የውጭ አገር ሚዲያዎች የትግራይን ጦርነት በሚዘግቡበት ወቅት ‘የትግራይ መከላከያ ኃይል’ ከማለት እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳስቧል።ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ዘገባዎችን ገምግሞም ህወሓትን ብሔራዊ ሠራዊት እንዳለው የትግራይ መከላከያ ኃይል እያሉ የሚጠሩ አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች አሉ ብሏል።
በመግለጫውም ላይ እንደተጠቀሰው የትግራይ ክልል ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን አንዷ አካል ናት ካለ በኋላም የመከላከያ ኃይል ሊኖራትም አይችልም ብሏል።ህወሓት ከፌደራል መንግሥት ጋር ጦርነት ከገባ በኋላ የተለያዩ ኃይሎችንና ከማኅበረሰቡ የተውጣጣ ኃይል መስርቻለሁ በማለት የትግራይ መከላከያ ኃይል በሚልም እየተጠራ ይገኛል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎችም ኃይሉ ራሱን በሚጠራበት የትግራይ መከላከያ ኃይል እያሉም እየጠሩት ይገኛሉ።
ከዚህም በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ሽብርተኛ ብሎ ከመሰየሙ ጋርም ተያይዞ እንዲህ አይነት ስያሜዎችን መጠቀም የአገሪቱን የግዛት አንድነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና ደኅንነት የሚጥስ ነው ብሏል። የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን እንዲህ አይነት ቃላቶችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ ያሳሰበ ሲሆን እነዚህን ቃላቶች መጠቀም ማለት የኢትዮጵያን ሕግ የሚጥስና ጥብቅ እርምጃም የሚወስድ መሆኑን አሳስቧል።
የተወካዮች ምክር ቤት በኅዳር ወር በሕገ መንግሥታዊ መሰረት የትግራይ ክልል መንግሥትን አፍርሶ ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቀኑን እስኪያስታውቅ ድረስ የትግራይ መንግሥት የለም ብሏል።እስከዚያውም ድረስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እየመራ ይቆያል ብሏል መግለጫው።
በመግለጫው በግልጽ ባይነገርም ይህን አክብረው በማይሰሩ የውጭ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አመላካች ሆኗል። ጸዳለ የምትመራው አዲስ ስታንዳርድ በተደጋጋሚ ይህን እንዲታረምና ትህነግን በትክክለኛ ስያሜው እንደትጠራ ቢነገራትም ባለመፈጸሟ ለፍቃዷ መነጠቅ አንድ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።
ቪኦኤና ጀርመን ድምጽም በተመሳሳይ ይህን ድንብ በመጣስ ትህነግን በሌለው ስምና በህግ በተነጠቀ ማንነቱ ሲጠሩት ያስተዋለል።
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ።… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች