Site icon ETHIO12.COM

ሴናተ ጂም ኢንሆፍ ለሕዝብ የማይታዩ የቪዲዮ መረጃዎችን መከራከሪያ ሊያደርጉ ነው፤ “ሪፐብሊካኖች ትህነግ እንዲነቀል ይፈልጋሉ”

UNITED STATES - SEPTEMBER 17: Sen. James Inhofe, R-Okla., speaks at the FRC's Values Voter Summit in Washington on Friday, Sept. 17, 2010. (Photo By Bill Clark/Roll Call via Getty Images)

በሜይ 31 አዲስ አበባ መጥተው የነበሩት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በቆይታቸው ካካሄዱት ውይይት በተጨማሪ ለሕዝብ እይታ የማይቀርቡ የቪዲዮ ምስልና የድምጽ መረጃ ተሰንዶ እንድተሰጣቸው፣ ይህንንም መረጃ ከባልደረቦቻቸው ጋር እየሰሩበት መሆኑ ሲታወቅ ሮይተርስ “ሃሳብ ለማሳት” በሚል የማይካድራውን ጭፍጨፋ በትግራይ ተወላጆች ላይ ብቻ እንደተፈጸመ አስመስሎ መዘገቡ ታወቀ። መንግስት ለሮይተርስ የፈጠራ ዘገባ ምላሽ አልሰጠም።

“የተጋነነ፣ የአንድ ወገን የሆነና መልኩን እየቀያየረ የማጥቃት ዘመቻ ከሚያካሂዱት ሚዲያዎች መካከል ይመደባል” የሚባለው ሮይተርስ ” የጎሳ ግድያ እንዴት ተቀጣጠለ” How ethnic killings exploded from an Ethiopian town የሚል እርእስ አለው። ስለማይካድራ ጭፍጨፋ ጁን ሰባት የቀረበው ልዩ ሪፖርት ማይካድራ የአማራ ሃይሎች በትግራይ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ እንደፈጸሙ የሚያትት ነው።

ሮይተርስ ምዕራባዊ ትግራይ ክልል ጦርነት ከተነሳ በሁዋላ ብዙም ሳይቆይ ማይ ካድራ በምትባል የእርሻ ከተማ ውስጥ የዘር ግጭትን አስመልክቶ እርስ በርሱ የሚጋጩ ዘገባዎች መሰማታቸው አስታውሶ፣ ዓመፅ እንዴት እንደተጀመረ እና ከዚያ በኋላ የተከተለውን የበቀልና ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ሪፖርት “እርስ በርስ ይጋጫል ያለውን ሪፖርት ለማጽዳትና ሃቁን ለማሳየት” በሚል እንዳዘጋጀ ሊናገር ይሞክራል።

120 የሚጠጉ የአካባቢውን ነዋሪዎችና ሱዳን ሸሽተው የሄዱ ስደተኞች ማነጋገሩን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘገባውን ቢያትትም በስም፣ በአድራሻ፣ በማንነትና በብሄር የሚታወቁትን ሰለባዎች ለይቶ አላስቀመጠም። በሺ የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆችን መታረዳቸው እውነት ሆኖ ሲያበቃ፣ ይህንን እውነት ማስተባበል ስለማይቻል፣ ሪፖርቱ የጠቀሳቸው ወገኖች የአማራ ሃይልን አማራ ለምን ሊገል እንደሚችል ምክንያት ማቅረብ አይችልም። ከዚያም በላይ ግድያው ሲፈጸመ አካባቢው በማን ቁጥጥር ስር ነበር ለሚለው ጥብቅ ጉዳይ መከራከሪያ የለውም። ለዚህ ነው እንግዲህ ጉዳዩ የሴናተሩን ዘመቻ ለማሰናከል ተደርጎ የተወሰደው።

ሮይተርስ ብቻ ሳይሆን ” አማራ ነን” የሚሉ አንዳንድ ክፍሎችና 360 ሴናተሩ ” እጃቸውን ከአማራ ላይ ያንሱ” በሚል ቅጥ አንባሩ የጠፋበት አስተያየት ሲሰጡ ነበር። ሴናተር ቀደ ባሉት ጊዜያት የተለያዩ ህጎች እንዳይጸድቁ ማድረጋቸውን በመጠቆም ለዛሬው ስራቸው ምስጋና እንደማያሻቸው ሲቀሰቅሱም ነበር። በማ

