ETHIO12.COM

ባይበላስ ቢቀር… ከገዳይ ጋር በፍቅር መውደቅ

ጸጋዬ ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ካድሬ ጋር ለጊዜው በውል ባልታወቀ ክፍያ ” በትህነግ አሸናፊነት ኮራሁ” እያለ ሲቀደድ፣ ኢሬቻ ላይ የተጨፈጨፉ ወገኖች፣ በስማሌ ጄል ኦጋዴን፣ በወለጋ የልጇ አስከሬን ላይ ተቀመጣ የተገረፈችው እናት፣ በየጎዳና ለምን ተቃወማቹህ በሚል ሲደፉ የነበሩ ምስኪኖችና የወላጆች ዋይታ፣ በአምቦ የእነ ደረራ ከፈኔ መቀጠፍ፣ … ስንቱን ልዘርዝር የግፉ መዓት አይነ ህሊናዬ ላይ እየተነከባበለ መፈጠሬን እንድጠላ አድርጎኝ። ሞራል አልባው ጸጋዬ ምን ቢከፈለው ይሆን እንዲህ ዘቅጦ በወገኖቻችን ሞትና ደም የሚሸቅጠው? ጠያቂው ዓላማው የታወቀ ነው። እንደ ጸጋዬ ያሉት ግን ሰው ስለመሆናቸው ከመተራጠር ውጭ ምንም ዓይነት ማብራሪያ መስጠት አይቻልም። ሲሞክረም ትርፉ ህመም ነው። “ባይበላ ቢቀርስ” ያልኩት ለዚህ ነው።

ባይበላ ቢቀርስ?

አቶ ፀጋዬ አራርሳ የፕሮፓጋንዳ ማሽን  ከሆነው በትግራዩ ሚዲያ ሀውስ ስታሊን ጋር ውይይቶችን ያካሂዳሉ፡፡ ትህነግ ቅዱስ ቅዱስ፤ እትዮዽያዊያንን እና አሁን በአፀደ ህይወት የሌሉትን ሁሉ የሚጨምር ኩነኔ እና ውረፋ የፕሮገራሙ መለያ ባህሪ ነው፡፡

የውይይታቸው ርዕስ ” የትግራይ ጦርነት እና የኦሮሞ ትግል” ይላል ፡፡ ይቅርታ ዶክተር በሌሊት ቀሰቀስከኩህ ይቅርታ እየተባባሉ ያወራሉ፡፡ ጆሮዬን ጣል አድርጌ መስማት ጀመርኩ የሚሉትን፡፡

Commemorating the 2016 Irreecha Massacre at Bishoftu |
የትህነግ ሃይል በግፍ ከጨፈቸፋቸው ሰላዊ የኦሮሞ ልጆች መካከል በኢሬቻ ይህ ሆኖ ነበር፤ ጸጋዬ አራርሳ ይህን የፈጸሙትን ነው ኦሮሞ ላይ እንዲፈርዱ ድጋሚ የሚጋብዛቸው

የኦሮሞ ልጅ /ቄሮ/ በዚህ ጦርነት ውስጥ በምንም ዓይነት መንገድ  መሳተፍ የለበትም የሚል ነው የውይይታቸው ጭብጥ፡፡ ትኩረቴን ሙሉ በሙሉ ወደ ውይይታቸው አድርጌ መከታተል ጀመርኩ፡፡ ምን እያሉ ነው ሰዎቹ ለመሆኑ የሚል ጥያቄ ወዲያውኑ ወደ አእምሮዬ መጣ፡፡ 

የእስር ቤቶች ቋንቋ ኦሮምኛ ሆኗል የተባለበት፣ የነከፍያለው እግር ከአንድም ሦስት ጊዜ የተቆረጠው ህውሃት፣ የኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እሴትና ባህሉ የሆነው እሬቻ በዓል ላይ ያሁሉ ወጣት፣ አዛውንት፣ እናቶች እና ህፃናት ሳይቀር በአረመኔው አጋዚ ህይወታቸው ተቀጠፈ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በህውሃት ላይ ጥያቄ የለውም የሚል እንድምታ ያለው ውይይት ማድመጥ ዛሬም ለዚህ ህዝብ የአብራኩ ክፋይ በሆኑ ቀለብተኞች አማካኝነት ምን እየተደገሰለት  ይሆን ?

“በትህነግ ማሸነፍ ኮርቻለሁ” ጸጋዬ አራርሳ

በስታሊንና በአቶ ፀጋዬ አራርሳ መካከል የሚደረገው ውይይት ቃል በቃል የተለዋወጡዋቸውን ቃላት ለናንተ ለአንባቢያን ማካፈል ወደድኩ፡፡ አቶ ፀጋዬ አራርሳ እንዲህ አሉ  “ የኦሮሞ ህዝብ እኔን ባገኘኝ አጋጣሚ ሁሉ አንድ ጥያቄ ይጠይቀኛል፣ እነዚህ ሰዎች አዲስ አበባ ከገቡ ደግመው እንደ በፊቱ ሊያደርጉን ነው፤ እያሉ በስጋት ውስጥ ናቸው ብዙ የኦሮሞ ሰዎች ፡፡

ነገር ግን ይሄ ሃሳባቸው ከመነሻው ጀምሮ ስህተት አለበት፡፡ የትግራይ መንግስት ዕድል ነበረው እኮ፤ አራት ኪሎ ለመግባት፣ ካለው መንግስት ጋር ለመደራደርና አብሮ ለመሥራት ፍላጎት ካለው ይችል ነበር፡፡

ምክንያቱም ተወዳድሮ ሊያገለግለው የሚፈልገው ትልቅ ህዝብ አለው፤ እንደገና መልሶ የሚያቋቁመው ሀገር አለው፤ እንደገና ከሞት አፋፍ የሚታገደው ሕዝብ አለው፤ የሚገነባው ኢኮኖሚ አለው፤ እንደገና የሚያስተዳድረው ማህበረሰብ አለው፣ ይህን ለማድርግ አይደለም ሌላ ሕዝብ ለማስተዳደር  ሌላ ኃላፊነት ተጨምሮበት በቀላሉ የሚሰራ አይደለም፡፡ ክልሉ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ነው የሚፈልገው ህውሃት፡፡

አዲስ አበባ ይምለሳሉ የሚለው ተገቢነት ያለው ስጋት አይደለም ይላል፡፡ በፌደራል መንግስት ውስጥ ትላልቅ ስልጣን ነበሯቸው፡፡ ስልጣን አንፈልግም ብለው ነው ሁሉንም ጥለው ወደ ትግራይ የሄዱት፡፡

ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ዐፈጉባዔነት ስልጣን ጀምሮ፡፡ ” ዶክተሩ ከዚህ በላይ ያለውን ውይይት ሲናገሩ በሙሉ እርገጠነኛነት እና በማይደነቃቀፍ አንደበት ነው፡፡ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ዘረኝነት ውስጥ እና ከህውሃት የሚሰጠውን ፍርፋሪ በመቃረም ህውሃት አልሞተም፣ ከፈለገ አዲስ አበባ መከተም ይችል ነበር ይለናል በዚህ ውይይታቸው ላይ፡፡

አቶ ፀጋዬ   አሁንም ቀጥለዋል ፡፡ ከውይይታቸው ውስጥ  በተለየ ሁኔታ እኚህ ሰውዬ ጤነኛ ናቸው እንዴ ? የሚል ሃሳብ ውስጥ ከተቱኝ፡፡ ወደ ሚለውን ሃሳብ ተሸጋገሩ፡፡አቶ ፀጋዬ በሰሜን ዕዝ ላይ የደሰውን ይግፍ ግፍ ራሳቸው ህውሃቶች ያላስተባበሉትን ሃቅ ለማስተባበል ደከሙ፡፡

 “ሁሌ ሲነሳ የሚገርመኝ  ህውሃት የሰሜን ዕዝን ደበደቡ ገደሉ የሚባለው ነገር ነው፡፡ ይላሉ አቶ ፀጋዬ፡፡ ትግራይ ውስጥ ነው እንጂ ያደረጉት አዲስ አበባ ውስጥ አይደለም እኮ ይህንን ያደረጉት፣ የሰሜን ዕዝን እንዳልመቱ ደግሞ እኛም የትግራይም ህዝብ ያውቀዋል፡፡ 

“ የሰሜን እዝ ከዛሬ 8 ወራት በፊት በተኛበት በግፍ ሲታረድ፣ ከክልሉ ለቆ ሊወጣ ሲል ቄስ፣ ህፃንና አዛውንትና እናቶችን በማሳለፍ ተንበርክከው  እንዳይወጡ ካደረጉ በኋላ ያንን አሰቃቂና የመላ ኢትዮዽያዊያንን ልብ የሚያደማ ሰቅጣጭ ድርጊትን አቅልለው እና ሸፍጠው አቀረቡት፡፡

የአቶ ፀጋዬና የስታሊን በፈግታ የታጀበው ውይይታቸው አላበቃም፡፡

“ የትግራይ መንግስትና ህዝብ የሚቃጣባቸውን ጦርነት የመመከት እንጂ መሬት የመውረር አይደለም፣ ዓማቸው፡፡ የትግራይ መንግስት ጦርነት የህውሃት ሊህቃን ስልጣን ስላጣን ብለው ኢትዮዽያዊያን ላይ የጀመሩት ጦርነት አይደለም አሉ፡፡

ይህ እጅ እግር የሌለው ቆሞ የሚሄድ እብለት አቶ ፀጋዬ በህውሃት / ወያኔ ባለፉት 28 ዓመታት የኦሮሞ ልጅ የከፈለውን መከራ በመሸምጠጥ ሠራዊቱ ውስጥ አብሮ የታረደውን የኦሮሚያ ወታደር ልጅ በመካድ በተለይ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የኦሮሞ ወጣት/ ቄሮ ከሌሎች ኢትዮዽያዊያን ጋር ያደረገውን ትግል አፈር ከድሜ በማስገባት  ህውሃት ስልጣን አልፈልግም ብሎ ነው ጥሎ የሄደው ይሉናል፡፡

በተቃራኒው የህውሃት አፈ ቀላጤ የነበሩት አቶ ሴኮ ቱሬ በትግራይ ቴሌቪዥን ቀርበው በወኔና ሳቅ በተቀላቀለው የደስታ ስሜት ውስጥ ሰሜን ዕዝ ላይ ያደረጉትን የጭካኔ ተግባር እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡

“ የሰሜን ዕዝን ከተባበሩት እጃችንን እናነሳም ካሉት የዕዙ አባላት ካሉት ጋር በመተባበር እና ለተባበሩ ፈቃደኞች የሆኑ ተልዕኮዋቸውን እንዳይወጡ ዲስታብላይዝ ወይም ደግሞ ዲሞብላይዝ በማድረግ የተደረገ እርምጃ ነው፡፡ በተወሰደው በ45 ደቂቃ ውስጥ ዕዝን በሙሉ ለመቆጣጠር የተቻለበት ነው፡፡

ፈጣን የመብረቃዊ የሚባል ጥቃት በሚደርስ ወራሪው  ኃይል  በማዛባት በማተማረስ፣ ራሳቸውን ከጥቃት የሚያድኑበት መብረቃዊ እርምጃ መውሰድ ነበረበት ያ መብረቃዊ እርምጃ ባይወስዱ ኖሮ ይህን ጊዜ ቁጭ ብለን የምናወራበት ክልል አይሆንም ነበር፡፡ ብለው ነበር  ሰሜን ዕዝ ላይ የሀገር ክህደት ተግባር ከፈፀሙ አቶ ሴኮ ቱሬ፡፡

አቶ ፀጋዬ አራርሳ፣ እና ቀደም ብሎ ከህውሃት ጉያ ጡት እየጠቡ ያደጉ የህውሃት የጡት ልጆች በመላው ኦሮሚያ በተለይም ለዚህ ፁሁፍ ሲባል ትኩረት የሚሰጠው የኦሮሚያ ልጆች ህውሀትን በመገርሰሱ በኩል አያገባህም፡፡ የዐብይን መንግስት ገርስሰህ የራስህን መንገስት መስርት ጥሪና ቄሮ በዚህ ጦርነት ምን አገባው የሚባልበት ሁኔታ አሳዛኝ እና ከእውነታው ይልቅ ዓላማው ሌላ በመሆኑ ነው::

ቄሮ ላይና የኦሮሞ ህዝብ ላይ የደረሰው የ28 ዓመታት መራር ሰቆቃን የቃደ ነው፡፡ ቄሮን ምን አገባው በዚህ የህልውና ጦርነት የሚሉት አቶ ፀጋዬ እነ ከፍያለውን፣ የዳባ ሀገሬን ስቃይ እና የመከራ ቁስል ላይ ጨው መነስነስ ነው፡፡

በ2011 ዓ.ም.  በሁሉም የመንግስት ቴሌቪዥኖች አንድ ዘጋቢ ፊልመ ተሰራጨ፡፡  ርዕሱ የፍትህ ሰቆቃ የሚል ነበር፡፡ በዚህ ዘጋቢ ፊልም ላይ በብሔራቸው እና በሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት የተነሳ ብቻ አይደለም፡፡  ወንድምህን እህትህን፣ አጎትህን አግኝተሃል ወይም የተደበቀበትን አውጣ በሚል የበደል ክምር ደርሶባቸዋል፡፡

የዓለም ፍፃሜ ፍርድ በገሀነም የተወሰነበትን የሀጢያት ፍርደኛ ውሳኔ የሚመስል ግፍ በህይወትና በሞት መካከል በወያኔ እስር ቤት ውስጥ አሳልፈዋል፡፡

በዘጋቢው ፊልም ውስጥ ከቀረቡት ሁለት የኦሮሞ ወጣቶችን ታሪክ እንጥቀስ፡፡  ዳባ ሀገሬ ይባላል፡፡

በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነበር፡፡  በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ፕሬዘዳንት ነበር በወቅቱ፡፡

በለገደንቢ የወርቅ ማውጫ በክልሉ ነዋሪዎች ላይ እያደረሰ ያለው የጤና እና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ የኦሮሞ ልጆችን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሃሳባቸው ደጋፊዎችን ይዘው በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የሰላማዊ ሰልፍ  ተቃውሞዋቸውን አሰሙ፡፡ በተቃውሞው ሰባ ሰዎች በህውሃት መራሹ የፀጥታ ኃይል ህይወቱን አጥቷል፡፡

ዳባ እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ለአንዲትም ቀን ብርሃንን ተመልክቶ እንደማያውቅ እየገለፀ ለመናገር በሚከብድ ሁኔታ በደረሰበት ግርፋትና እስር ምክንያት በተለይም እግሩ በድብድባ ብዛ በመጎዳቱ በህክምና የገድ ቆሞ ለመሄድ ብረት ለማስገባት ሲሉ በህክምና ስም የደረሰበት ስቃይ ማየቱ ሰው ለሆነ ሰው ከባድ ነው፡፡

ሌላኛው የህውሃት ግፍ ሰለባ አብደታ ታደሰ ይባላል፡፡ ሳይቤሪያ በሚባለው ማዕከላዊ እስር ቤት  ስውር እና ቀዝቃዛ የሰቆቃ ቤት  ያሳለፈው መከራ እውን በነአቶ ፀጋዬ እና በስታሊን አንደበት እንዲህ ዋጋ አጥቶ ፤ ምንም አይደለም የሚል ትርጉም ያሰጣል፡፡

አብደታ አንድ ማለዳ ላይ በህውሀት የፀጥታ ኃይሎች ከቤቱ ይዘውት በመኪና ከጫኑት በኋላ ዓይኑን በጨርቅ ሸፍነው እና የፍጥኝ አስረው እየደበደቡ  እያሰቃዩት ወደ ሳይቤሪያ እስር ቤት አስገቡት፡፡

ደብዳቤዎች እየተፈራረቁ “አንተ ብሎ የኦሮሞ መብት ተሟጋች እያሉ ያደረሱበትን በደል” ሲገልፅ ከለውጡ በኋላ በማዕከላዊ እስር ቤት ሳይቤሪያ ክፍል ውስጥ በአካል ተገኝቶ በዛ በስቃይ ጊዜ እርሱና ግድግዳው ብቻ የሚነጋገሩትን ምስጢር”  ይህም ያልፋል የሚለው የእጅ ፁሁፉን“ በእማኝነት በማሳየት የህውሃት ሰይጣናዊ ድርጊትን ቀርቧል፡፡

አብደታ ላይ የደረሰው የበደል ጅራፍ ይህ ብቻ አይደለም፡፡  ዓይኑን በመሸፈን እጅና እግሩ ላይ ማሽን በማጥበቅና በማላላት ያደረሱበትን ሰቆቃ መግለፅ አቅቶት እንባ ሲተናነቀው በዚህ ዘጋቪ ላይ ለመመልከት ያቅታል፡፡

