተጠቆመው።

ከሰሞኑ ሃዘን ጋር በተያያዘ ያለው እውነት ይህ ሆኖ ሳለ ” የኮሚሽነር አበረ ህልፈት” የተጨማሪ ቁጣ ማቀጣጠያ እንዲሆንና አሁን ሰከን ያለውን የአማራ ክልል ለማተራመስ እንደ ግብዓት ለመጠቀም ” ተገደሉ” እየተባለ ነው። ለዝግጅት ክፍላችን ሃሳባቸውን የሰጡ ባለስልጣን እንዳሉት ” ቢያንስ የህክምና ባለሙያውን ማክበር ይገባል” ሲሉ ” ተገደሉ” መባሉ ክልሉን ለማናጋት ያለሙ ወገኖች ተንኮል እንደሆነ ሕዝብ መረዳት እንዳለበት አመላክተዋል። አያይዘውም ” አሁን አሁን የሰው ልጅ ሞት ከሚያሳዝነው ይልቅ መቆመሪያ መሆኑ ያሳዝናል” ብለዋል።

ሃኪምን ጠቅሶ አዲስ ዘመን ምን አለ?

በድንገተኛ ህመም ምክንያት ዛሬ ህይወታቸው ያለፈው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አበረ አዳሙ ህልፈተ ህይወትምክንያቱ የልብ ጡንቻ መጎዳት መሆኑን ህክምና የሰጧቸው ስፔሻሊስት ሀኪም ነገረውናል።የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያነጋገራቸውና ለኮሚሽነር አበረ አዳሙ ህክምና የሰጡት በድሪም ኬር ጠቅላላ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሀብታሙ የእኔአባት እንደገለጹት፤ ኮሚሽነሩ ጠዋት ላይ ለህክምና ወደ ሆስፒታሉ ሄደዋል።

የጤናቸው ሁኔታ ከበድ ያለ ስለነበር በፍጥነት ወደ ድንገተኛ ህክምና መስጫ ክፍል እንዲገቡ ተደርጎ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎላቸው የልብ ህመም ምልክቶች ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።እንደ ዶክተር ሀብታሙ ገለጻ፤ ኮሚሽነር አበረ ልብ ላይ የታየውን ጥርጣሬ በተደጋጋሚ የህክምና ምርመራ ማረጋገጥ ስለሚገባ ሁለት ጊዜ የኢሲጂ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፤ በተጨማሪም ሌሎች ከዚሁ ጋር የተያያዙ ምርመራዎች ተደርጎላቸዋል።

ውጤቱም “myocardial infarction” መሆኑ ተረጋግጧል።ይህም ወደልባቸው የሚሄዱ የደም ስሮች ተዘግተው ስለነበር የልባቸው ጡንቻ ከሚጠበቀው በላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የምርመራ ውጤቱ አሳይቷል።በዚህ መሀል ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በተደጋጋሚ ራሳቸውን እየሳቱ ይነቁ እንደነበር የገለጹት ዶክተር ሀብታሙ፤ የልብ ጡንቻ ጉዳታቸው ከፍ ያለ ስለነበር አይሲዩ ወዳለበት የባህር ዳር ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ወደሆነው እንዲሄዱ በመወሰን ወደ ጥበበ ግዮን ሆስፒታል ተወሰደዋል ነው ያሉት።ለኮሚሽነሩ ህልፈተ ህይወት ዋናው ምክንያት የልባቸው ጉዳይ ቢሆንም በወቅቱ ወደ ሆስፒታል ሲመጡም የስኳር መጠናቸው ከ400 በላይ ደርሶ እንደነበር ዶክተር ሀብታሙ ለኢፕድ ገልፀዋል።

ዶክተር መኮንን 

Exit mobile version