Site icon ETHIO12.COM

እየተባባሰ በመጣው አለመረጋጋት ተስፋ የቆረጡ ደቡብ አፍሪካዊያን ንብረታቸውን ጥለው እየለቀቁ መሆኑ ተገለጸ

የቀድሞው ደቡብ አፍርካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ መታሰርን ተከትሎ በተከሰተው ብጥብጥና ዘረፋ መባባስ ተስፋ የቆረጡ ደቡብ አፍርካዊያን ንብረታቸውን ጥለው አከባቢያቸውን እየለቀቁ መሆኑን አልጃዝራ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በተኩስና በቤንዚን ቦንብ ታጅቦ በመላ ኩዋሉ ናታል አውራጃ መስተጋባቱን አልጀዚራ በዘጋባው አስነብቧል።

ደቡብ አፍሪካ-በጆሃንስ በርግ ከተማ የግድግዳ ጌጦችና በቀለማት ያሸበረቁ የፓርቲ አቅርቦቶችን የሚሸከሙ መደርደሪያዎች ተሰባብሮ ከባዶ ሣጥኖችን ጋር በታንዲ ጆንሰን ሱቅ ይታያሉ። ንብረቱ የተሰባበረበት የሱቅ ባለቤት ጆንሰን “የዲፕክሎፍ ማህበረሰብ በጥልቅ ጎድቶኛል፤ በጣም ተሰብሬያለሁ” ይህንን ቢዝነስ ለመገንባት 12 ዓመታት ፈጅቶብኛል በማለት ተናግሯል።

እንደ አልጃዚራ ዘገባ የተቃውሞ ሰልፎቹ ተስፋፍቶ ወደ ዘረፋ ተለውጠው በሁለት የደቡብ አፍሪካ ትልቁ የኢኮኖሚ ማዕከላት-ደርባንና ጆሃንስበርግ አመፅና አውዳሚ ክስተት እንዲከሰት አድርጓል። በተቀሰቀሰው ሁከትና ብጥብጡ ሕፃናት፣ መኮንኖችን ጨምሮ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎችን ለህልፈት ሲዳርግ፤ በድምሩ ከሁለት ሺህ አምስት መቶ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በጆሃንስበርግ አሌክሳንድራ ከተማ ውስጥ ነጋዴው ስቲቭ ሌድዋባ እንደገለጸው አርብ ማለዳ ላይ ሱቁ መዘረፉንና ፣ በምቹ መደብሮች ላይ የደረሰው ውድመት ለማገገም ረጅም ጊዜ ይወሰዳል “ምንም ቃል የለኝም! ሁሉንም ነገር አጣሁ! አሁን አጥቻለሁ›› ሲል ተናግሯል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲረል ራማፎሳ አርብ ምሽት በሰጡት መግለጫ ትርምሱ እና ጥፋቱ ከትላልቅ ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች እስከ ትናንሽ ንግዶች የማይቋረጥ እና የማይመረጡ ድርጊቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሁከትና ብጥብጡ የታቀደ እና የተቀናጀ በመሆኑ የደቡብ አፍሪካ መንግስት “ለስርዓት አልበኝነትና ሁከት” እንደማይፈቅድ ገልፀዋል።

የተቃዋሚ የፓርላማ አባል እና የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን ንቅናቄ ፕሬዚዳንት ቮዮ ዙንጉላ በበኩላቸው “በዝርፊያ ላይ የሚገኙት አብዛኛው ህዝብ ድሆች እና ስራ አጦች እና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ልዩነቶቹ የደከሙ ናቸው” በማለት ገልጸዋል።

ክስተቶቹን ከረጅም ጊዜ በፊት የተገለሉ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ትርጉም ያለው የኢኮ ኖሚ ማሻሻያ ካልተደረገ በቀር በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የዚህ ተፈጥሮ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ህዝባዊ አመፅ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ ዙንጉላ ተናግ ረዋል ።

ጆንሰን ወደፊት ነገሮች እንዴት ወደ ነበሩበት ለመመለስ በሱቆቹ ላይ ብቻ ማተኮር ሳይሆን የማህበረሰብን ግንኙነቶች እንደገና መገንባት እንዳለበት ትገልፃለች። “ድርጊቱ ለዲፕክሎፍ ማህበረሰብ የነበራትን እንክብካቤ ሊያጠፋ የተቃረበ ቢሆንም ከሰው ሁሉ ብዙ ፍቅርና ድጋፍ ስለተቀበለች ይቅር ለማለት ቀላል ሆኖልኛል” ትላለች ጆንሰን።

በሰፊው የተደረገው ድጋፍ እንደገና እንዲያገግም አድርጎታል። ፍቅር ሁሉን ያሸንፋል ከችግሩ የመጡትን ድጋፎች እና ወዳጅነቶች ለዘላለም ይቀጥላሉ። ምንም እንኳን የተሰማኝ የማይረሱ ቢሆንም ዘራፊዎቹን ይቅር ማለት እንዳስቻላት ለአልጀዚራ ተናግራለች ። ሁሉም ከዚህ ቀውስ አንድ ትምህርት እንደሚያገኝ ተስፋ እንዳላት ገልጻለች።

 ገመቹ ከድር

አዲስ ዘመን ሐምሌ  15/2013

Exit mobile version