Site icon ETHIO12.COM

ግብጽ ተቀምጠው የጠሚ አብይን የተለያዩ ንግ ግር ገጣጥመው ለትርምስ ያዋሉ ተወገዙ

የሃሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ተራ ተግባር መሆኑን ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ፤

ከፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት ንግግር በማስመሰል ተፈብርኮ የተለቀቀውን ድምጽ አስመልክቶ ፓርቲው ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ እንዳሉት፣ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ሃሰትና የፓርቲው ፕሬዝዳንት በተለያየ መድረክ ላይ ከተናሩት ንግግሮች ተቆራርጦ የተፈበረከ ነው፡፡

አለማውም ህዝቡን ማደናገርና ህዝብና መንግስት መካከል ያለመተማመን እንዲፈጠር ብሎም ውጥረትና ያለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ቢቂላ፣ ተግባሩንም ተቀባይነት የሌለው ሃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የሚሰራጭ የወረደ ተግባር ነው ብለውታል፡፡

በዚህ ተግባርና ከጀርባ ያለው ድብቅ አጀንዳ ላይ የኢትዮጵያን እድገት የማይፈልጉ የውስጥ እና የውጭ አካላት እጅ እንደሚኖር ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

መሰል የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት ባለፉት ቅርብ አመታት እየተለመደ መጥተዋል ያሉት ሃላፊው ህዝቡ መሰረት ከሌላቸውና ምንጫቸው ካልታወቀ መረጃ እንዲጠበቅና መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲመርጥ አሳስበዋል፡፡

ebc


Exit mobile version