ጥቂት አጭር መረጃዎች – የእስራኤልና የሃማስ ጦርነት

የእስራኤልና የፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት ዛሬም መቀጠሉ ተነግሯል።ጦርነቱ ሰፍቶ ሌሎች ኃይሎችም እንዳይጨመሩ ስጋቶች ከቀን ወደ ቀን እያየሉ ነው።

✔️- እስራኤል የሰብዓዊ እርዳታ በግብፅ እና ጋዛ ድንበር በኩል ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዲገባ ፈቅዳለች ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች ቢዘገብም የእስራኤል ጦር  ” የተኩስ አቁም የሚባል ነገር የለም ፤ መሻገሪያዎቹም እንደተዘጉ ናቸው  ከወንጀለኛው ሃማስ ጋር መዋጋታችንን እና ማጥቃታችንን እንቀጥላለን። ጋዛ የትግላችን ማዕከል ናት የታገቱ እስራኤላውያንን ይዛለች  ” ብሏል።

✔️- ” ሃማስ የፍልጤምን ህዝብ አይወክልም ” ያሉት የፍልስጤሙ ፕሬዜዳንት ማሃሙድ አባስ ” በሁለቱም በኩል በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈፀመውን ግድያ እቃወማለሁ ፤ በሁለቱም በኩል የታገቱ እና የታሰሩ እስረኞች ሊለቀቁ ይገባል ” ብለዋል።

✔️- ኢራን በጋዛ ውስጥ ላለው ጦርነት የፖለቲካ መፍትሄዎች የሚያገኝበት ጊዜ እያለቀ ነው ስትል አስጠንቅቃለች። ኢራን የጦርነቱ መስፋፋት ወደማይቀርበት ደረጃ መቃረቡን አመልክታለች።

✔️- የእስራኤል ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ፤ ” ግባችን ድል ማድረግና እና ሀማስን ማስወገድ ነው ” ብለዋል። ” ኢራንን እና ለሂዝቦላህን ተጠንቀቁ ” ብለዋቸዋል። ” ለቤተሰቦቻችን ግዴታ አለብን ” ያሉት ኔታንያሁ ” የታገቱትን ሰዎችን እስክንመልስ ድረስ አንታክትም።” ብለዋል።

✔️- ሃማስ ያገታቸውን ሰዎች ለመልቀቅ እስራኤል ውስጥ የታሰሩ 6000 እስረኞች እንዲለቀቁ መጠየቁ ተዘግቧል። ሃማስ አሁን ላይ ከ200 – 250 የሚደርሱ ታጋቾችን መያዙን አመልክቷል። 22 የእስራኤል ታጋቾች በእስራኤል የአየር ጥቃት ተገድለዋል ሲል ገልጿል።

✔️- የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ለተወሰኑ የአሜሪካ ወታደሮች እስራኤል በምትፈልጋቸው ጊዜ ” ለመሰማራት ዝግጁ ሁኑ ” የሚል ትዕዛዝ መስጠታቸውን ፎክስ ኒውስ አንድ ስማቸው ያልተገለፀ ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው ወደ 2,000 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች ተመርጠዋል ፤ ነገር ግን ይህ ቁጥር አልተረጋገጠም ተብሏል።(BirlikEthiopia)


See also  የጠፈር ሽርሽር በረራ ሊጀመር ነው

Leave a Reply