Site icon ETHIO12.COM

የአረብ ሊግ በግብፆች ሲዋረድ ! “ኢትዮጵያን የሚባሉ ህዝቦች ምን አይነት ናቸው…” የግብጾች ንትርክ

ሱሌማን አብደላ የግብጽ ሚዲያዎችን እየደነ መረጃ የሚያካፍል ታዳጊ

ኢትዮጵያን የሚባሉ ህዝቦች ምን አይነት ህዝቦችና መሪዎች ናቸው ? አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት ተመድ አረብ ሊግን እንዲህ የሚያብጠለጥሉት ምን አይነት ህዝቦች እንደሆኑ ግራ ግብት ብሎኛል! ክርክሩ በሁለቱ ግብፃውያን መካከል ነው!

በቴሌቪዥን መስኮት የምታዩት የፕሬዝዳንት ሲሲ ደጋፊ ግን ፖለቲከኛ ነው! የመንግስት አክቲቪስትና ፖለቲከኛ በሉት። ትናንት ኳተር የተሰበሰበው የአረብ ሊግ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ይጥልልናል፣ ወይም የሆነ እርምጃ ይወስዳል፣ ወይም የለመዱትን ቀይ መስመር ያሰምራሉ ብለው ተስፋ ጥለውበት ነበር።

ነገሩ ግን እንደዛ ሆኖ ያላገኘው የሲሲ አክቲቪስት ቆይ ግን ለምን ተሰበሰባችሁ?,, አስገዳጅ ስምምነት ላይ ይድረሱ ለሚል መግለጫ ነበር የተሰበሰባችሁት ? 22 አባል አገሮችን ይዘን እንዴት አንዲት አገርን ማንበርከክ አቃተን ሲል ይጠይቃል ?

ቀጥሎም፣ ቆይ ግን የግብፅ ወዳጅ የሆነችው አሜሪካ የህዳሴ ግድቡን ጉዳይ ለምን እንደ ዩክሬን ጉዳይ ትኩረት አልሰጣቸውም ? ትናንት ጆባይደን” ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ የምታደርገው እንቅስቃሴ

አለሜሪካ ቀይ መስመር ነው አለ.? ለምን ኢትዮጵያ በናይል ውሃ ላይ የምታደርገውን ማጭበርበር ቀይ መስመር ነው አላለም.? ለመሆኑ ኢትዮጵያ ማናት ? ቆይ እንዴት ነው ዕርምጃ የማይወሰድባት እያለ ሲፎገላ

« መሃመድ ናስር ቆይ ቆይ ተረጋጋ ውሀ ጠጣ የለህ ከሆነ ደውየ ሱቅ እንዲሰጡህ.» ልንገርህ ብሎ በቴሌቪዥን ሻሻው ላይ እንዳለ አቆመው ! ወዳጄ አለው ያንተ የአረብ ሊግ ምን አዲስ ነገር እንዲፈጥርልህ ፈልገህ ነበር ? እነዚህ ከማውራት ውጭ ተግባር የማያውቁ መሪዎች ምን ያደርጉልኝ ነው የምትለው ?

“ያንተ ፕሬዚዳንት ሲሲ” ቀይ ነጭ እያለ መስመር እያሰመረ ለምን ያሰመረው መስመር ሲጣስበት አረቦች ፍረዱኝ እያለ ሲልሞሰሞስ ምነው አልጠየከውም ?

ጦሬ ከአፍሪካ አንደኛ ነው! ህዝቤ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ነው፣ በላህ ላይ ሱዳን ተጨምራልሀለች፣ ይሄንን መጠየቅ እረስተህ ነው ! አሜሪካ አስረዳችንም እያልክ የምታደነቁረን ? አሜሪካ ምን ታድርግልህ ! «.ሲጀመር የአሜሪካና የግብፅ ግንኙነት ጥቅም እንጅ መርህ አለው.»? እስራኤል ጋዛን በቦንብ አውድማ በነፃ እሰራላታለሁ ያለው መንግስትህ ከአሜሪካ ጋር ሆነን ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁምም ስምምነት ላይ ደርሻለሁ ያለው መንግስትህ ለምን ለነ አሜሪካ

ለነ እስራኤል የሰጠውን ትኩረት ለናይል ውሃ አልሰጠውም ? አውሮፓ ህብረት ምን ያድርግህ ? ተመድስ ምን አድርጉ ይበልህ ? አስር አመት ሙሉ የምንታወቀው፣ በሩጫና ዙረት በፉከራና ሁከት ነው። አንትጩሁ አሁን ግድቡ ይሞላል ያነየ መቸም” ቀላቢህ ሲሲ

« ና ተነስ » ኢትዮጵያን በጦር እንደብድብ ቢልህ አይንህን እየዳጥክ ሰበር ዜና አትልም አልልም ! ከዛ ሱዳን ራሷ ለመኖር ስትል ኢትዮጵያ ሳትደረስ ትመልሳችኋለች። ምክኒያቱም ግድቡ የውሃ ኒኩሊየር ቦንብ የታጠቀ ግድብ ነዋ! አትጫጩ ፣ እያለ ማዋረዱን ቀጠለ፣ ግን ጎበዝ ይቺ ኢትዮጵያ

የምትባል አገር ማናት ? ሲል ራሱም ጠየቀ ግብፅና ሱዳን አመት ሙሉ ያለስምምነት ውሃ ሙላት አይታሰብም አሉ። ዶናልድ ትራፕ፣ ያለ ስምምነት ውሃ መሙላት አይታሰብም አለ

ትናት የአረብ ሊግ ስምምነት ሳይደረስ ውሀ እንዳይሞላ አለ,። ኢትዮጵያ የምትባል ጉደኛ አገር ግን ወዲያውኑ በዘንድሮው ዓመት ውሃውን ከመሙላት ማንኛውም ሀይል አያስቆመንም አለች። የአረብ ሊግን ውሳኔ ላንድ ወገን ያዳላ ነው ስትል አጣጥላቸዋለች ! እንግዲህ ያለው እውነት ይሄ ነው ሲል ትንታኔውን ደመደመ !

ሱሌማን አብደላ

Exit mobile version