Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ኒኩሌር ታጠቀች

በኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር የህዳሴው ግድብ ዛሬ ለሌት ሲሞላ ” ኢትዮጵያ ኒኩሌር ታጠቀች” ማለት እንደሆነ ባለሙያዎች አስታወቁ። ሲያብራሩም የህዳሴውን ግድብ መሙላት ማለት ግድቡን ከማንኛውም ክፉ ሙከራ መታደግ እንደማለት ነው።

“በኢትዮጵያዊያን ደም፣ አጥንትና ላብ የተሰራ ነው” ሲሉ ድየውሃና መስኖ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ የገለጹት የህዳሴው ግድብ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ተገባዷል። ወይም እንደተገባደደ ይታመናል። በዚሁ ሂሳብ መሰረት ከፍታው ከባህር ወለል በላይ 574 ሜትር ሆኗል። ዶክተር ስለሺ በተደጋጋሚ እንደተናገሩት የውሃው ሙሌት ሲጠናቀቅ በሁለት ተርባይን የኤሌክትሪክ ሃይል ለማምረት የተያዘው ዕቅድ የሚሳካ ነው።

የሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት አስመለክቶ ግብግብ ፈጥራ የነበረችው ግብጽ የውሃው ሙሌት ጫፍ መድረሱንና ምንም ማድርተግ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን ስትረዳ አልሲሲ “ኢትዮጵያን በልማት ማገዝ እንፈልጋለን” ማለታቸውን ያስታወሱ ባለሙያዎች እንዳሉት ካሁን በሁዋላ የህዳሴው ግድብ ጥበቃ አያስፈልገውም።

ግብጽ ግድቡን ብትመታ ሽቅብ ወደላይ ሳይሆን ወደታች ሲወርድ ሱዳንና ግብጽን ተረት እንደሚያደርጋቸው በሂሳብ የሚያስረዱ እንዳሉት፣ ግብጽ ካሁን በሁዋላ ማተረማመሷን ታስቀጥል ካልሆነ በቀር ህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ አንዳችም ክፋት ማሰብ አትችልም።

ነገ የወሃው ሙሌቱ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያዊያን በይፋ ” ኒኩሌር ታጠቁ እንደማለት ነው” ሲሉ የተናገሩትም በዚሁ መነሻ መሆኑንን አመልክተዋል። “ምርጫ ካካሄደች ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” ሲባል የተሳካ ምርጫ ማካሄዷን፣ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ሙሌት መሳካቱን አንድ ላይ አዳምረው ለኢትዮጵያዊያን ይህ ታላቅ የድል ዜና እንደሆነ እየተገለጸ ነው።


Exit mobile version