Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካ ወጣች ታሊባን ገባ

የአፍጋኒስታን ወታደሮች ወደ ጎረቤት ታጂኪስታን መሸሻቸውን ተከትሎ የታሊባን ሃይሎች ባዳክህሻን እና ካንዳሃር አካባቢ የሚገኙ አስተዳደራዊ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል።

የታሊባን ተዋጊዎች ወደ ድንበሩ ሲያቀኑ ከ300 በላይ የአፍጋኒስታን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን የባዳክህሻን ግዛት ወደ ታጂኪስታን መሻገራቸውን የታጂኪስታን ብሔራዊ ደህንነት ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

”በመልካም ጎርብትና እና በሰብዓዊነት ” መርህ ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉትን የአፍጋኒስታን ወታደሮች ወደ ታጃኪስታን ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ መፍቀዳቸውን ባለስልጣናቱ በመግለጫቸው አክለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአፍጋኒስታን “የዘላለም ጦርነት” አብቅቷል ብለው ካወጁ ከሚያዝያ አጋማሽ ጀምሮ የታሊባን ሃይሎች በመላ ሃገሪቱ መስፋፋታቸው ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም ወሣኝ የሚባሉ ቦታዎችን የተቆጣጠሩት በሰሜናዊ አፍጋኒስታን ግማሽ ክፍል ሲሆን÷ ይህም በፈረንጆቹ 2001 የአፍጋን ወታደሮች ታሊባንን ለማሸነፍ የረዳቸውና የአሜሪካ መራሹ ጦር ምሽግ ነው ፡፡ ታሊባን በአሁኑ ጊዜ በአፍጋኒስታን ውስጥ ካሉት 421 አስተዳደራዊ አካባቢዎች 1/3 መቆጣጠሩ ይነገራል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

Exit mobile version