” ድርቁ በጣም እየባሰ ነው። መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም” – ዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ
በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ በዞኑ ስላሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ችግሩን በማሳየት ጀምረው ታጣቂ ሃይሎች የህጻናት አልሚ ምግብ፣ የነብሰጡሮችና የ፣ኢያተቡ እናቶችን መደጎሚያ ከጤና ጣቢያ እንዴት እንደሚዘርፉ አብራርተዋል።
ስለ ድርቁ
- ድርቁ በጣም እየባሰ ነው። ባለፈው ጥናት ካጠናን በኋላ ሊደረግ የሚገባው ግን ያልተደረገ በጣም በስፋት ነው ያለው። የምግብ እጥረት እንዳለባቸው በተረጋገጠው መሠረት ህፃናት ነፍሰጡር፣ አጥቢ እናቶች ወደ ተለያዩ ፕሮግራሞች ገብተው ሊደገፉ ነበር። እስካሁን ማሟያ ምግብ በምንለው እጥረት እስካሁን ምንም አልተደረገላቸውም። እኛ እየጮህን ነው። እስካሁን የመጣ፣ የተደረገ ድጋፍም የለም።
- ስለ ጤና
- በሌላ በኩል ድርቅ በተከሰተባችው አካባቢዎች አጠቃላይ የጤና መድህን የምንለው ፕሮግራም የአመት ክፍያው የሚያልቀው አሁን ነው። አልፎ ለማስከፈልም አልቻልንም። በጠቅላላ የጤና አገልግሎታቸው በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ እየገባንበት ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።
- ምን ያህል ህፃናትና እናቶች ናቸው አሁን አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው?
- በድርቅ የተጎዱት ወደ 33,000 የሚሆኑ ሰዎች ናቸው ከአንድ ወረዳ ብቻ። በአጠቃላይ እንደ ዞን በዚህ ድርቅ ተጎድተዋል ብለን የምናስባቸው ከ180,000 በላይ ህዝቦች ናቸው። ከእዚህ ውስጥ የሚበዙት ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች ናቸው። ወደ 7,000 ይደርሳሉ ነፍሰጡርና አጥቢዎች ብቻ። ከአምስት ዓመት በታች ህፃናት በግምት ወደ 18,000 አካባቢ ይደርሳሉ። እነዚህ ሁሉ አስቸኳይ ምግብ የሚፈልጉ ናቸው።
አቶ አሰፋ ታጣቂዎችን በተመለከተ ምን አሉ ?
° ታጣቂዎች የመጀመሪያ ታርጌታቸው ጤና ተቋማትን መዝርፍ ነው። እኛ አገልግሎት ላለማቋረጥ እየታገልን ነው እንጂ እስካሁን 3 የሚደርሱ ጤና ጣቢያዎች፣ ወደ 12 የሚደርሱ ጤና ኬላዎች አሁንም በየቀኑ በታጣቂ ኃይሎች ይዘረፋሉ።
° መጀመሪያ በስፋት ፕላምፕሌት አልሚ ምግቦችን ሲወስዱ ነበር። እነርሱ ምግቦች ለሕፃናትና ለእናቶች ካልደረሱ ወደዛ መውሰድ አስፈላጊ አይደለም ብለን ስናስቆም “ጤና ኤክስቴሽኖችን እናንተ ናችሁ የደበቃችሁት አምጡ አስልኩ” አይነት ነገር ማስፈራሪያ፣ ዛቻ፣ ድብደባዎች እያደረሱ ነው።
° ጋዝጊቭላና ድሀና ወረዳዎች አዚላ የሚባል ክላስተር አለ፣ በዚያ ስር ያሉ ጤና ኬላዎች፣ በጋዝጊብላ ወረዳ ደግሞ አዱፍቃ፣ አርካ ጤና ጣቢያዎች ስር ባሉ ጤና ኬላዎች ላይ ነው እንግልት እየተደረገ ያለው።
° የጤና አገልግሎቱ እየተቆራረጠ ነው። በቋሚነት እየተሰጠ አይደለም። ከአንድ እስከ ሶስት ቀናት በተከታታይ ይሰጣል። ከሆነ ጊዜ በኋላ ይመጡና እደገና ያቋርጡታል። ኮሚዩኒቲ ሰርቪስ የምንለው በጤና ኬላ ደረጃ የሚሰጠው ቆሟል ማለት የሚቻልበት ደረጃ ነው።
ለመፍትሄው ከማን ምን ይጠበቃል?
- – የአጋር ድርጅት ድጋፍ የተቀዛቀዘ ነው። ድጋፍ ማድረግ ቢችሉ የሰዎችን ሕይወት ይታደጋሉ። ከጸጥታው ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል ኤኒይወይስ ስለ ረሀብ ደግሞም ስለ ህፃናት፣ ነፍሰጡር አጥቢ እናቶች ረሃብ ነው እያወራን ያለነው።
- – አይደለም እንደዚህ ድርቅ ተከስቶ አፍጦ መጥቶ ኖርማል በመደበኛ ሁኔታ እንኳ እንደዚህ ለይተናቸው የምግብ እጥረት እንዳለባቸው ሲታወቅ ወዲያውኑ ወደ ፕሮግራም ገብተው መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም።