NEWS

በአቡነ ማቲያስ መልዕክት ሳቢያ – ሲኖዶስ በመቆጣቱ አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ የተግሳጽና የማስተካከያ መግለጫ ሊሰጥ ነው

ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ቅዱስ ፓትሪያርኩ አቡነ ማቲያስ አማካይነት ያሰራጩት የቪዲዮ መልዕክት ቤተ ክርስቲያን የማታውቀው መሆኑንን የሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ እንዳረጋገጡላቸው አስታወቁ። ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልዕክት እጅግ ልን የሚያደማና ከአንድ መንፈሳዊ አባት የማይጠበቅ፣ እንዲሁም አሁን አገሪቱ ካለችበት ውጥረት አንጻር እሳት ለማቀጣጠል እንደተዘጋጀ ነዳጅ እንደሚቆጠር አመልክተዋል።

አቡነ ማቲያስ ሃሳባቸውን ማንጸባረቃቸውን መብታቸው እንደሆነ ቢያምኑም በይዘቱ ግን ቅር መሰነታቸውን ያስታወቁት አቡነ ፋኑኤል ነግግራቸው በተለያዩ አካላት ሲነገር የሚሰማና የተለመደ መሆኑ ጠቅሰዋል። ሆኖም ግን ይህ የተለመደ ንግግር ከሳቸው አንደበት ሲወጣ መስማት የተለየ ስሜት እንደሚፈጥር አብራርተዋል። “የትግራይ ህዝብ እንዳይኖር ተደርጓል። እንዲጠፋ ተፈርዶበታል” ማለታቸውን ክፉኛ አውግዘዋል።

የትግራይ ህዝብ በሁሉም ኢትዮጵያ ሰርቶ የሚኖር ታታሪ ህዝብ መሆኑንን ያነሱት አቡነ ፋኑኤል፣ እንዲጠፋ የተወሰነበት ህዝብ በሚል የተላለፈው ሃሳብ ልክ እንዳልሆነ እንደማሳያ አቅርበውታል። በትግራይ የደረሰውን ቀውስ መፍትሄ እንዲበጅለት እንደ ሃይማኖት አባት በህብረት ጥረት ማድረግ አግባብ ቢሆንም ለይቶ ማልቀስ ግን ከደረጃ መውረድ እንደሆነ ነው ያመለከቱት።

የG-7 ሀገራት መግለጫ ስለኢትዮጵያ ምን አለ?

በእንግሊዝ እየተካሄደ ያለው የቡድን 7 ሃገራት ስብስባ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል:: በመግለጫው የኢትዮጵያ ጉዳይም ተካቷል:: በአንቀፅ 54 ላይ የሰፈረው መግለጭ ቃል በቃል የሚከተለውን ይላል። ትርጉም 54. “በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ግጭት እና እየወጡ ባሉ ሪፖርቶች ምናልባት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ሁኔታ ውስጥ ሊሆኑ ስለሚችሉ የሰብአዊ አደጋዎች በጣም ያሳስበናል፡፡ የጾታ ጥቃትን ጨምሮ እየተፈፀሙ ያሉ […]

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከአንዴም አራት ጊዜ ቤተክርስቲያን ጉዳዩ በሰላም እንዲያልቅ ያደረገችውን ጥረት፣ እናቶች በእንብርክክ እየሄዱ በማልቀስ እርቅን ሲማጸኑ ማን እንደገፋ በጹዕነታቸው ጠንቅቀው እንደሚያውቁ አቡነ ፋኑኤል ገልጸዋል። በአገር መከላከያ ላይ የተፈጸመውን የክህደት ግፍ በማስታወሰ፣ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸመውን ዘር ላይ ያተኮረ የጅምላ ግድያ፣ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣ ስም እየጠሩ በመግለጽ ” ይህ ሁሉ ሲሆን ብጽእነታቸው የት ነበሩ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ከጥንት የመጽሃፍ ቅዱስ ታሪክ ጀምሮ ሴይጣን በአገልጋዮች ላይ እይደረ ያሳስት እንደነበር ያስታወሱ ት አቡነ ፋኑኤል፣ ዛሬም እንዲሁ እንደሆነ ጠቁመው ህዝብ እንዲረጋጋና ከማይጠቅም አጥፊ ጉዳይ ላይ ትኩረቱን እንዲያነሳ ተማጽነዋል።

ለትግራይ ህዝብ ክብርና ፍቅር እንዳላቸው፣ ትግራይ የኢትዮጵያ ቁልፍ እንደሆነችና ቤተሰቦቻቸው በስጋና አጥነት ከትግራይ ሕዝብ ጋር መውሃሳቸውን በማውሳት ስቃያቸውንና ሃዘናቸውን እንደሚጋሩ አስታውቀዋል። አያይዘውም የትግራይ ህዝብና ህወሃት አንድ አይደሉምና ህዝብ ለትግራይ ወንድምና እህቶቹ ፍቅርን ሊሰጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ምንም እንኳን ጠላቶቿ አባይን በመገደቧ ቢነሱባትም የድንግል ማሪያም አስራት ያላት አገር በመሆኗ እንደማትፈርስ፣ ትንሳኤዋም ቅርብ እንደሆነ አቡነ ፋኑኤል በእምነት ተናግረዋል።

ከሲኖዶስ ጸሃፉ በተነገራቸው መሰረት ለግንቦት ልደታ ወደ አጥቢያቸው ያመሩ አባቶች ሲመለሱ ሰኞ ሲኖዶስ ስብሰባ ይቀመጣል። በጉዳይ ላይ ተወያይቶ በቤተክርስቲያን ቀኖና አማካይነት መግለጫ እንደሚሰጥ ከዋና ጸሃፊው እንደተነገራቸው አስታውቀዋል። በቪዲዮ ያሰራጩትን ሃሳብ ያድምጡ

 • የG-7 ሀገራት መግለጫ ስለኢትዮጵያ ምን አለ?
  በእንግሊዝ እየተካሄደ ያለው የቡድን 7 ሃገራት ስብስባ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል:: በመግለጫው የኢትዮጵያ ጉዳይም ተካቷል:: በአንቀፅ 54 ላይ የሰፈረው መግለጭ ቃል በቃል የሚከተለውን ይላል። ትርጉም 54. “በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ግጭት እና እየወጡ ባሉ ሪፖርቶች ምናልባት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ሁኔታ ውስጥ ሊሆኑ ስለሚችሉ የሰብአዊ አደጋዎች በጣም ያሳስበናል፡፡ የጾታ ጥቃትን ጨምሮ እየተፈፀሙ ያሉ […]
 • በመጨረሻው ከበባና በድርድር ተስፋ መካከል ላለው ትህነግ አዲስ የሚዲያ ዘመቻ ተጀመረለት፤ የማርቲን ፕላውት ለቅሶ
  “ቢቢሲን ጨምሮ፣ ሮይተርስ፣ ዘ ጋርዲያን፣ ዘ ቴሌግራፍ፣ ሜይል ኤንድ ጋርዲያን፣ ዘ ኢንዲፔንደንትና ሌሎች በርካታ መገናኛ ብዙኃን (ድረ-ገፆችን ጨምሮ) የውሸት ዜና በማሰራጨት ዘመቻ ተጠምደው ከርመዋል፤ አሁንም በአልሞት ባይ ተጋዳይነታቸው ቀጥለዋል። የእነዚህ ‹‹መገናኛ ብዙኃን›› የሐሰት ፕሮፓጋንዳና ውንጀላ ጠቅለል ያለ ምክንያት ‹‹ፀረ-ኢትዮጵያዊነት›› ነው።ይህ ኢትዮጵያን የመጥላት አባዜ እንግሊዝ ከከሃዲው የህ.ወ.ሓ.ት ጁንታ ጋር ካላት ወዳጅነትና ኢትዮጵያን ከማዳከም የዘመናት ሴራዋ የሚመነጭ […]
 • “እያንዳንዳችን ሰላምን አጥብቀን የምንሻና የምንኖራት እንሁን”ጠ/ሚ አብይ አህመድ
  – በነገ ብሩህ ተስፋና ተዝቆ የማያልቅ እድል ላይ አነጣጥረን የመጭውን ትውልድ ብልፅግና እውን ማድረግ አለብን በነገ ብሩህ ተስፋና ተዝቆ የማያልቅ እድል ላይ አነጣጥረን የመጭውን ትውልድ ብልፅግና እውን ለማድረግ በዛሬ ላይ ሳንታክት መትጋት ይገባናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ከመስቀል አደባባይ እስከ ማዛጋጀ ቤት የሚዘልቀውና በ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የተገነባውን […]
 • ከምርጫው ራሳቸውን እንደማያገሉ ፓርቲዎች አስታወቁ፤ “ይህ ማለት ግን ቢሸነፉ ለአሸናፊው እውቅና መስጠት አይደለም”
  በተለያየ ጊዜ በግልና በፓርቲ ሲሰጡ የነብሩ አስተያየቶች ተሰባስበው በአንድ ላይ እንደቀረቡ በማስታወቅ ራሳቸውን ከምርጫ እንደማያገሉ ቀድመው ያስታወቁት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ናቸው። ከሳምንት በፊት የአሜሪካንን ውሳኔና ማዕቀብ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበሉ የተናገሩት ኢንጂነሩ የፓርቲአያቸውም ሆነ የህብረታቸው አቋም ለውጥ መነሻ ምን እንደሆነ አላብራሩም። የህብር ኢትዮጵያ፣ እናት ፓርቲ፣ ባልደራስ፣ አብን እና መኢአድ ፓርቲ አመራሮች ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ምርጫው “በብዙ […]

Categories: NEWS

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s