Site icon ETHIO12.COM

ከምርጫው ራሳቸውን እንደማያገሉ ፓርቲዎች አስታወቁ፤ “ይህ ማለት ግን ቢሸነፉ ለአሸናፊው እውቅና መስጠት አይደለም”

በተለያየ ጊዜ በግልና በፓርቲ ሲሰጡ የነብሩ አስተያየቶች ተሰባስበው በአንድ ላይ እንደቀረቡ በማስታወቅ ራሳቸውን ከምርጫ እንደማያገሉ ቀድመው ያስታወቁት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ናቸው። ከሳምንት በፊት የአሜሪካንን ውሳኔና ማዕቀብ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበሉ የተናገሩት ኢንጂነሩ የፓርቲአያቸውም ሆነ የህብረታቸው አቋም ለውጥ መነሻ ምን እንደሆነ አላብራሩም።

የህብር ኢትዮጵያ፣ እናት ፓርቲ፣ ባልደራስ፣ አብን እና መኢአድ ፓርቲ አመራሮች ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ምርጫው “በብዙ ችግሮች እና ወጣ ውረዶች የተሞላ” ቢሆንም ራሳቸውን ከምርጫው እንደማይገልሉ በተናገሩበት መግለጫ ላይ ኢንጂነሩ እንዳሉት በምርጫው መሳተፍ ማለት ለመንግስት እውቅና መስጠት ማለት እንዳልሆነ ግን ሰፊ ማብራሪያ በመስተት ነው ያስታወቁት።

የአሜሪካ መንግስት ” ቅድሚያ ሰላማዊ ምርጫ” ሲል ሁሉም ወገኖች በሰላማዊ መንገድ ምርጫ እንዲያካሂዱ ያቀረብውን ጥሪ ተከትሎ ” የምርጫው ሂደት መስፈርት የሚያሟላ አይድለም” ለማለት በተጠራ መግለጫ ላይ ይልቃል ” አጨናፊውን መንግስት እውቅና አንሠጥም” ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ በግልጽ አላብራሩም። ሆኖም ግን በውስጥ ሆነው ለግብር ከፋዩ ህዝብ፣ ለውጩ ማህበረሰብ፣ ለመንግስትና ለምርጫ ቦርድ ችግሮች እንዳሉ ደጋግሞ በማስታወቅ በምርጫው መዝለቅ ከዚህ በፊት ” አኩራፊ ናቹህ” በሚል ሲሰነዘር ለነበረው ወቀሳ በቂ ምላሽ እንደሆነ ገልጸዋል።

” እስከዛሬ ከተደረጉ ምርጫዎች ሁሉ አሳፋሪ” ሲሉ ከዚህ ቀደም የተካሄዱትን “የመቶ በመቶ አሸንፌያለሁ” ምርጫ ይመራ የነበረውን ቦርድ አሁን ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ የሚመሩትን ፓርቲ የተሻለ አድርገው ያቀረቡት ኢንጂነር ይልቃል ” ማፊያ” የሚል ቃል ተጠቅመው ምርጫ ቦርድን ሲያበሻቅጡ ተሰምተዋል። እሳቸው ግን ወ/ት ብርቱካንን በዚህ ደረጃ ለማበሻቀጥ የሚያስችል ስብዕና ያላቸው ሰው ስለመሆናቸው፣ ከሰማያዊ ፓርቲ በስርቆት ስለመባረራቸውና ሌብነታቸውን ማስተባበል አለመቻላቸውን ጠቅሶ የጠየቃቸው ባለሙያ ስለመኖሩ ቃለ ምልልሱ የተደረገበት ቪዲዮ አያስረዳም።

ከዚህ ቀደም ” ከሃጂ” ተብለው ከቅንጅት የተባረሩትና ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ተውግደው የነበሩት ልደቱ አያሌው ምርጫ ቦርድ ያወታውን የአባላት ፊርማ መስፈርት አላሟላችሁም በመባላቸው ወ/ት ብርቱካንን “ተላላኪ” እያሉ ሲሳደቡ ጠያቂው መስቀለኛ ጥያቄ ከመተየቅ ይልቅ ዝም ብሎ ያደምጥ ነበር። ይህንን ያስተዋሉ ታዛቢ ” ሚዲያው ሁሉ የሆነ ዓላማ ያነገበና ሙያዊ ስነምግባር የሌለው በመሆኑ ሰው ሲዘነጠልና ስብዕናው ባደባባይ ሲጣስ ማስቆም አይችልም፤ ስለዚህ ማንም ጀርባው ምንም ይሁን ምን ሚዲያዎቹ ለተቋቋሙበት ዓላማ የሚመች ጉዳይ እስካራመዱ ድረስ አረንጓዴ ይበራላቸዋል። ይህ እንደ አገር ውድቀት ነው” ማለታቸው አይዘነጋም።

አዲሱ የኢንጅነር አቋም ” አገራችንን ለማንም ጠላት አሳልፈን አንሰጥም” የሚል ነው። ከሳምንት በፊት ከአቶ ግርማ ሰይፉ ጋር በኤል ቲቪ ቀርበው ሲምሟገቱ የነበሩት ይልቃል፣ መንግስት ከትህነግ ጋር ሊደራደር እንደሚገባ አስታውቀው ” የአሜሪካንን አቋም እንደግፋለን። ፍጹም ትክክል ነው” ባሉበት አንደበታቸው ” ምንም እንኳን በርካታ ግድፈቶች ቢኖሩበትም ምርጫውን ጥለን አንወጣም” የሚለው አቋም ላይ የተደረሰው አገሪቱን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እንደሆነ ማናገራቸው አስገርሟል።

በዛው መድረክ ከምርጫ እንደማይወጡ ያስታወቁት የአብን መሪ አቶ በለጠ ሞላ ፣“የምርጫውን ውጤት ምንም ይሁን ምን ትቀበላላችሁን?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ፓርቲዎች “ ብያኔያቸውን የሚሰጡት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን እና ቆጠራውን ከተመለከቱ በኋላ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ይህን ሲሉ ስንት ወንበር ወይም ምን ያህል በመቶኛ ስሌት ሲያሸንፉ ውጤቱን ” አሜን” ብለው እንደሚቀበሉ አላብራሩም።

“ውጤት መቀበል አለመቀበል በአጠቃላይ ሂደት ድምር ግምገማ ላይ ተመስርተን የምናደርገው ነው የሚሆነው” ሲሉ የተደመጡት አቶ በለጠ ስሌቱ በምን እንደሚለካ አሁንም አልገለጹም። ኢትዮ አስራ ሁለት ከሳምንት በፊት በተለይ ባልደራስና አብን ከምርጫ እንውጣ ወይስ እንቀጥል በሚለው አሳብ ላይ በአመራር ደረጃ መስማማት አለመቻላቸውን ጠቅሰን ዘግበን ነበር። አሜሪካ ምርጫ ቦርድን እንደምታምን በይፋ ካስታወቀች በሁዋላ ቀድሞ የነበረው ልዩነት ወደ አንድ አቋም ሊመጣ እንደቻለ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ነግረውናል። ሶስት የአሜሪካ ተቋማት፣ የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪካ ህብረት እንዲሁም አገር በቀል ተቋማት የሚታዘቡትን ምርጫ “ውጤት ለመቀበል የውጤት ስሌት አስለተን የመናውቀው ይሆናል” ሲል መልስ መስጠታቸው አግባብ መልስ ስለመሆኑ አስተያየት የጠየቅናቸው ነግረውናል።

የተቀረውን ከቪዲዮው ይከታተሉ


Exit mobile version