ሌላኛው የህውሃት በደል ገፈት ቀማሽ የሆነው ወጣት ከፍያለው ታሪክ ነው፡፡ ኦሮሞ በመሆኑ የደረሰበትን መከራ መጥቀስ የህውሃት  የጭካኔ ጥግ የት ድረስ እንደነበረ ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡  ኦሮሞ በመሆኑ እና የነበረውን መንግስት ለምን ተቃወማለህ በሚል አረመኔያዊ የሆነ ጭካኔ የተነሳ ነው የበደል እጃቸውን ያነሱበት፡፡

ከፍያለው በህውሃት ታጣቂ የተያዘበትን ሁኔታ ሲፈልፅ አንድ ዕልት ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ኃይሎች  መንገድ እየሄደ እያለ የማያውቃቸው ሰዎች ወደ እርሱ በመምጣት እርሱን በቀላሉ መያዝ እየቻሉ እዛው መንገድ ዳር ላይ በጥይት እግሩ ላይ  መቱት ፡፡

አብረውት ሁለት ጓደኞቹ ነበሩ ፡፡ ሁለቱም በጨካኙ የህውሃት አባላት ተመቱ፡፡ ሁሉንም ቁስለኞች አንስተው ወደ ፖሊስ ሆስፒታል ወሰዷቸው፡፡ አንደኛው ወጣት ወዲያውኑ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱን አጣ፡፡

ከፍያለው ቆስሎ በተኛበት የፖሊስ ሆስፒታል ውስጥ የእርሱም ሆነ የቤተሰቦቹ ፈቃድ ሳይጠየቅ እግሩን ተቆረጠ፡፡ የቀዶ ጥገና ክፍል ከገባ በኃላ በሀኪሙ በኩል አግሩ ሊቆርጥ እንደሆነ ሲነገረው እምቢ ቢልም  እግሩን ያለእርሱ ፈቃድ ቆረጡት፡፡

ከፍያለው በዚህ ሁኔታ አንድ ጊዜ  ብቻ ሳይሆን ለሦስት ጊዜ ያህል በጭካኔ ያለበቂ ሁኔታ እና የህክምና ስነምግባር ውጪ እግሩ ተቆረጠ፡፡ ከፍያለው በህውሃት ያሳለፈውን መከራና ሰቆቃን ለመመልከት እና ለመስማት ጆሮም ዓይንም ፈቃደኛ ለመሆን ይቸገራሉ፡፡

ህውሃት ዛሬ ጠላቴ የዐብይ መንግስትና የአማራ መንግስትና ህዝብ ይበል እንጂ ብሔር ብሔረሰቦች አይደላችሁም ሲል በሌሎች ብሔረሰቦች ዘንድ በቅድስናው የሚወደስ ተመልሰህ መተህ አንተ ካልመራሀን የሚል እንድምታ ያለው መልዕክት ይዘው ሲዳክሩ ያታያሉ፡፡

ዛሬም ህውሃትና ጭፍሮቹ በከፋፍለህ ግዛው ትርክታቸው አንገቱ ጨርሶ እንዳልተቆረጠ ዶሮ እየተንፈራገጡ አለሁላችሁ ወይም ድረሱልኝ የሚል ያለየለት ጥሪውን በከፍተኛ የማወናበድ ዘመቻ እነ አቶ ፀጋዬን በመሳሰሉ ሆድ አደሮችን ይዞ እየተንደፋደፈ ይገኛል፡፡

ህውሃት ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ያዞት የተነሳውን አንዱን ብሔር ከሌላኛው ብሄር ጋር የማናከስና የማባላት ስልት ዛሬም መቀሌ ከትሞ ከነበረበት ጫካ በመውጣት በሁሉም አቅጣጫ ኢትዮዽያዊያንን ሰላም በመንሳት ምንም የማያውቁ የትግራይ ልጆቹንም ወደ ጦርነት እየማገደ ከእኔ በላይ የሚል ሽለላና ፉከራው ቀጥሏል፡፡

በብሔሮች ጀርባ ታዝዬ በድጋሚ ወደ ሥልጣን እመለሳለሁ አለበለዛ ደግሞ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባትን ሀገር አፈርሳለሁ የዕለት ፀሎቱ ከሆነ ሰነበተ፡፡

Exit mobile version