Site icon ETHIO12.COM

ጥሞና ለትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር

በኢትዮጵያ ስልጣን ለሃያ ሰባት ዓመታት ይዞ የነበረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በስልጣን ላይ እያለና ከስልጣን ከሄደ በሁዋላ ወይ ከብልጽግና ሆኖ መቀጠል አልቻለ፣ ወይም ክልሉን እየመራ ለመኖር አልወሰነ፤ በአጉል እብሪት ጦርነት ውስጥ ገብቶ ይህንን ሁሉ ውድመት ማስከተሉን አብይ አህመድ አስታወቁ። ብልጽግናን አስቦና አመዛዝኖ ቢቀላቀል ኖሮ የያዘውን ይዞ በህዝብ ይቅርታ ይቀጥል እንደነበር፣ አርፎ እንደ ሌሎች ክልሎች ትግራይን እያተዳደረ ቢቀጥል ሌላው አማራጭ ነበር ሲሉ ሁሉንም መስመር መሰባበሩን አመልክተዋል። ዛሬ በጥሞና ይህን ሁሉ ዞር ብሎ እንዲያስብ መክረዋል። በዋናነት ከፈጸማቸው ሴራዎች

እነዚህ እና ሌሎችም ችግሮች እንዳይከሰቱ በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በተደጋጋሚ ልመናና ሽምግልና ተደርጓል ያሉት ዶ/ር አብይ ፤በግላቸው ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን፤ባለሃብቶችንና የክልሉ ጉዳይ በቅርበት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገራቸውን ነገር ግን ይህ ሳይሆን እንደቀረና ተጠያቂ አመራሮችን በህግ ወደ ሚያስጠይቀው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጀመሩን አንስተዋል፡፡

በጦርነት ሂደት ተሳታፊ እና ተጠያቂ አካላትን ብቻ ለመያዝ ጥረቶች መደረጋቸውን ያነሱት ዶ/ር አብይ ክልሉን ካጋጠመው ውድመትና ኪሳራ መልሶ ለማቋቋምና ለማረጋጋትና ህግን ከማስከበር ዘመቻው ጎን ለጎን ክልሉ በጊዜያዊ መንግስት እንዲተዳደር የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውንም አንስተዋል፡፡

በክልሉ በነበረው ጦርነት የተገኘውን ፋይዳን በተመለከተ ሰሜን እዝን ዳግም መመለስ መቻል፤ ከዚህ በኋላ መከላከያ ጠንካራ አቋም ይዞ እንዲገነባ የሚያስችል ልምድ መገኘቱን፤ ኢትዮጲያዊያንን ለመከፋፋል እንዲሁም ለመለያየት ሲሰራ የነበረው ሴራ እምብዛም እንዳይሳካ ከዚህ ጦርነት ልምድ መወሰዱን ያነሱ ሲሆን በትግራይ ዘመቻ ትልቅ ኪሳራን አድርሷል ያሉትም ዘርዝረዋል።

ጊዜ፤ገንዘብ፤ ከሁሉ በላይ የሰው ሃይል ፤ለ40 ዓመታት የተተከለው የዘረኝነት መርዝ ትልቅ ኪሳራና ጉዳት ሆኖብናል ሲሉ አክለዋል፡፡በመንግስት በኩል የነበረውን ኦፕሬሽን ግን ባልተገባ መልኩ እንደ ስህተት ሲነገር ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡ግጭቱን ማስቀጠል አሁንም ቢሆን ይቻላል ያሉት ዶ/ር አብይ ነገር ግን ይህንን ማድረግ ኪሳራና ያልተገባ መሆኑን ሊታወቅ እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

የፀጥታ ሃይሉ ከትግራይ ክልል እንዲወጣ የተደረገበትን ምክንያት በተመለከተ በክልሉ ያለውን የፀጥታ ሃይል የማስወጣት ዘመቻ አንድ ወራትን ያክል እንደፈጀና በአራት ዙር ይሄንን ትጥቅ የማስወጣት ሂደት መካሄዱን አስታውቀዋል፡፡ይህንንም በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽና የሚያሳድረውን ውጤት በቅርቡ እናየዋለን ያሉት ዶ/ር አብይ፤ አሁንም ቢሆን ቆም ብሎ ማየት እንደሚበጅና የተወሰነው ውሳኔ ለኢትዮጵያዊያን የሚጠቅምና ውጤት እንደሚያመጣም አስታውቀዋል፡

መከለከያ መውጣት ሲጀምር ስራውና ንብረት ማጓጓዙ እጅግ ሰፊ ስለነበር ከወር በፊት መጀመሩን አመልክተዋል። በሺህ የሚቆጠር ተሽከርካሪ በማነቃነቅ የመጀመሪያው ነቅናቄ ከወር በፊት መካሄዱን፣ ከምርጫው በፊት ባሉት ቀናቶች ሁለተኛ ደረጃ እንቅስቃሴ ተደርጎ ጦሩ መልቀቁን፣ በሶስተኛ ደረጃ ከመሃል ትግራይ አካባቢ ንቅናቄ ሲጀመር መንገድ ባመዝጋት፣ ጎማ በማቃጠል፣ ሰራዊቱ ላይ መንገድ በመቁረጥ ህዝብ እንቅፋት መሆኑን፣ በአራተኛው ንቅናቄ ግን ከመቀሌ ጦሩ ሲወጣ በሺህ የሚቆተር መክና አሰልፎ ነበርና አንድም የተተናኮለው ሃይል እንደሌለ አመልክተዋል። ከፊል ዜናው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ፌስ ቡክ የተወስደ ነው።

Exit mobile version