Site icon ETHIO12.COM

ኦፕሬሽን…ዋ! …(ኦፕሬሽን ባይደዋ!..)

ከሱዳን እሰከ ግብፅ፤ ከግብፅ አሰከ ባይደዋ ወደብ፤ ከባይደዋ እሰከ ጎንደር የተዘረጋውን የግብፅ ሴራ ያከሸፈው የኢትዮጵያ የመከላከያና የደህንነት መሳሪያቤት በጋራ የፈፀሙት የዘመኑ ድንቅ ኦፕሬሽን…ኦፕሬሽን ባይደዋ!

አዲስ አበባ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም የአድዋ ድል በዓል በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ነው። በሱዳን የስደተኞች ካምፕ ውስጥ አንድ የUNHCR አርማ የለጠፈ ሀርድ ቶፕ ላንድ ክሩዘር መኪና ቆሟል።አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ መኪናው ላይ አይኑን ጥሏል።ወጪ ወራጁን በአንክሮ ይከታተላል። በተንቀሳቃሽ ስልኩ ፎቶ ያነሳል።

አራት ሰዎች እየተጣደፉ ወደ መኪናው ተጠጉ። ከአራቱ አንዱ ኮፍያ አድርጓል፣ አለባበሱም በረሃ ከርሞ የተጎሳቆለ ኢትዮጵያዊ ይመስላል። አንደኛው ቀጭን ረጅም ነው እንዲሁ መልኩ ሲታይ ሶማሊ ይመስላል። እንቅስቃሴውና ንግግሩ ያሳብቁበታል። አንደኛው ሱዳናዊ የመኪናዋ ሹፌር መሆኑ ያስታውቃል። አራተኛው ሰው ግን ነጭ ነው መልኩን አይቶ የከሌ ዜጋ ነው ማለት ይከብዳል።

አራቱ ሰዎች የመኪናውን በር ከፍተው ገቡ። ኮፍያ ያደረገው ሰውና ሶማሊያዊ ሞቅ ያለ ወሬ ይዘዋል። ንግግርራቸው እንግሊዘኛ ነው። ኢትዮያዊው ስደተኛ
በስልኩ ካሜራ ለቀም አደረጋቸው። ፎቶውን ዙም አድርጎ ተመከው፣ ባለኮፍያውን ሰው ለየው። ኢትዮጵያዊ ነው። ከሳምሪ የተመለመለው ሰው። ወዲ ሱሁል… አለ ኢትዮጵያዊው ስደተኛ።

መኪናው ከካምፑ ወቶ ተፈተለከ። ኢትዮጵያዊው ስደተኛ ጊዜ አላባከነም አዲስ አበባ ለሚገኘው በአካል አይቶት ለማያውቀው ግን አለቃው ለሆነ ሰው ፎቶውን ላከው።

መኪናው ሰዎቹን ካርቱም አየር ማረፊያ አድርሶቸው ተመልሷል። አራቱ ሰውች የኳታር አየርመንገድ ንብረት በሆነ ቦይንግ 733 ተሳፍረው ካይሮ ግብፅ ደረሰዋል። እድሜ ለስደተኛው ሰላይ የአራቱ ሰዎች አጠቃላይ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ የደህንነት መረብ ውስጥ ገብቷል።
ሁለቱ ሰዎች ለሁለት ወራት ያህል በግብፅ ሲናይ አካባቢ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሽብር ድርጊት መፈፀም የሚያስችል ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ከፍተኛ ገንዘብ ይዘው ወደየ አገራቸው ተመልሰዋል።

የሳምሪው ምልምል ወዲ ስሁል በጎንደር በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል። የቅማንት ማንነት ኮሜቴ ከሚባል ሀይል ጋር ተገናኝቶ መከሯል። ከጎንደር ወጣ ብሎ በርካታ ሕገወጥ ቤቶች እንዲሰሩ አድርጓል።

ዱቄት፣ ዘይት፣ ስኳርና ሌሎች ስንቆችን ሕገወጥ ቤቶች አስጠግቶ፣ ወታደራዊ ስለጠና የወሰዱ የሽብር ቡድን አባላቱን በሕገ ወጥ ቤቶቹ አስጠልሏል። በርካታ ጥይቶች፣ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳርያዎች አከማችቷል። ለቡድኑ አባላት የጎንደር ከተማ፣ የጎንደር ዞኖች ወረዳዎችን የሀሰት መታወቂያ ታትሞ ተሰራጭቷል። በጎንደር አካባቢ ሰዎችን በማገት የሽብር ስራው ተጀምሯል። ዋናው የሽብር ጥቃት ደግሞ የግምቦት 20 እለት ለመፈፀም ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ ሆኗል።

የሞቃዲሾ ተወላጁ የወዲ ስሁል ጎደኛ በሱዳን የሰው ደተኛች ካምፕ ከታዩት አራቱ ሰዎች አንዱ አባስ ኢብሮ ባይደዋ ገብቷል። ለወደብ ቅርብ በሆነ አካባቢ ሆቴል ተከራይቶ እንቅስቃሴውን ጀምሯል። በአካባቢው ከሚንቀሳቀሰው የአልሸባብ ቡድን ጋር ግንኙነት ፈጥሯል። በኢትየጵያ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ስምምነት ላይ ተደርሶ ዝግጅቱ ተጠናቋል። የቀረው ግብፅ በወረታ መልክ ለአልሸባብ ልትልክ ቃል የገባችው አራት መርከብ ሙሉ የጦር መሰሪያ ባይደዋ ወደብ መድረሱ ብቻ ነው።

አባስ ኣብሮ ባይደዋ ከገባ ጀምሮ ዘወትር ጧት ነጭ ጀለብያውን ያጠልቃል ጥቁር መነጠሩን ያደርግና ከሆቴሉ ህንፃ ስር ወደ አቆማት ጥቁር ሜርሰዲስ መኪና ገብቶ ወደ ወደቡ አካባቢ ያሽከረክራል።
የኢትዮጵያ የደህንነት ሰዎችም መኪና እየቀያየሩ ዘወትር ይከታተሉታል። ሁለት የደህንነት ሰዎቾም ከአባስ ክፍል ፊትለፊትና ጎን ሁለት ክፍል ተከራይተው መኖር ጀምረዋል። ለአባስ ደግሞ ሁሉም ነገር እንዳሰበው አየሄደ ያለ ይመስላል…

…ግንቦት 1 ቀን 2013 ዓም ግን ለአባስ ጥሩቀን አይመስልም። አባስ እንደ ወትሮው ከእንቅልፉ ተነስቶ ወደ መኪናው አመራ። ሁለቱ ወጠምሻ ኢትዮጵያውያን የደህንነት ሰዎች የአባስ ጎረቤቶች በተመሳሳይ ሰዓት ከክፍላቸው ወጡ። ፊትና ኋላ ሆነው አባስን ተከተሉት።
አባስ የሰው ኮቴ ሲሰማ ገልመጥ ብሎ ተመለከተ። ጥቂት እንደተራመደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ተገለጠለት። ተደናገጠ። አንደኛው ኢትዮጵያዊ ሻንጣውን እየጎተተ አባስን አለፈው። አባስ ተረጋጋ።
ባለሻንጣው ኢትዮጵያዊ ለሆቴሉ ሪሰብሽን ቁልፍ አሰረክቦ ከሆቴሉ ወጣ…አባስ ተከትሎት ወጣ። ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ አባስን ተከተለው። አባስ ቆም ገተር አለ ኋለኛው ኢትዮጵያዊ አባስን አልፎት ወደ መኪና ማቆሚያው አመራ።

አባስ ከመኪናው በር ደረሰ። የሆነ ነገር ማጅር ግንዱን አለው አባስ ወደቀ። ኢትዮጵያውያኑ የወሳንሳ አንሱት። ከራሱ መኪና አስገብተው በረበሩት። ከጀለብያው ኪስ የሆቴሉን ቁልፍ አገኙት።

ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓም የግብፅ ባንዲራ የሚያውለበልቡ አራት መርከቦች ባይደዋ ወደብ ደረሱ። ሁለት ሱ27 ሚግ የጦር ጀትች ከካራማራ የጦር ካምፕ ተነሱ። በባይደዋ ሰማይ ላይ አገሱ! ከመርከቦቹ ላይ በሚራገፈው የጦር መሳሪያ ላይ እሳት ነሰነሱ። በ28ደቂቃ ውስጥ ግዳጃቸውን ጨርሰው ተመለሱ..ወዲያው በUN ከሚሽን ስር ያለውና በአካባቢው የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ደረሰ። የኢትዮጵያ እምባ ታፈሰ። የግብፅ ሴራ ፈረሰ።

ግንቦት20 2013 ዓም የምዕራብ እዝ አንድ ክፍል ጭልጋ ደረሰ። በጎንደርና አካባቢዋ የሽብር ጥቃት ሊፈፅም የተዘጋጀውን ሀይል ደመሰሰ። ስንቅና ትጥቀን ወረሰ። ከሱዳን እሰከ ግብፅ፤ ከግብፅ እሰከ ባይደዋ፤ ከባይደዋ እሰከ ጎንደር የተዘረጋው የግብፅ ሴረ ፈረሰ።

ኦፕሬሽን ዋ (እፕሬሽን ባይደዋ) በድል ተፈፀመ።

ኢትዮጵያ ትቅደም።
Dereje Asmamaw እንደፃፈው።

Exit mobile version