Site icon ETHIO12.COM

በአቡነ ማቲያስ መልዕክት ሳቢያ – ሲኖዶስ በመቆጣቱ አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ የተግሳጽና የማስተካከያ መግለጫ ሊሰጥ ነው

ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ቅዱስ ፓትሪያርኩ አቡነ ማቲያስ አማካይነት ያሰራጩት የቪዲዮ መልዕክት ቤተ ክርስቲያን የማታውቀው መሆኑንን የሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ እንዳረጋገጡላቸው አስታወቁ። ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልዕክት እጅግ ልን የሚያደማና ከአንድ መንፈሳዊ አባት የማይጠበቅ፣ እንዲሁም አሁን አገሪቱ ካለችበት ውጥረት አንጻር እሳት ለማቀጣጠል እንደተዘጋጀ ነዳጅ እንደሚቆጠር አመልክተዋል።

አቡነ ማቲያስ ሃሳባቸውን ማንጸባረቃቸውን መብታቸው እንደሆነ ቢያምኑም በይዘቱ ግን ቅር መሰነታቸውን ያስታወቁት አቡነ ፋኑኤል ነግግራቸው በተለያዩ አካላት ሲነገር የሚሰማና የተለመደ መሆኑ ጠቅሰዋል። ሆኖም ግን ይህ የተለመደ ንግግር ከሳቸው አንደበት ሲወጣ መስማት የተለየ ስሜት እንደሚፈጥር አብራርተዋል። “የትግራይ ህዝብ እንዳይኖር ተደርጓል። እንዲጠፋ ተፈርዶበታል” ማለታቸውን ክፉኛ አውግዘዋል።

የትግራይ ህዝብ በሁሉም ኢትዮጵያ ሰርቶ የሚኖር ታታሪ ህዝብ መሆኑንን ያነሱት አቡነ ፋኑኤል፣ እንዲጠፋ የተወሰነበት ህዝብ በሚል የተላለፈው ሃሳብ ልክ እንዳልሆነ እንደማሳያ አቅርበውታል። በትግራይ የደረሰውን ቀውስ መፍትሄ እንዲበጅለት እንደ ሃይማኖት አባት በህብረት ጥረት ማድረግ አግባብ ቢሆንም ለይቶ ማልቀስ ግን ከደረጃ መውረድ እንደሆነ ነው ያመለከቱት።

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከአንዴም አራት ጊዜ ቤተክርስቲያን ጉዳዩ በሰላም እንዲያልቅ ያደረገችውን ጥረት፣ እናቶች በእንብርክክ እየሄዱ በማልቀስ እርቅን ሲማጸኑ ማን እንደገፋ በጹዕነታቸው ጠንቅቀው እንደሚያውቁ አቡነ ፋኑኤል ገልጸዋል። በአገር መከላከያ ላይ የተፈጸመውን የክህደት ግፍ በማስታወሰ፣ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸመውን ዘር ላይ ያተኮረ የጅምላ ግድያ፣ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣ ስም እየጠሩ በመግለጽ ” ይህ ሁሉ ሲሆን ብጽእነታቸው የት ነበሩ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ከጥንት የመጽሃፍ ቅዱስ ታሪክ ጀምሮ ሴይጣን በአገልጋዮች ላይ እይደረ ያሳስት እንደነበር ያስታወሱ ት አቡነ ፋኑኤል፣ ዛሬም እንዲሁ እንደሆነ ጠቁመው ህዝብ እንዲረጋጋና ከማይጠቅም አጥፊ ጉዳይ ላይ ትኩረቱን እንዲያነሳ ተማጽነዋል።

ለትግራይ ህዝብ ክብርና ፍቅር እንዳላቸው፣ ትግራይ የኢትዮጵያ ቁልፍ እንደሆነችና ቤተሰቦቻቸው በስጋና አጥነት ከትግራይ ሕዝብ ጋር መውሃሳቸውን በማውሳት ስቃያቸውንና ሃዘናቸውን እንደሚጋሩ አስታውቀዋል። አያይዘውም የትግራይ ህዝብና ህወሃት አንድ አይደሉምና ህዝብ ለትግራይ ወንድምና እህቶቹ ፍቅርን ሊሰጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ምንም እንኳን ጠላቶቿ አባይን በመገደቧ ቢነሱባትም የድንግል ማሪያም አስራት ያላት አገር በመሆኗ እንደማትፈርስ፣ ትንሳኤዋም ቅርብ እንደሆነ አቡነ ፋኑኤል በእምነት ተናግረዋል።

ከሲኖዶስ ጸሃፉ በተነገራቸው መሰረት ለግንቦት ልደታ ወደ አጥቢያቸው ያመሩ አባቶች ሲመለሱ ሰኞ ሲኖዶስ ስብሰባ ይቀመጣል። በጉዳይ ላይ ተወያይቶ በቤተክርስቲያን ቀኖና አማካይነት መግለጫ እንደሚሰጥ ከዋና ጸሃፊው እንደተነገራቸው አስታውቀዋል። በቪዲዮ ያሰራጩትን ሃሳብ ያድምጡ

Exit mobile version