ለአሸባሪው ህወሀት ቡድን በተለያየ መንገድ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 28 ግለሰቦችና ንብረቶቻቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በሶማሌ ክልል የሚገኙ የጁንታው ተላላኪዎች ለቡድኑ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለፁት የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር መሀመድ አሊ ሐሰን፥ 28 ግለሰቦች፣ አስር የሲኖትራክ መኪና እና ሌሎች ንብረቶቻቸው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ በተደረገ ከፍተኛ ክትትል መያዛቸውን ገልፀዋል።
ግለሰቦቹ በክልሉ ብጥብጥ ለማስነሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውንም ነው ረዳት ኮሚሽነሩ የገለፁት። ለዚህ ተግባር እንዲያብሩ ከዚህ ቀደም የነበረው አመራር አባላትና ደጋፊዎች የሆኑ የክልሉ ተወላጆችን በማስተባበር ሲሰሩ ቆይተዋልም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ።
በተለይ የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ፖሊስ ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ወደ ግዳጅ ማምራቱን ተከትሎ በክልሉ የሚገኙ የጁንታው ተላላኪዊች ይህንን ሀገራዊ ሀላፊነት ሌላ ቅጥያ ስም በመስጠትና በማህበራዊ ሚዲያ ለፕሮፖጋንዳነት በመጠቀም ሂደቱን ለማስተጓጎል ሲጥሩ ነበርም ብለዋል።
የክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ የሀገሪቷን ሉዓላዊነት እና ህገ መንግስት ለመጠበቅ የገባውን ቃለ መሀላ ለመተግበር ዛሬም ሆነ ነገ ዝግጁ ነው ያሉት ረዳት ኮሚሽነሩ፥ ጁንታው ስርዓተ ቀብሩ እስኪፈፀም ድረስም ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በመሆኑም በእንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ እጃቸውን በማስገባት ለጁንታው ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙ ግለሰቦችና በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨትና ንብረቶቻቸውን በመሸሸግ እየተባበሩ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ሲሉ ረዳት ኮሚሽነሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከዚህ በኋላ በእንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ የተገኘ ግለሰብም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ረዳት ኮሚሽነሩ ማስታወቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት እንጂ መከራዋን ለመካፈል አይደለም፤ በተቃራኒው… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን መልካም ነው፣ ወንጀለኛ መኾን ግን ሐጥያት ነው ብለዋል፡፡… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም ትኩረቴ በቀላሉ ይከፋፈል ነበር። ሐኪሜ የብረት ማዕድን አዘዘልኝ። ኪኒኖቹን… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን የትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞን አስተዳዳሪዎች የተባሉ ሁለት… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ የሚከተሉ ስምምነቱ መክሸፉንና መንግስት ውሉን… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት