ETHIO12.COM

ዝርፊያ በትግራይ – «በክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ»

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ገልጿል

የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ አካላት፣ የየዩኒቨርስቲዎች አመራሮች እና ከዓለም አቀፍ ተራድኦ ተቋማት ጋር በመሆን ጉዳዩን እየሰራበት እንደሚገኝ አስታውቋል።

በተደረገው ጥረትም የዩኒቨርቲዎችን አመራር ለማግኘት የተቻለ ሲሆን ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ናቸው ብሏል ሚኒስቴሩ።

ስለሆነም የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸው በመልካም ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ተረድተው በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶችን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሚኒስቴሩ በቀጣይ ተማሪዎች ፈተና ወስደው ሲጨርሱ የሚኖሩ ጉዳዮችን እንደሚያሳውቅ ገልጾ፤ የተማሪ ወላጆች በመደበኛ መገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ መረጃዎችን ብቻ እንዲጠቀሙ እና ተረጋግተው እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

በትግራይ የህክምና ተቋማት ላይ ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን አስታወቀ

ከሳምንት በፊት በትግራይ ክልል እርዳታ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ በአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ባልደረባው የተገደለበት የድንበር የለሽ ሀኪሞች ቡድን በክልሉ የጤና ተቋማት ላይ ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑን ይፋ አደረገ።

አሁን ላይ በክልሉ ያለው ሁኔታ ሰቆቃ የበዛበት ነው ያለው የሀኪሞች ቡድን፤ በዚህ የተነሳ ህዝቡ በስቃይ ውስጥ መሆኑንም አስታውቋል። Vis -ENA

Exit mobile version