Site icon ETHIO12.COM

ሚዲያዎች ትህነግን በስሙ “አሸባሪ” ብለው እንዲጠሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ

የውጭ አገር ሚዲያዎች የትግራይን ጦርነት በሚዘግቡበት ወቅት ‘የትግራይ መከላከያ ኃይል’ ከማለት እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳስቧል።ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ዘገባዎችን ገምግሞም ህወሓትን ብሔራዊ ሠራዊት እንዳለው የትግራይ መከላከያ ኃይል እያሉ የሚጠሩ አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች አሉ ብሏል።

በመግለጫውም ላይ እንደተጠቀሰው የትግራይ ክልል ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን አንዷ አካል ናት ካለ በኋላም የመከላከያ ኃይል ሊኖራትም አይችልም ብሏል።ህወሓት ከፌደራል መንግሥት ጋር ጦርነት ከገባ በኋላ የተለያዩ ኃይሎችንና ከማኅበረሰቡ የተውጣጣ ኃይል መስርቻለሁ በማለት የትግራይ መከላከያ ኃይል በሚልም እየተጠራ ይገኛል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎችም ኃይሉ ራሱን በሚጠራበት የትግራይ መከላከያ ኃይል እያሉም እየጠሩት ይገኛሉ።

ከዚህም በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ሽብርተኛ ብሎ ከመሰየሙ ጋርም ተያይዞ እንዲህ አይነት ስያሜዎችን መጠቀም የአገሪቱን የግዛት አንድነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና ደኅንነት የሚጥስ ነው ብሏል። የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን እንዲህ አይነት ቃላቶችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ ያሳሰበ ሲሆን እነዚህን ቃላቶች መጠቀም ማለት የኢትዮጵያን ሕግ የሚጥስና ጥብቅ እርምጃም የሚወስድ መሆኑን አሳስቧል።

የተወካዮች ምክር ቤት በኅዳር ወር በሕገ መንግሥታዊ መሰረት የትግራይ ክልል መንግሥትን አፍርሶ ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቀኑን እስኪያስታውቅ ድረስ የትግራይ መንግሥት የለም ብሏል።እስከዚያውም ድረስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እየመራ ይቆያል ብሏል መግለጫው።

በመግለጫው በግልጽ ባይነገርም ይህን አክብረው በማይሰሩ የውጭ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አመላካች ሆኗል። ጸዳለ የምትመራው አዲስ ስታንዳርድ በተደጋጋሚ ይህን እንዲታረምና ትህነግን በትክክለኛ ስያሜው እንደትጠራ ቢነገራትም ባለመፈጸሟ ለፍቃዷ መነጠቅ አንድ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።

ቪኦኤና ጀርመን ድምጽም በተመሳሳይ ይህን ድንብ በመጣስ ትህነግን በሌለው ስምና በህግ በተነጠቀ ማንነቱ ሲጠሩት ያስተዋለል።


Exit mobile version