ከግንባታ አልፎ የፖለቲካ አቅም የሆነው የህዳሴ ግድብ ንግግር ተቋጨ፤

ዛሬ ከፕሮጀክትነት አልፎ የፖለቲካ አቅም የሆነው የህዳሴው ግድብ እጅግ ሰፊ የማጥላላትና ህዝብን የማነሳሳት ቅስቀሳ ሲካሄድበት እንደነበር በመጥቀስ በርካቶች አስተያየት እየሰጡ ነው። ከግንባታው ሩጫና ድካም ባልተናነሰ ህዝብ እንዲያምጽ በፈጠራ “ዋጋ ቢስ ሆኗል” የተባለው የህዳሴው ግድብ ሁሉንም አልፎ ዛሬ ተጽዕኖ ፈጣሪ ደረጃ ላይ በመድረሱ ” ኢትዮጵያ ኒኩሊየር ታጠቀች” እስከማለት ደርሷል።

” የህዳሴ ግድብ ተሸጠ” ሲል በአቶ ጌታቸው አማካይነት ትህነግ ሳይታክት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ የማጥላላት ዘመቻ ሲያካሂድ ነበር። ” ውስጥ አዋቂዎቼ ነገሩኝ” ሲል ዋዜማ “ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግስት የመፈረም ፍላጎት እያሳየ ነው” ሲል ግድቡን አስመልክቶ ዛሬ ድረስ “ዋሽቻለሁ” በሚል ይቅርታም ሆነ ማስተባበያ ያልሰጠበት ዜና የሚታወስ ነው። ሁሉም ወገኖች የሚከሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ነው።


ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ

ዜናው መረጃ የሚያስተላለፍ መሆን ሲገባው ግምት፣ መላምት፣ ጠማማነትና ምኞትን የሚገልጽ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከዚህ ይልቅ ግን የዘነጋው አንድ ትልቅ እውነታ አለ – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ስምምነቱ እንዳይፈረም መመሪያ ስለመስጠታቸው ነው።

ሙሉውን ሊእዚህ ላይ ሊንኩን በመጫን ያንብቡ


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሱዳን ጉዳይ ለመምከር ግብጽ በተጓዙበት ወቅት ከፕሬዚዳንት አልሲሲን ጋር ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውንና የህዳሴው ድርድር በቅርቡ፣ አነሰ ቢባል በአንድ ወር ውስጥ እንደሚጀመር ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀው ነበር። በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ንግግር ካይሮ ላይ ተካሂዶ ተጠናቋል።

ይህን ድርድር አስመልክተው አንዳንዶች በቲውተርና በማህበራዊ ገጾቻቸው ትችት ሰንዝረዋል። እዚህ ግባ የሚባል ከጉዳዩ ጋር እውቂያ የሌላቸው ” ግድቡ ለአረብ ኤመሬትስ ተሽጧል” የሚል ከመላ ምትም በታች የሆነ ጽሁፍ አሰራጭተዋል። ይሁን እንጂ ” ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥቅም በሚሰጥ እና ፍትሐዊ አጠቃቀምን በሚያረጋግጥ መልኩ እየሠራ ይገኛል” ሲሉ አምባሳደር ስለሺ በቀለ የሚመሩትን ቡድን ሚና አስታውቀዋል።

በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ፊት ፍትህ ተጓድሎባት ስትሰቃይ ለነበረችው አገራቸው ምስክርና ሞጋች የነበሩት የድርድሩ ቡድን መሪ በወቅቱ ያቀረቡት ንግግር ታሪካዊ፣ እንደ ዜጋ እልህ ውስጥ የሚከት እንደነበርም አይዘነጋም። “ምናልባትም በታሪክ ኢትዮጵያ ብቻ ለምን ግድብ ሰራሽ ተብላ በጸጥታው ምክር ቤት ፊት የቀረበች አገር ሆና ትኖራለች። ይህ ታሪክ ነው” ሲሉ ደም የሚያሞቅ ንግግር ያቀረቡት ኢንጅነር ስለሺን የህዳሴው ግድብ ሽያጭ ተዋዋይ አድርገው ለማቅረብ የሞከሩ እንዳሉት ሳይሆን የመጀመሪያው ውይይት በበጎ መልኩ መጠናቀቁ ነው የተገለጸው።

See also  "... በብረት ድስት አንመስለም"

ኢንጂነር ስላሺ ሃላፊነት ከወሰዱ በሁዋላ የህዳሴው ግድብ በሌብነት፣ በዕውቀት ማነስ፣ በግንባታ መጓተትና ቴክኒክ ችግር የተነሳ በችግር የተተበተበ ፕሮጀክት እንደሆነ ጠቅሰው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስጠንተው የወሰዱት የማሻሻያ እርምጃ “ለግድቡ ነብስ አድን” እንደሆነ ምስክርነት መስጠታቸውም ይታወሳል። ሜቲክ የዘረፈው ሃብትና ኢትዮጵያን ያሸከማት ዕዳም በወቅቱ ከተሰራው የግንባታ ስህተት ጋር ተዳምሮ መቅረቡ አይዘነጋም።

ለሁለት ቀናት ሲካሔድ የቆየው የሕዳሴ ግድብን የመጀመሪያ ሙሌትና ውኃ አለቃቀቅ የተመለከተው የመጀመሪያ ዙር ውይይት መጠናቀቁን ያመለከቱት ኢንጂነር ስለሽ፣ እሳቸው የሚመሩት የልዑካን ቡድኑ ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት በሚደረስበት ሁኔታ ሐሳብ እንደተቀያየረ አመልክተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የመጀመሪያ ሙሌትና ውኃ አለቃቀቅን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ ልዑካን መካከል ለሁለት ቀናት የተደረገው የመጀመሪያው ዙር የሦስትዮሽ ድርድር መካሄዱን ይፋ አድርጓል። ሦስቱ አገራት የሦስትዮሽ ድርድሩን በመስከረም 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለመቀጠል መስማማታቸውንም ገልጿል። ኢትዮጵያ በፍትሐዊ እና ምክንያታዊ መርሕ መሠረት የራሷን ድርሻ እና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ድርድሩ በስምምነት እንዲቋጭ ጥረቷን እንደምትቀጥልም አመልክቷል።

ዳግም በተጀመረው የሕዳሴ ግድብ ድርድር ላይ እየተከፋለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወገን ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥቅም በሚሰጥ፣ ውኃውን በቀጣይ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀምን በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲሁም በቀጣናው ትብብር እንዲጎለብት እየሠራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ልዑክ መሪ የሆኑት አምባሳደር ስለሺ በቀለ ማስታወቃቸውን የመንግስት ሚዲያዎች አመልክተዋል።

አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ደግሞ በኢትዮጵያ፤ ግብጽ እና ሱዳን መካከል ሲደረግ የነበረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሁለት ቀናት የሦስትዮሽ የመጀመሪያ ሙሌት (ግድቡ በጥቂት ዓመታት ሙሉ ደረጃ እስኪደርስ) እና ውኃ አለቃቀቅ ድርድር መጠናቀቁን አመልክተዋል። ዝርዝሩን ባያቀርቡም በበርካታ የስምምነት አንቀጾች ላይ ከስምምነት ለመድረስ ውይይቱ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

ግብጽ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ከሰላማዊ ውይይትና ድርድር ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ መከተል የማትችልበት ደረጃ ላይ መድረሷን፣ ግድቡ አሁን ላይ የፖለቲካ ሃይል የሆነበት ደረጃ ላይ መድረሱን የግብጽ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ አመልክተዋል። የህዳሴውን ግድብ ለማስተጓጎል ከሚዲያ ጀምሮ መሳሪያ በማጓጓዝ ትህነግን በገሃድ ሌሎች ታጣቂዎችን በሱዳን በኩል ስትደግፍ የቆየችው ግብጽ አካሄዷን ለመቀየር መስማማቷም እየተሰማ ነው።

See also  በማይጠብሪና ዓድዋ የትህነግ ሰራዊት ማሰልጠኛ ማደራጃና ትጥቅ አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል ላይ አየር ኃይል እርምጃ ወሰደ

” ግብጽ ሩጫዋ ሁሉ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ሳትተራመስ ግድቡን ህዝብ ከዳር እስከዳር ገንዘብን ተባብሮ ወደ ፍጻሜው እያመራው ነው” የሚሉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ የህዳሴው ግድብ ዛሬ ላይ የድርድር አቅሙን አሳድጎ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅም በመሆኑ ግብጽ ሲጀመር እንደነበራት አይነት አቋም መያዝ አትችልም። ይልቁኑ ስጋቷ ሌሎች ግድቦች እንዳይሰሩ እንደሆነ ያመለከቱት ባለሙያዎች “ግድቡ ሊሸጥ ነው” ለሚሉ “ተነቅሎ ነው የሚሸጠው? እንዴት ነው የሚሸጠው? ስንት ብር ነው ዋጋው? ከተሸጠ በሁዋላ የግድቡ ውሃ ተለቆ ባዶ እንዲሆን ነው? ” ሲሉ ይጠይቁና “ይህ የአመለካከት ውርጋጥነት ነው” ሲሉ ሃዘናቸውን ይገልጻሉ።

እነዚህ ወገኖች ግብጽ የድርቅ ወቅት ከመጣ ኢትዮጵያ የነሱ ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ውሃ እንዲለቀላቸው ዋስትና እንደሚፈልጉ ጥርጥር የሌለው ጉዳይ መሆኑንን አመልክተዋል። አክለውም ይህን ጉዳይ ማንም ስለ ጉዳዩ እውቂያ የሌለው ውርጋጥ ሳይሆን ኢንጂነር የሚመሩት የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ያውቁታል።

ግብጽ ወደዚህ ድርድር ከማምራቷ በፊት ፕሬዚዳንት አልሲሲ ከኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በነበራቸው ንግግር ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር ተሰምቷል። እሳቸውም ይህንኑ ጥያቄ በመቀበላቸው ድርድሩ መጀመሩን ስለጉዳዩ የሚያውቁ አስታውቀዋል።

ኢንጂነር ስለሺ ከዚህ ቀደም “ኢትዮጵያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሚጎዳ ማናቸውም ዓይነት ውል አይፈጸምም” ማለታቸው ይታወሳል። የህዳሴው ግድብ ከኤሌክትሪክ ሃይል ማምረት በተጨማሪ አሳ ማምረት መጀመሩ፣ በርካታ ደሴቶች ያሉት የቱሪስት መዳረሻ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል።


Leave a Reply