የሃሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ተራ ተግባር መሆኑን ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ፤
ከፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት ንግግር በማስመሰል ተፈብርኮ የተለቀቀውን ድምጽ አስመልክቶ ፓርቲው ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ እንዳሉት፣ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ሃሰትና የፓርቲው ፕሬዝዳንት በተለያየ መድረክ ላይ ከተናሩት ንግግሮች ተቆራርጦ የተፈበረከ ነው፡፡
አለማውም ህዝቡን ማደናገርና ህዝብና መንግስት መካከል ያለመተማመን እንዲፈጠር ብሎም ውጥረትና ያለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ቢቂላ፣ ተግባሩንም ተቀባይነት የሌለው ሃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የሚሰራጭ የወረደ ተግባር ነው ብለውታል፡፡
በዚህ ተግባርና ከጀርባ ያለው ድብቅ አጀንዳ ላይ የኢትዮጵያን እድገት የማይፈልጉ የውስጥ እና የውጭ አካላት እጅ እንደሚኖር ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡
መሰል የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት ባለፉት ቅርብ አመታት እየተለመደ መጥተዋል ያሉት ሃላፊው ህዝቡ መሰረት ከሌላቸውና ምንጫቸው ካልታወቀ መረጃ እንዲጠበቅና መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲመርጥ አሳስበዋል፡፡
ebc
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው”… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”