ETHIO12.COM

ገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 11 ወራት ከ20.7 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች አከፋፈለ

በፌዴራል የጋራ ገቢዎች ቀመር መሠረት ባለፉት 11 ወራት ከ20.7 ቢሊዮን ብር በላይ የክልሎች ድርሻ መሆኑን በመለየት ማስተላለፍ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ገለጹ።

ይህ የበጀት ክፍፍል ከአለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ 11 ወራት አንፃር ሲታይ የ16.6 ቢሊዮን ብር ወይም 400.14% ዕድገት አለው።ይህ ገንዘብ የክልሎችን የልማት ወጭ በመሸፈን ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ገልጸዋል።

ለክልሎች የተላለፈው የገቢው ምንጭ ከኤክሳይዝ፣ ከተርን ኦቨር፣ ከተጨማሪ እሴት እና ከንግድ ስራ ገቢ ግብር ታክሶች ብቻ የተሰበሰበ ነው ተብሏል።የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፌዴሬሽን ም/ቤት መሻሻል በመቻሉ፣ የተቋሙ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እያደገ በመምጣቱ እና ተቋሙ በተቀመጠው የማከፋፈያ ቀመር መሰረት ክፍፍሉን በአግባቡና በትክክል መስራት በመቻሉ የጋራ ገቢው ድርሻ ማደጉ ተገልጿል።

ክፍፍሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ታላቁና ፍትሃዊ ነው የተባለ መሆኑንን ለማሳየት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገላጭ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል። በሰንጠረዥ አስደግፎ የቀረበው ማስረጃ ሃሜታንና የጎንዮሽ ወሬዎችን ያስቀራል ተብሏል።


Exit mobile version