Site icon ETHIO12.COM

በ 2013 እና 2014 ምርት ዘመን 374 ሚለዮን ኩንታል ምርት ይገኛል

በ 2013 እና 2014 ምርት ዘመን 12.7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለልማት የዋለ ሲሆን ከዚህም 374 ሚለዮን ኩንታል ምርት እንደሚገኝ በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኢሳያስ ለማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በዘር አቅርቦቱ ላይ በበቆሎ ሰብል ላይ ከተከሰተው እጥረት ውጪ በሌሎች ሰብሎች ላይ የምርጥ ዘር አቅርቦቱ እየተሻሻለ መምጣቱን ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡

በቆሎን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ላይ የሚታየውን የሰብል እጥረት ለመቅረፍም በሃገር አቀፍ ደረጃ በምርምር ስራዎች የወጡ ዘሮች እንዲሰራጩ እየተደረገ እንደሚገኝ አቶ ኢሳያስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

የግብዓት አቅርቦቱን ተደራሽ ለማድረግም በሚሰራው ስራ እስካሁን ከ 55 ሺ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለክልሎች ተደራሽ መደረጉንም ሰምተናል፡፡


Exit mobile version