ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ “አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካውያን” የሚል የጸና አምነቷን አጸናች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ አበባ ከሚገኙት ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺኬዲን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው ” ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች መፈለግ ” የሚለውን አቋም እንደምታጸና የተናገሩት።

ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከፍተኛ አቀባበል ያደረጉት የኮንጎ ፕሬዚዳንት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ከሆኑት አምባሳደር ጀፈሪ ፈልትማን አዲስ አበባ መግባታቸውን ተለትሎ ነው። ፊልትማን ግብጽ፣ ኤርትራና ሱዳን ከደረሱ በሁዋላ ነው አዲስ አበባ የገቡት። መርሃ ግብሩ ባይታወቅም አፍሪካ ህብረትንና የተባበሩት መንግስታት ሃላፊዎችን እንደሚያገኙ አስቀድሞ ተጠቁሟል። ከሹመታቸው ማግስት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ” ልቅ” የተባለ ቃለ ምልልስ ያደረጉትና ኢትዮጵያ እንደምትፈርስ ያሟረቱት ፊትማን ኤትዮጵያ በኤምባሲዋ አማካይነት በይፋ ” ዲፕሎማሲ የጎደለዎ” ስትል መረን ለለቀቀው ንግግራቸው ምላሽ ሰጥታለች።

እውን ሊሆን እየተንደረደረ ያለው የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ገጽታ

በሱዳን ቆይታቸው ወታደራዊ መሪውን ጀነራል መአስደንገጣቸውና ” ኢትዮጵያ በአባይ ወሃ የመጠቀም ሙሉ መብት አላት” ሲሉ የተድመጡት የምስራቅ አፍሪቃ ሹመኛ፣ በመቸረሻ አዲስ አበባ ከገቡ በሁዋላ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ደመቀ መኮንን ጋር መነጋገራቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል። በውይይቱም አሜሪካ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ሶስቱ አገራት እንዲስማሙ አጥብቃ እንደምትሰራ ፍላጎት መኖሩን ተመልክቷል።

ይህ እየሆነ ባለበት ወቅት ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺኬዲን እና የልዑካን ቡድናቸው ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ በኩል ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች መፈለግ የሚልው እምነት የጸና መሆኑንን አጉልተው መናገራቸው አሜሪካ እያደረኩ ነው ለምትለው ጥረት ምላሽ መስሏል።

በህብረቱ ሊቀመንበር አመቻችነት በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የታላቁ ሂዳሴ ግድብ የድርድር ሂደት ላይም አገሪቱ አትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን እንዳስታወቁ ኢዜአ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ አስታውቋል። ታላቁ የህዳሴ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል የትብብር እና የጋራ ልማት ተምሳሌት ሊሆን እንደሚችል እና በግብጽና ሱዳን ላይ ምንም ጉዳት በማያስከትል መንገድ እንደሚከናወን በኢትዮጵያ በኩል ጽኑ አቋም መኖሩንም በድጋሚ ተመልክቷል።

ኢትዮጵያ በትብብር መርህ ማዕቀፍ (ዴክላሬሽን ኦፍ ፕሪንሲፕልስ) መሠረት ለሁሉም ወገኖች የሚጠቅም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ፍላጎት እንዳላት በይፋ ማስታወቋም ተመልክቷል።

ኢትዮጵያ አባይን ለመገደብ ስታስብ ያልተነሳው ጦርነት ግድቡ ከነበረበት ችግር ተላቆ በኢንጂነር ስለሺ መሃንዲስነት ወደ መገባደጃው ሲቃረብ አገሪቱን ከየአቅጣጫው የመወጠር ርብርቡ መጠናከሩን በርካታ ምሁራን እየገለጹ ነው። የግድቡ ሁለተኛ ሙሌት በተያዘለት መረሃ ግብር መሰረት እንደሚከናውን መንግስት ይፋ ማድረጉን ምሁራን ሁሉ ” ግፉበት” የሚል ምክረ ሃሳብ እየሰጡበት ነው።

አሁን አዲስ አበባ ላይ የሚደረገው ምክክር በቀጣይ የኢትዮጵያ አካሄድና ሰላም ላይ ወሳኝ በመሆኑ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ሁሉም ሆኖ ግን በዘርፉ የተማሩ እንደሚሉት ኢትዮጵያውያን ሁሉንም ዋጋ ከፍለው ሁለተኛው ዙር ሙሌት ከተከናወነና ምርጫ ከተካሄደ ነገሮች መልካቸውን እንደሚይዙ ያምናሉ። አሁን በየአቅጣጫው የተከፈተው ዘመቻ ይህ እንዳይሆን ለማጨናገፍ እንደሆነም ይናገራሉ።


Exit mobile version