ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መደበኛ የብዙኃን መገናኛዎችን ጨምሮ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች እየተበራከቱ መጥተዋል። የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ አዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ ከዋለ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ቢቆጠርም ችግሩ በመቀነስ ፈንታ እየሰፋ ይገኛል። ለመሆኑ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት እየጨመረ የመጣው ለምንድን ነው? በሀገር ላይ የደቀነውን አደጋ ለመቀልበስ ምን መደረግ አለበት?
አንተነህ ፀጋዬ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል የድህረ ምረቃ መምህርናተመራማሪ ናቸው። ሐሰተኛ መረጃዎች በተለይ ከለውጡ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ መሄዳቸውን ይናገራሉ። ከተካሄደው የፖለቲካ ሪፎርም በኋላ ዋናዎቹ የብዙኃን መገናኛዎች እና ማኅበራዊ ሚዲያዎች በአንድ ጊዜ በጣም በተለጠጠ መልኩ ማንኛውም ሰው ሀሳቡን እንዲገልጽባቸው ሆነው ክፍት መደረጋቸው የፈጠረው ዕድል እንዳለ ሆኖ፤ ሀገር ላይ ብዙ አደጋዎችን መደቀኑን ይገልጻሉ።
ዶክተር ጸጋዬን ጠቅሶ ኢፕድ እንደዘገበው አብዛኞቹ ሐሰተኛ መረጃዎች ሥራዬ ተብለው የሚሠሩ በመሆናቸው አቅጣጫ በማሳትና መረጃን በማዛባት ኅብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላሉ። ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲወዳደር ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት ተደራሽነት ውስን ቢሆንም ሐሰተኛ መረጃ በሚገርም መጠንና ፍጥነት እየተሰራጨ ነው። ማኅበራዊ ሚዲያው በባሕሪው ተመሳሳይ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች የሚሰበስብ በመሆኑ አንድ ሐሰተኛ መረጃ በብዙ ሰዎች ከተወደደና ከተጋራ ከእውነተኛው መረጃ ይልቅ ብዙዎች ጋር ይደርሳል።
ማኅበራዊ ሚዲያ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ዓላማው የማኅበረሰብን ትስስር ማጎልበት መሆኑን የሚያወሱት መምህሩ፤ አሁንም ድረስ በአውሮፓና አሜሪካ ያለው ሚና ይህ ነው። ከዓረብ የፀደይ አመጽ ወዲህ ግን በተለይ በአፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ለተለየ ዓላማ እየዋለ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያደረገ ባለው ጥናት የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚዲያ ይዘት ከ85 በመቶ በላይ ፖለቲካዊ ሆኖ ተገኝቷል ይላሉ።
አያይዘውም፤ “እንደ ዩቱዩብ ያሉ መተግበሪያዎች ክፍያ ስለሚፈጽሙ ሰዎች ለገንዘብ ሲሉ ሀገራቸውን የሚሸጡበት ሁኔታ መፈጠሩ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት እንዲጨምር አድርጓል። ይህ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በስፋት ታይቷል። የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚዲያ ለጦርነቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። ለጦርነቱ ሂደትና ውጤት ትክክለኛ ያልሆነ መልክ ሰጥቷል። አሁን ያለንበት ጦርነትም ከዚያ ጋር የተያያዘ ነው።” በማለት ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ትልቅ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን ያስረዳሉ።
ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን ተጠያቂ በማድረግ ረገድ የሕግ ክፍተት መኖሩንም ያነሳሉ። የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ታዋቂ ለሆኑ ሰዎች፣ ለፖለቲከኞችና ሃይማኖት መሪዎች ከለላ እንደሚሰጥ የሚጠቅሱት ዶክተሩ፤ “በተጨባጭ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭት እንዲስፋፋ እያደረጉ ያሉት እነዚህ ሰዎች ናቸው። ግለሰቦችን የሚያነሳሱት የዝና፣ የፖለቲካና የሃይማኖት ካባ የለበሱ ሰዎች ናቸው” ሲሉ ይተቻሉ።
አንተነህ (ዶ/ር) ትችት ያቀረቡበት የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 ላይ “ልዩ ሁኔታ” በሚል የሰፈረው የአዋጁ ክፍል “አንድ ንግግር እንደ ጥላቻ ንግግር ወይም እንደ ሐሰት መረጃ ተወስዶ ማሰራጨት የማይከለከለው የትምህርታዊ ወይም ሳይንሳዊ ምርምር አካል እንደሆነ፤ የዜና ዘገባ፤ ትንታኔ ወይም የፖለቲካ ትችት አካል እንደሆነ፤ አልያም የኪነጥበብ፣ ትወና ወይም መሰል የሥነጥበብ ውጤት ከሆነ እንዲሁም የሃይማኖታዊ አስተምህሮት አካል እንደሆነ ነው።” ይላል።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት የምርምርና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሩ ገብረክርስቶስ ኑርዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ሰዎች መረጃዎችን መረዳት ከሚገባቸው በታች አድርጎ ማሳነስ ወይም አግዝፎ ማጋነን እንዲሁም ሐሰተኛ የሆነውን እውነት፣ እውነት የሆነውን ደግሞ ሐሰት አድርጎ ማቅረብ ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ነው። ውጤቱም የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲኖር ያደርጋል። ሥራዎችን ባወቅነው ልክ ስለሆነ የምንሠራው፣ የተሳሳተ ነገር ካወቅን የምንፈጽማቸው ተግባሮች በሙሉ የተሳሳቱ ይሆናሉ። ይህ ደግሞ በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያመጣል ይላሉ።
የምርምርና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሩ፤ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን አሳካዋለሁ የሚሉት ዓላማ ኖሯቸው አቅደው የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ እና መረጃዎችን ሳያጣሩ ስህተት የሆነን ነገር ትክክል አድርገው የሚከተሉ በማለት ይከፍሏቸዋል።
ግብ ያላቸውን ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በሕግ ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ የሚያሳስቡት ገብረክርቶስ (ዶ/ር)፤ ሳያውቁ የሚከተሉትን ወገኖች ግን እውነቱን ደጋግሞ በማሳየት አንዲታረሙ ማድረግ ይቻላል ሲሉ ይገልፃሉ።
መረጃ እንደ ምግብ አስፈላጊ የሆነበት ዘመን በመሆኑ መንግሥት በየጊዜው ትክክለኛ መረጃዎችን መደበኛ በሚባሉት የብዙኃን መገናኛዎች መስጠት መቻል እንዳለበት አስረድተው፤ ለጊዜው በሚስጥር መያዝ ያለባቸው ጥብቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ከሆኑም ፍንጭ በመስጠት ወደፊት ጊዜው ሲደርስ በዝርዝር እንደሚገለጹ ማሳወቅ ይገባዋል ይላሉ።
የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ሥራ ላይ ካልዋለ መደንገጉ ብቻ ውጤት እንደማያመጣ ጠቅሰውም፤ ኅብረተሰቡ ያገኘው መረጃ ትክክል መሆንና አለመሆኑን ከተለያዩ ምንጮች ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲሉ ይመክራሉ።
አንተነህ (ዶ/ር) በበኩላቸው በሚያቀርቡት የመፍትሔ ሃሳብ፤ “ሊንጉስቲክ” የሚባል በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መልዕክቶችን መቆጣጠሪያ ዘዴ አለ። የማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፎችን ከምስሎች ጀምሮ ቃል በቃል እያጣራ ተደጋጋሚ የሐሰት መረጃዎችን እና የጥላቻ ቃላትን በመቶኛ በማስቀመጥ የሚያሰራጯቸውን ግለሰቦች በመለየት ተጠያቂነት እንዲኖር ያደርጋል። መንግሥት በዚህ ላይ እየሠራ ነው። በአማርኛ ተሠርቶ አልቆ በኦሮምኛ፣ ትግሪኛ፣ ሶማሌኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች እየተዘጋጀ ይገኛል ይላሉ።
መወሰድ ያለባቸውን ተጨማሪ የመፍትሔ እርምጃዎች ሲጠቁሙም፤ መንግሥት ፌስቡክን እና ዩቱዩብን ከመሰሉ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ አስተዳዳሪዎች ጋር በጋራ በመሥራት ኃላፊነት እንዲወስዱ ማድረግ መቻል አለበት። ተቋማትም ትክክለኛ መረጃ የሚሰጡበትን ይፋዊ ገጻቸውን በሚገባ በማስተዋወቅና ሐሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ ፈጥነው እውነተኛውን መረጃ ለሕዝብ በማድረስ መታገል አለባቸው ይላሉ።
የሐሰተኛ መረጃዎች ሰለባ የሚሆነው ኅብረተሰብ መረጃዎችን ማጣራት እንዲችል ተደማጭ የሆኑ ሰዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የትምህርት ተቋማት የኅብረተሰቡን ንቃተ ሕሊና የሚጨምር ሥራ መሥራት ይኖርባቸዋልም ብለዋል።
ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ የሚታየው ቀደም ሲል የነበሩን ኢትዮጵያዊ ባሕላዊ እሴቶች ወደ ኋላ የመቅረት ነጸብራቅ መሆኑን የገለጹት መምህሩ፤ በዋናነት እንደ መከባበር፣ መቻቻል እና አብሮነት ያሉ ኢትዮጵያዊ እሴቶች በብዙኃን መገናኛዎችና በትምህርት ሥርዓት ጎልብተው አንድነት ያለው ኅብረተሰብ እስካልተፈጠረ ድረስ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መቀጠሉ አይቀርም ሲሉ አሳስበዋል።
መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. የጸደቀው የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ፣ ማንኛውም ሰው የሐሰት መረጃን በአደባባይ ስብሰባዎች፣ በብሮድካስት፣ በሕትመት ወይም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሑፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለ ተግባር መሆኑ ይደነግጋል።
- ሰው ሰራሽ ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን መቀላቀል የኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ?አርተፊሻል ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይችላል፤ ይህ በአለም ላይ በኢትዮጵያ የአፋር ምድር ረባዳነት የተነሳ ተፈጥሮ የሰጠው እድል ነው! በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል አርተፊሻል ቦይ በመስራት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት መሆን ትችላለች፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሊፈጠር የቻለው፤ የኢትዮጵያ የአፋር ቦታ ከባህር ወለል በታች እስከ 110 … Read moreContinue Reading
- ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥሩን አጠንክሮ እንደሚገፋበት አስታወቀ፤ ህገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ለመግራት የግንዘብ ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፤ ተጠናክሮ ክምሩ እንደሚሰራበትና ግሽበትን በዓመቱ መጨረሻ 20 ከመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተሰማ። ህገወጥ የወርቅ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና የማበረታቻ መደረጉ ለውጥ ቢያሳይም በቂ እንዳልሆነ ተመለከተ። … Read moreContinue Reading
- የኮሚሽኑ የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሙስና ክስ ጋር ተያይዞ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነየአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የአልባሳት ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ። ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ … Read moreContinue Reading
- መንግስት የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ ነበሩ ያላቸውን 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ አስወጣ፣ የሰርቁትን ይከፍላሉየታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የመንግሥት የ2016 የመጀመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው። የግምገማው ተሳታፊዎች መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ጨምሮ በርካታ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጡ ተግባራትን ማከናወኑን አድንቀው፤ ሆኖም” ድጎማው … Read moreContinue Reading
- በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተው ፋብሪካ ከመጋቢት በሁዋላ የሲሚንቶ ዋጋ ወደ ነበረበት የሚመልሰ ነውበቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ ያለውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል። ምርቱ በተባለው ወር ሲጀምር የሲሚንቶ ዋጋ አሁን ካለበት በግማሽ እንደሚወርድ ይጠበቃል። ከመጋቢት በሁዋላ ፋብሪካው በ50 በመቶ የሲሚንቶ እጥረቱን ያስወግዳል። ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ … Read moreContinue Reading