ለትግራይ ሕዝብ ያለንን ሐሳብ፤ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያለንን ቦታ ለመጨረሻ ጊዜ አሳይተናል። ግጭት ላለማባባስ፣ ለሕዝቡ የእርሻ ወቅት ፋታ ለመስጠት እንዲሁም የርዳታ አቅርቦቱ ያለ ሰበብ እንዲከናወን ስንል በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተናጠል የተኩስ አቁም አድርገናል። ሰላም የተወሰነ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ብናውቅም ይህ ግን የመጨረሻ ሰላማዊ ዕድል ነው።
ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ እንደሚባለው ጁንታው የሰላም መንገድ ሊዋጥለት አልቻለም። አሁን ባለው ቁመናው ያለ ግጭት ውሎ ማደር አይችልም። ሕጻናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛለ። የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ሕጻናት ወታደሮች የመታደግ ሞራላዊ ግዴታ ወድቆበታል።
ለሕዝባችን ስንል የከፈልነው ዋጋ ባልገባቸው ደካሞች ምክንያት ውጤት አላመጣም። ጁንታው የኢትዮጵያ ህልውና ቀንደኛ ጠላት መሆኑን ደግሞ እያስመሰከረ ነው። ይሄንንም መላ ሕዝባችንን አስተባብረን እንቀለብሰዋለን። በአንድ በኩል ሰብአዊ ርዳታ እንዲቀላጠፍ እየሠራን በሌላ በኩል የውጭና የውስጥ ጠላቶች ተናበው የከፈቱብንን ጥቃት መክተን እንቀለብሰዋለን።
ጁንታው ዋሻ ውስጥ ገብቶ ሕዝቡ በረሐብ ሊያልቅ ነው እያለ ሲያላዝን ነበር። ለሕዝቡ ሲባል ሰብአዊ የተኩስ አቁም ሲደረግ ደግሞ የረሐቡን አጀንዳ ትቶ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ጀመረ።
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለ ርዳታና ስለ ረሐብ ሲናገር መቆየቱን ዘንግቶ ጁንታው ሕጻናትን ሲያሰልፍ እንኳን ዝምታን መርጧል። የርዳታ መግቢያ ኮሪደሮችን የግጭት ቦታዎች ሲያደርጋቸው የርዳታ ድርጅቶች አሁንም መንግሥትን ለመውቀስ ይቃጣቸዋል። እነዚህን ሁሉ ከግምት በማስገባት መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ ነገር በተገቢው መንገድ ያደርጋል።
ሕዝባችን ከሐሰተኛ መረጃዎች እና ከጠላት ፕሮፓጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ አሁንም ለማሳሰብ እንወዳለን። ጁንታውና አጋሮቹ ያላቸው ዐቅም ውሸትን መፈብረክ ብቻ ነውና። የውስጥና የውጭ ኃይሎች ፕሮፓጋንዳቸውን አቀናጅተው ሕዝብን ለመከፋፈል እየሠሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ሕዝባችን እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ እንደ አንድ ሠራዊት ሆኖ ለሀገሩ ህልውና በመቆም፣ የመከላከያ ሠራዊቱን በሁሉም ነገር በመደገፍ፣ የውጪውን ጫና እና የውስጡን ትንኮሳ እንዲመክትና እንዲቀለብስ ጥሪ እናቀርባለን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሀምሌ 7, 2013 ዓ.ም
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding the country’s diplomatic activities over the week, Spokesperson of the Ministry Nebiyu Tedla, indicated that Ethiopian delegation led by State Minister of Foreign Affairs Ambassador Mesganu Arga participated in the consultation… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ በላይ ማሻቀቡ ይፋ እየሆነ ባለበት ወቅት ነው። መንግስት ሰላማዊ ዜጎችን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት አግባብ እንዳልሆነ ጠቅሶ ” መንግስታዊ ሃላፊነትን መወጣት ፍርሃት አይደለም” ቢልም የትግራይ አመራሮች ሂደቱ ከመንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት እየተከናወነ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለተከላ ተዘጋጅቷል። ለዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በቂ ቅድመ ዝግጅት መተናቀቁን ያመልከቱት የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ባለፈው ዓመት የተተከለው ችግኝ ዘጠና በመቶ የመጽደቅ ደረጃ መድረሱን አመልክተዋል።… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም ዜናው “ሴራ” ነው በሚል አስተያየት ከሰጡ ወገኖች ጋር የሚስማማ ሆኗል። ቀሲስ በላይ መኮንን አፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢው ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ነገሩ ሲነቃ ከተሰወሩ ግለሰቦች ጋር ተገኝተው በሃሰተኛ ሰነድ 6.5… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት ላይ ጥሎት አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንዲወስድ ያስገደደው? ከሆነም ህብረቱ ይህን አቋሙን ለምን በይፋ ከማስታወቅ ይታቀባል? ነገሩ በዚህ ደረጃ አሳሳቢ ከሆነ ቢያንስ ሁለት መስመር መግለጫ እንዴት ማውጣት ተሳነው …. ብዙ መወያያ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች