Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካ ለምርጫው ድጋፍ በሰጥች ማግስት አምስት ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድንና የምርጫውን ሂደት ኮነኑ፤ ሊወጡ ነው?

በየአቅጣጫው ሕዝብ ምርጫውን አከናውኖ ወደ ተረጋጋ ሕይወት የመለስና አገሩ ላይ የተቃታውን ሴራ ለመመከት ህብረት እየፈጠረ ባለበት ወቅት አምስት ፓርቲዎች ምርጫው መስፈርት የማያሟላ ነው ሲሉ ውግዘት አሰሙ። ባለቀ ሰዓት ምርጫውን ጥለው ስለመውጣታቸው ያሉት ነገር የለም። በኢትዮ 12 አስቀድ ስም ሳይዘረዘር ይህ እንደሚሆን ተነግሮ ነበር።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ(ባልደራስ)፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ እናት ፓርቲ፣ ህብር ኢትዮጵያ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሰኙት ፓርቲዎች በቡድን ዛሬ በራስ አምባ ሆቴል በሰጡት መግለጫ ምርጫው መስፈርት ያሟላ እንዳልሆነ አመልክተዋል። አገሪቱ የተሳካ ምርጫ አድርጋ ስለማታውቅ ተስፋ ሰንቀው እንደነበር በመጥቀስ በተግባር ሲታይ ያሰቡት አልሆነም።

ፓርቲዎቹ በንባብ ይፋ ባደረጉት መግለጫቸው ምርጫው “መሰረታዊ መመዘኛዎችን የማያሟላ ነው” ካሉ በሁዋላ “አስቻይ ሁኔታዎች በሌሉበት የሚካሄድ ምርጫ፤ ሀገር በጉጉት ወደምትጠብቀው ስርዓት አያሸጋግርም” ብለዋል። ይህም በመሆኑ በቀጣይ ምን እርምጃ ሊወስዱ እንደተዘጋጁ አላስታወቁም።

ቀደም ብለን እንደዘገብነው ቅድመ ምርጫ ዳሰሳ ካከናወኑ ታዛቢ ድርጅቶች በጓሮ እንደሰማነው ተቀናቃኝ ድርጅቶችና ፓርቲዎች ምርጫውን የማሸነፍ እድላቸው የተመናመነ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩትና በቅድመ ምርጫ ዳሰሳ አብዛናው ሕዝብ ብልጽግና እንዲቀጥል እንደሚፈልግ ነው የታየው። በዚህ መረጃ መነሻነት አሜሪካ በምርጫ ቦርድ ገለልተኛነት ላይ እምነት እንዳላት፣ ምርጫው በስለም ኮሽታ ሳይኖር እንዲጠናቀቅ፣ ከምርጫ በሁውዋላ በቀጣይ አገሪቱን ወደ አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት ብሔራዊ ንግግር፣ ድርድርና አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ ስትል መግለጫ እንዳወጣች ቀደም ሲል መረጃ የሰጡን ክፍሎች ነግረውናል።

ፓርቲዎቹ አዲስ ነገር ባያሰሙም ቀደም ሲል ይናገሯቸው የነበሩዋቸውን የምዝገባና ከምዝገባ ጋር የተያያዝይ ችግሮች እንደ ተግዳሮት ባነሱበት መግለጫቸው ወ/ት ብርቱካን የሚመሩትን ተቋምም ተዓማኝ እንዳልሆነ ለምሳየት ሞክረዋል።

መግለጫውን ተከትሎ በቅድመ ምርጫ የተሳተፉትን ምንጫችንን የተለየ ነገር ስለመኖሩ ጠይቀናቸው ” ምርጫ ሊካሄድ ቀናት እየቀሩ የምዝገባ ቀን ይራዘም ማለት በየትኛውም አገር የሚደረግ አይድለም” ካሉ በሁዋላ ” ውጤቱን ፍርሃቻ ይሆናል” ሲሉ ዝርዝር ጉዳይ መናገር እንደማይፈልጉ፤ ነገር ገን በቅድመ ምርጫ ትንተና ይኸ ነው የሚባልና ቦርዱን ጥያቄ ውስጥ ሊጥል የሚችል ከባድ ችግር እንዳልተገኘ ገልጸዋል። ጥቃቅን ችግሮች ቢኖሩም በዚህ ደረጃ ሊቀርቡ የሚችሉ እንዳልሆኑ አመልክተዋል።

የባልደራስ የውጭ አገር ምክትል ሊቀመንበርና የ360 የየዕለቱ ተንታኝ ” በባልደራስ የድጋፍ ሰልፍ የህዝብ ሱናሚ ይታየኛል” ባለው መሰረት ሳይሆን ፓርቲው እሱን መሪ አድርጎ መምረጡና ከአብን ጋር መቀናጀቱ አዲስ አበባ ላይ ነጥብ እንዳስጣለው፣ ይህ ደግሞ በዚህ ምርጫ የሚታረም እንዳልሆነ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አመልክተዋል።

ሰሞኑንን የአዲስ አበባ አስተዳደርና መንግስት እያሰራጩ ያሉት የልማት ቪዲዮዎችና የፈጠሩት ስሜት ፓርቲዎቹ አዲስ አበባ ላይ በሚፈልጉት ደረጃ ድምጽ ማግኘት እንደማያስችላቸው አመላክች መሆኑ፣ ብልጽግና ያቀረባቸው አብዛኞቹ እጩዎች በመኖሪያቸው ተቀባይነት ያላቸውና ከሚታሙበት የአንድ ብሄር ጫና ውጭ መሆኑ ፓርቲዎቹ በምርጫው ተስፋ እንዲቆርጡ እንዳደረጋቸው ያነጋገርናቸው ገልጸዋል።

አብን አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን አማራ ክልልም ቢሆን መንግስት ለመሆን የሚያስችለው ድምጽ እንደማያገኝ ፓርቲው ባደረገው የውስጥ ትንተና ማወቁ ለዚህ መግለጫ መነሻ እንደሆነም ስማቸውን እንዳንተቅስ የጠየቁ የፓርቲው ቅርብ ሰው ገልጸውልናል። ፓርቲው ባለቀ ሰዓት ከምርጫው ለመውጣት ዝግጅት ቢኖረውም በውስጥ ይህንን ሃሳብ የማይቀበሉ መኖራቸው እስካሁን በልዩነት የተያዘ ጉዳይ ሆኗል። መረጃውን የሰጡን እንዳሉት ይህ ልዩነት በቀናት ውስጥ ይለይለታል ወይም አደባባይ ወጥቶ በገሃድ ሰው ጆሮ ይደርሳል።


Exit mobile version