ETHIO12.COM

ትህነግ በአፋር ግንባር ሕጻናትን መጠቀሙ በመረጃ እየተደገፈ ነው፤ መንግስት የተማረኩትን ለዓለም ዓቀፍ ቀይ መስቀል ያሳያል

ትናንት በአፋር በኩል ትንኮሳ ፈጽሞ ሜይዴይ የሚባለው ሀይሉ የተደመሰሰበት አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን በጦርነቱ ማሳለፉን የሚያረጋግጥ ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው። በጌታቸው ረዳ ቅስቀሳ እየተማገዱ ያሉ ሕጻናትን ያዩ የትግራይ ተወላጆች ቁጣቸውን እያሰሙ ነው።

በትናንትናው እለት በአፋር ክልል አለሌ ሱሉላ በኩል የመጣውና የጁንታው ሜይደይ ተብሎ የሚጠራ ሀይል በሙሉ መደምሰሱ የተለጸ ሲሆን፤ ጁንታው ህጻናትን በጦርነቱ አሰልፎ እንደነበር በቁጥጥር ስር ከዋሉ ህጻናት ምርኮኞች ማረጋገጥ ተችሏል።

በቆቦ በኩል ሲተነኩስ የነበረው የአሻባሪው ሀይል እንደተደመሰሰ፤ ጁንታው ያሰማራቸው በርካታ ህፃናትም መማረካቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ትናንት ምሽት ላይ መዘገቡ ይታወሳል። በዚህ ግንባር ተሰልፈው በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በአፋር ልዩ ሃይል ከተያዙ ህጻናት መካከል የተወሰኑት ህጻናት ምስል ከስር ተያይዞ ቀርቧል።

ጁንታው ህጻናትን ለጦርነት እያሰለፈ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማህበሰብ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን ለውትድርና እየተጠቀመ መሆኑን በመጥቀስ የባይደን አስተዳደር ምን ምላሽ አለው በሚል ጥያቄ የተነሳላቸው የአሜሪካ የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ጥያቄውን ሳይመልሱት ማለፋቸው ይታወሳል።

ዞባ ተምቤን እንዳለው ጌታቸው ረዳ ለፍርድ መቅረብ አለበት። ሲያስረዳም “የትግራይ ህጻናት ለምን ይጨፈጨፋሉ? ተጠያቂው እሱ ነው” ብሏል። ዞባ ይህን ይበል እንጂ ትህነግ ሓጻናትን ለጦርነት ሲያበረታታና ሲያዘገጅ የነበረው አስቀድሞ በመሆኑ ሁሉም የዚህ ወንጀል ተተያቂ መሆን እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተሰሚነት ያላቸው ወገኖች ቀስ እያሉ ተቃውሞ ከሚያሰሙት ጎን እየሆኑ ነው።


Exit mobile version