ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ አለማየሁ የትዊተር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና መመረጧን ድርጀቱ አስታውቋል፡፡
እያደገ በመጣው ገበያ ከ20 ዓመታት በላይ የኢንቨስትመንት እና የገበያ ባለሞያነት ልምድ ያላት ሚሚ ለቦርድ አባልነት አብቅቷታል ተብሏል፡፡
ሚሚን ለቦርድ አባልነት ያበቃት በተለያዩ አዳጊ ገበያዎች በመንግሥት እና የግል የኢንቬስትመንት እና የፋይናንስ ዘርፎች ከ20 ዓመታት በላይ በመስራት ያካበተችው ልምድ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ሚሚ ያላት ይህ ሰፊ ተሳትፎ እና ልምድ ትዊተር በዓለም ዙሪያ የህዝብ ውይይትን ለማዳበር የያዘውን ተልዕኮ ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ ፒቼት ገልፀዋል፡፡
ሚሚ የትዊተርን ማህበራዊ ኃላፊነት እና ዓለምአቀፋዊ ማህበረሰብን የመፍጠር ተልዕኮ ትጋራለች ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ትዊተር በተለይ በአፍሪካ ያለውን ተልዕኮ ለማስፋፋት በጋና ቢሮ በመክፈቱ የሚሚን ስራ እንፈልገዋለን ብለዋል፡፡
በዓለም ላይ ህዝባዊ ውይይቶች እንዲዳብሩ ዓልሞ እየሰራ ያለውን ትዊተር አደንቃለሁ ያለችው ሚሚ በበኩሏ የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ አባል በመሆኔ ኩራት ተሰምቶኛል ስትል ደስታዋን ገልፃለች፡፡ ሚሚ አለማየሁ በማስተርካርድ የመንግስት እና የግል ጥምረት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያለገለች ትገኛለች፡፡
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው።… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership