Site icon ETHIO12.COM

“ተረጋጉ”የፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ መልዕክት ነው

ሲሲ ይሄንን ማለቱን ተከትሎ ከፍተኛ ትችትን እያስተናገደ ነው። ገና ከማለቱ ቀይ መስመርህ ይሄ ነበር ወይ ? ወይስ መስመርህ ጠፋህ የሚል ዘመቻ ተጀምሮበታል።

ሰውየው ይሄንን ያለው ያለምክንያት አይደለም። የናይል ጉዳይ እንዳሰበው አልሄደለትም። የዱባዩ ልኡል መሀመድ ቢንዛይድ ጋር ከተወያዩ ቡሀላ የግብፅና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ግንኙነት ሻክሯል። የመሻከራቸው ምክኒያት በዋናነት፣ ኤሚሬትስ በኤርትራ ወደብ ላይ የገነባችውን የጦር ሰፈር ማፈርሷ ነው።
.
የጦር ሰፈሩ እንደፈረሰ፣ ዱባይ ተደጋጋሚ ጊዜ ከግብፅ ትችት ደርሶባታል። ግብፃውያን አፋቸው እንደተፋላቸው ለመናገር ወደኋላ አይሉም። ያልተገራ ንግግራቸው ሀብቷሟን ዱባይን አስቆጥቷል።

መረጃ በማፈንፈን የሚታወቀው ጆርደን ታየምስ ይሄንን መረጃ በሰፊ ሀተታ ፅፎት ካነበብኩት፣ ከአስር ቀን በላይ ሆኖታል። ዘጆርደን ታየምስ የተባለው ሚዲያ የሲአይኤን መረጃ በማሳጥ ይታወቃል ።

ወደ ሲሲ ቀይ መስመር መጥፋት ልመለስ፣
ሲሲ እንዲህ የፈራበትና ጉልበት ያጣባት የናይል ፖለቲካ በቀላሉ እንዲህ የሚሸነፍ አልመሰለውም ነበር። ኢትዮጵያ በአቋሟ
የምትፀና በየክልሉ የሚደግፋቸው ሽምቅ አገር አፍረሽ ጦረኞች የማዕከላዊ መንግስቱን አንኮታኩተው የሚጥሉለት መስሎት ነበር። በጂኦ ፖለቲካ አሰላለፍ አፍሪካንና ኤሺያን ዞሮ ዞሮ የደከመው ሲሲ የዞረባቸው አገሮች እንዲህ የሚክዱት አልመሰለው ነበር። የሱዳን አቋም ጂዋጂዌ ቢሆንም፣ የወታደራዊ ሀይሉ ሳያስቡት ስልጣን የሚለቁ አልመሰለው ነበር።
የሱዳን ህዝብ ጫና እንዲህ ጎልብቶ ወታደራዊ ክንፉን ከስልጣን የሚያሶግደው አልመሰለው ነበር።

ሱዳን አሁን ውስጥ ውስጡን ጉም ጉም እያለች ነው። የወታደራዊ አገዛዝ በሱዳን መሬት ሊያበቀላት ትንሽ ቀናት ናቸው የቀሩት። ወታደራዊ ሀይሉ በፖለቲካው ጉዳይ ላይ ፈላጭ ቆራጭ የሆኑበት ዘመን አክትሟል። አሁን ያላቸው አማራጭ አንድም የሱዳን ጦር ጋር ገንፎ እየበሉ መዋል ነው። ሁለትም ባመንቀን ያገቧቸው ኢትዮጵያዊያን ቆነጃጅቶች ጋር ሪሞት ሲያገላብጡ መዋል ነው።

በዚህ ሁሉ የሱዳን ፖለተካዊ ለውጥ መሀል የከሰረው የግብፅ ፖለቲካ ነው። ሲሲ ጉልበት ያገኘበት የሱዳን ፖለቲካ በአሜሪካ ጫና እንዳይሆን ሆኖ ተበላሽቶበታል። ወታደራዊ ሀይሉ የስልጣን ዘመኑ አጨለሟል። አሜሪካም ወታደራዊ ሀይሉ ከፖለቲካ ወደ ሉአላዊ ዘበኛነት እንዲቀየር አፅኖት ሰታለች።

የፕሬዝዳንት አብዱልታህ ሲሲና የጀነራል ቡረሀን እቅድም አንድ እዚህ ላይ አብቅቷል። እንዲህ ማላምቱ የጨለመበት ፕሬዚዳንት ሲሲ በአጭር አነጋገር የአባይን ግድብና የናይልን ጉዳይ በተመለከተ ተረጋጉ። ሁሉም ነገር ጊዜ ይፈልጋል። ድርድሩ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ አይደለም !
.
ይሄንን ሁሉ ያለው አሜሪካ ልዩ መልዕክተኛዋን ልካ የግድቡ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ይለቅ ካለች ቡሀላ ሲሆን የግብፅ እሩጫ ሁሉ እንደ ኤሊ ጉዞ ተሰባበረ። በውስጥ ሀይል እየተፈነች ከአቋሟ ” ንቅንቅ ያላለችው ሀበሻዊቷ አገር ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር መንገዷን አሰመረው።
.
አሁን ድሉ የኢትዮጵያ ነው። ግድቧን ሞልታ በወገቡ ላይ ኒኩሊየር ያገለደመ የኤሌክትሪክ ሀይል ግድብ ልታደርገው ነው። ጥላቶቿ አይናቸው ደም እያነባ ፣ እሷ አይኗን በኩል ኑር አሸብራቅ፣ ህዝቦቿን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት 2 ወራትን እየጠበቀች ነው።

ሰላም ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ

ፀሃፊ፦ ሱሌማን አብደላ

Exit mobile version