የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ከጎጆ ብሪጅ ማህበር ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል። የከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት ችግርን ከማቅለል አንፃር የተያዘውን እቅድ ለመተግበር ሲባል አብሮ ለመስራት መስማማቱ ተገልጿል።
ይህ ማህበር በቅርቡ ከ1000 የሚልቁና ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን ለመገንባት የዲዛይን ስራ እያከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል። በቀጣይም በዋነኛነት መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ግለሰቦች የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ማድረግ ላይ በማተኮር ቤት ተመዝግበው ለሚጠባበቁ እንዲሁም በማህበር ተደራጅተው እየተጠባበቁ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን ለመደገፍ ማለሙ ተገልጿል።
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አልማው ጋሪ ማህበሩ ቤቶችን በእቅዱ መሰረት ሰርቶ ለማስረከብ እና ሀላፊነቱን ለመወጣት እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል።
የከተማው ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መስከረም ዘውዴ በበኩላቸው በከተማው ያለውን የጋራ መኖሪያ ቤት ችግር ለማቅለል ይዞ የመጣውን አማራጭ ሃሳብ በመቀበል አስተዳደሩ ከማህገሩ ጋር በጋራ እንደሚሰራም በማስታወቅ የጋራ የመግባቢያ ፊርማ ተከናውኗል።
ጎጆ ብሪጅ የግል ይዞታ ኖሯቸው መገንባት ያልቻሉ ግለሰቦችን በማህበር በማደራጀት ከቦታቸው ሳይነሱ ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት በማለም ከ3 ዓመታት በፊት የተደራጀ ማህበር ነው።
በጥላሁን ካሳ EBC
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም ትኩረቴ… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት