Site icon ETHIO12.COM

አዲስ አበባን በፓርላማ ለመወከል የተመረጡት እነማን ናቸው?

በፎቶው ላይ የሚታዩት የውሃ፣ መስኖ እና ኢንርጂ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ፣ዛዲግ አብርሀ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ ፕ/ር ሂሩት ወ/ማርያም፣ የአገር አቀፍ ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ ናቸው።

በዘንድሮው ምርጫ ብልፅግና ፓርቲ ከ436 መቀመጫዎች ውስጥ 410 ያሸነፈ ሲሆን ለቀጣዩ አምስት አመታትም መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ወንበር አግኝቷል።

ለዘመናት የአገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ማዕከል ሆና በቆየችው አዲስ አበባ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከተማዋ ላይ ባተኮረ መልኩ ፖሊሲዎችን ሲቀርፁና ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ።

በዘንድሮው ምርጫ ብዙ ትኩረት በነበረባት አዲስ አበባ የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 1,819,343 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 99ኛው በመቶ ድምፅ ሰጥቷል።

አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23 መቀመጫዎች ያሏት ሲሆን ገዢው ፓርቲ ብልፅግና 22 መቀመጫዎችን ሲያሸንፍ በግል የተወዳደሩትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መቀመጫ አግኝተዋል።

ለመሆኑ በቀጣዮቹ አምስት አመታት አዲስ አበባን በፓርላማ የሚወክሏት እነማን ናቸው?

የክልል ምክር ቤቶችን በምንመለከትበት ወቅት ብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባን ምክር ቤት ሁሉንም 138 መቀመጫዎችን አሸንፏል።

ምርጫ 2013 በጨረፍታ

ምስጋና ፎቶና ዘገባ ቢቢሲ


Exit mobile version