Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ 22 የትግራይ ተወላጅ አመራሮችን ገድሎ 20 ማገቱ ተገለጸ

ቀደም ሲል መንግስት እያለ የአሜሪካ መንግስት ከሽብረተኞች መዝገብ ውስጥ ያልፋቀውና በቅርቡ ፓርላማ ከኦነግ ሸኔ ጋር አሸባሪ ብሎ የሰየመው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ፣ ሃያ ሁለት ዓላማውን የማይቀበሉ የአመራር አባላትን መግደሉና ሃያ ያሚሆኑትን ማገርቱ ተገለጸ።

“የተበተኑ የአሸባሪው የሕወሓት ርዝራዦች እስከ አሁን 22 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን ገድለዋል፤ 20 የሚሆኑትን አግተዋል” ሲል ያስታወቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ነው።

የተበተኑ የአሸባሪው የሕወሓት ርዝራዦች በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች እስከ አሁን ድረስ ብቻ 22 የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት መግደላቸውን ፣ ከዚህ በተጨማሪ 20 የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት መታገታቸውን እና 4 የአስተዳደሩ አባላት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ሆስፒታል መግባታቸውን ስፍራና የስራ ሃላፊነት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።

“እየታገልኩ ያለሁት ለትግራይ ህዝብ ነው የሚለው አሸባሪው ሕወሓት ይልቁንም የክልሉን ሃብት እያወደመ እንዲሁም በክልሉ መረጋጋትን ለማምጣት የሚሰሩ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላትን እየገደለና እያገተ” ነው ሲል መረጃው አስታውቋል።

በትግራይ የሰብአዊ ዕርዳታ በወጉ እንዳይዳረስና በነጻነት እንዳይሰራጭ ህወሃት በየስርቻው እየተሹለከለከ እክል መፍጠሩን፣ ሰላማዊ ዓላማውን የማይደግፉትን አካላት መግደሉን በመጥቀስ የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ መናገራቸው ይታወሳል። ህወሃት ይህን ቢያደርግም የውጭ ሚዲያዎችና የመብት ተቆርቋሪዎች መረጃውን አይጠቀመኡበትም።


Exit mobile version