ሴናተር ኢንሆፍ 360 ታማኝ ምንጮቹ እንደነገሩትና እንደዘገበው ሳይሆን አዲስ አበባ የቆዩት ለ18 ሰዓታት ብቻ ሆኖ ሳለ ፓርላማ ቀርበው የኢትዮጵያን ልዩ ሽልማት እንደሚሸለሙም ሲዘገብ ነበር። 24 ሰዓታት ባልሞላው የአዲስ አበባ ቆይታቸው ” ፓርላማ ልዩ ሽልማት ሊሰጣቸው ነው” በሚል ልዩ ፕሮግራም እንደተያዘና የብርጭቆ ዋንጫ የሚመስል ፎቶ በማሳየት 360 ትንተና በሚያቀርብበት ሰዓት ከሴናተሩ ጋር በአገር ጉዳይ እየሰሩ ከሚገኙ መካከል ለኢትዮ 12 የገለጹ እንዳሉት ” ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት አጣብቂኝ ከታደጉ ቢሸለሙስ” ሲሉ ግርምታቸውን ይገልጻሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ

በኢትዮጵያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብና የቪዛ እገዳ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንደሌለው ያስታወቁት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አዲስ አበባ በነበራቸው አጭር ቆይታ ትህነግ አካላዊ ጉዳት ያደረሰባቸው፣ የሰጡት ምስክርነት፣ ለሕዝብ ቢተላለፍ ውጤቱ መጥፎ ስለሚሆን የአማራ ክልልና የፊደራል መንግስት እንዳይሰራጭ ያገዱት የማይካድራ ጭፍጨፋ ቪዲዮ፣ በጭፍጨፋው የተቀጠፉ ሰዎች ሙሉ ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም ጭፍጨፋዉን ከመሩ ሃይሎች የተሰጠ ምስክርነት የተካተተበትንና ሌሎች መረጃዎች ተሰጥቷቸዋል።

የኢትዮ 12 መረጃዎች እንደሚሉት ሴናተር ኢንሆፍ በዝግ መረጃውን ለባልደረቦቻቸውና ይጠቅማሉ ላሉዋቸው ወገኖች አሳይተዋል። ይህ መሆኑ በመሰማቱ ሮይተርስ የማይካድራውን ጭፍጨፋ መልክ የሚያስቀይር ሪፖርት ቀድሞ እንዲያወጣ ተደርጓል። በመጨረሻ –

የማይካድራ ጭፍጨፋ ሆን ተብሎ በዝግጅት የተፈጸመ፣ የተጨፈጨፉት ሰዎች በስም የሚታወቁ፣ የአማራ ትወላጆች እንደሆኑ፣ ጭፍቸፋውን የፈጸሙት ክልሉን የሚያስተዳድሩት አካላት፣ ፖሊስ፣ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና ሳምሪ የተባለ ኢመድበኛ አደረጃጀት መሆኑንን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በይፋ ሪፖርቱ ማስታወቁ አይዘነጋም። ኮሚሽነር ዳንኤልም ይህንኑ በይፋ መናገራቸው ይታወቃል።

ይህንን እውነት ነው ሮይተርስ ያዛባው

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባቻ ሳይሆን አምነስቲና ሂውማን ራይትስ ዎችም ተመሳሳይ ሪፖርት አቅርበው ነበር። ቪኦኤ በምስል አስደግፎ ቅንብር ማቅረቡም አይዘነጋም።

ጦርነቱ እስከሚጀመር፣ ተጀምሮም አካባቢውን መከላከያ እስከሚቆጣጠር ድረስ አካባቢው በትህነግ ቁጥጥር ስር እንደነበር የቪኦኤ ዘጋቢ በቪዲዮ ምስክርነት ሰጥቷል። ገሃድም ጉዳይ ነው።

