ETHIO12.COM

የG-7 ሀገራት መግለጫ ስለኢትዮጵያ ምን አለ?

በእንግሊዝ እየተካሄደ ያለው የቡድን 7 ሃገራት ስብስባ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል:: በመግለጫው የኢትዮጵያ ጉዳይም ተካቷል:: በአንቀፅ 54 ላይ የሰፈረው መግለጭ ቃል በቃል የሚከተለውን ይላል።

May be an image of text

ትርጉም

54. “በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ግጭት እና እየወጡ ባሉ ሪፖርቶች ምናልባት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ሁኔታ ውስጥ ሊሆኑ ስለሚችሉ የሰብአዊ አደጋዎች በጣም ያሳስበናል፡፡ የጾታ ጥቃትን ጨምሮ እየተፈፀሙ ያሉ አሰቃቂ ድርጊቶችን እናወግዛለን ፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን (OHCHR) ምርመራዎችንም በደስታ እንቀበላለን እንዲሁም በትግራይ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሙሉ ተጠያቂነት እንዲሆኑና ወንጀለኞቹም ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡ ግጭት በፍጥነት እንዲቆም ፣ ያልተዳረሰ ሰብዓዊ አቅርቦት ወደ ሁሉም አካባቢዎች እንዲደርስ እና የኤርትራ ኃይሎች በፍጥነት እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡ ለችግሩ ብቸኛ መፍትሄ ተአማኒ የፖለቲካ ሂደት ሁሉም ወገኖች እንዲከተሉ እንጠይቃለን፡፡ በቀጣይም የኢትዮጵያ መሪዎች የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶችን በማክበር ላይ በመመስረት ብሄራዊ እርቅ እና መግባባት እንዲፈጠር ሰፋ ያለ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲያራምዱ ጥሪ እናቀርባለን፡፡” ትርጉሙ የተወሰደው ከደጀኔ አሰፋ ነው።

በዚህ አንቀጽ መሰረት ኢትዮጵያ ያልተስማማቸው ከትህነግ ጋር ንግግር የሚባለውን ህሳብ ነው። አልተካተተም። ጥቅል የፖለቲካ ፈውስ እንደሚያስፈልግ መንግስትም አምኗል። አስቀድሞ ተናግሯል። የሚገባ ምክር ነው ተብሏል። አሜሪካ ያወጣቸው መግለጫ ሲጨመቅ አይነት ነውልል


Exit mobile version