ሴናተሩ ምን ሊያደርጉና ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ዘመቻ እንዴት ለያመጣጥኑት እንደሚችሉ ግልጽ ባይሆንም፣ የመረጃ ሰዎቹ እንዳሉት የሪፐብሊካን ፓርቲ ሴናተሮች መረጃውን ተመልክተውታል። በቀጣይም የሚይዙት አቋም ይጠበቃል። እንደ ወሬው መረጃው አስደንግጧቸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቀደመውን ሪፖርቱን በሚጻረር መልኩ እርስ በርስ የሚጋጭ መረጃ እያወጣ ነው። ኢትዮ 12 የኮሚሽኑንን የተምታታ መረጃ ማጥራት እንዳለበት ሲወተውት ቆይቷል። ይባስ ብለው ዶክተር ዳንዔል በአርት ቲቪ ላይ ቀርበው ” የትህነግ አመራሮች ትዕዛዝ ስለመስጥታቸው መረጃ የለም” ሲሉ ተደምጠዋል። ምርመራውም ሱዳን ድረስ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ማይካድራ በአጭር ሰዓት፣ በተደራጁ የሚታወቁ ሃይሎች፣ ሰፊ ቁጥር ያለው ህዝብ ያለቀበትና የተጨፈጨፉት ሰዎች በስምና በአድራሻ የሚታወቁ ሆነው ሳለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ ኮሚሽን ይህንን ጠንቅቆ እያወቀ የተጠቃለለ ሪፖርት ከማቅረብ ለምን ወደሁዋላ እንዳለ ለበርካቶች ጉዳዩን የሚከታተሉ እንግዳ ነው። የማይካድራን ግዙፍ አድራጊዎቹ የሚታወቁበት ጭፍጨፋ እያለ ዶክተሩ “እነ ስብሃት ነጋን ጎበኘሁ” አስገራሚ ሪፖርት ያሰራጩ ነበር።

አስቀድመው ካወጡት ሪፖርት በተጨማሪ ኢትዮ ቲዩብ ላይ ቀርበው ጭፍጨፋውን ማን እንደፈጸመው ያስታወቁት ዶክተር ዳንኤል የኮንጎንና የሩዋንዳን ጉዳይ በማንሳት ነጹሃንን የጨፈጨፉ ወንጀለኞች ከስደተኛ ጋር ተመሳስለው ወደ አጎራባች አገራት እንደሚሄዱም አመልክተው ነበር። ኮሚሽነሩ ይህን ሲናገሩ ቆይተው ” የትህነግ ሰዎች ትዕዛዝ ሲሰጡ እንደነበር የሚያረጋገጥ መረጃ አላገነንም” ሲሉ በአርት ቲቪ መናገራቸውና ሮይተርስ አሁን የተሳሳተ ዘገባ ማዘጋጀቱ ምን አልባትም ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ስጋት የገባቸው እየጠቀሱ ነው።

መንግስት ለምን ለሮይተርስ ምላሽ እንዳልሰጠ የጠይቅናቸው ዲፕሎማት ” የሚዲያዎቹ አካሄድ ይታወቃል” ካሉ በሁዋላ ” ሪፐብሊካኖች ትህነግ ከቀጠናው እንዲነቀል ይፈልጋሉ፤ እዛ ላይ እየተሰራ በመሆኑ ለሮይተርስ ዘመቻ መልስ መስጠቱ ብዙም ትርጉም የለውም” ብለዋል።

ዴሞክራትስ ወደ ዋይት ሃውስ ሲመለሱ ዶናልድ ትራምፕ ያባረሩዋቸው የትህነግ ደጋፊና ተከፋይ ባለስልጣኖች ዳግም መመለሳቸው አሜሪካ አሁን ለያዘችው አቋም ዋንኛ ተጠቃሽ ምክንያት ነው። በታሪክም በአብዛኛው ዴሞክራቶች ኢትዮጵያ ላይ ታሪካው ስህተት በመስራት የሚታወቁ ናቸው። የትህነግ የውጭ ክንፍ ለባይደን ምርጫ በጀት መድቦ ሲቀሰቅስ እንደነበር የሚታወስ ነው።


Exit mobile version