Site icon ETHIO12.COM

ለምን ኃያላን መንግስታት አብይ ላይ ተነሱባቸው?

በኤርትራና በኢትዮጵያ የተፈጸመው የዕርቅ ሂደትን ሰላም መምጣቱ ያላስደሰታቸው አሜሪካ እና የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች (አውሮፓ ሕብረት) በህዋሃት በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እየፈጠሩ መሆኑን እያየነው ነው። ቢሆንላቸው ጠ/ሚሩን ለማስወገድ ወይም አደጋ ላይ ለመጣል የሚችሉትን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ እናውቃለን። አፍሪካ ውስጥ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እና አንድነት እንዲጠናከር አይፈለግም። በአፍሪካ ምድር የቅኝ አገዛዝ ዘመን ካበቃ በኋላ ሃያ ዘጠኝ ሰላም ወዳድና ለሃገራቸው ህዝብ የቆሙ መሪዎች በአሜሪካና ሌሎች ውጪ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ተገድለዋል።

ልጅ ግሩም ( ፒኤችዲ)

እርቅ፣ ሰላም እና ትብብር የሚል ሀሳብ ስለፈለገ ብቻ ነው። ግብፅን እንደ ምሳሌ እንመልከት፡-ግብፃውያን ከእስራኤል ጋር አራት ጊዜ ታላላቅ ጦርነቶችን አካሂደዋል፡፡ እስከ መጀመሪያው የግብፅ አብዮት መሪ ጋማል አብድል ናስር አስተዳደር ድረስ ከእስራኤል ጋር ሦስት ጦርነቶች ተካሂደዋል፡፡

ፕሬዝዳንት አንዋር ሳዳትንም አራተኛውን ጦርነት ተሸንፈው በኋላ ግን ፊታቸውን ወደ ሰላም አዞሩ፡፡ የዛሬ 40 ዓመት ገደማ በዘመኑ ብዙዎችን ያስገረመ ያስደነቀም ያልተጠበቀም ነገር አደረጉ፡፡ የሰላም እና እርቅ ንግግር ለማድረግ ወደ እስራኤል አቀኑ፡፡

ከዘመኑ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሜኒያሂም ቤጊን ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው በመነጋገር የመጀመሪያው አረብ ሆኑ። በጊዜው ለፍልስጤማውያን ተቆርቋሪዎች ነን ይሉ የነበሩ የአረብ አገሮችና ሌሎች ሳዳትን በከሃዲነት አብጠለጠሏቸው፡፡

ሰላምን መምረጣቸው የተቀረውን ዓለም አድናቆት አተረፉ፣ ተወደሱ፣ ተሞገሱበት፡፡ እስራኤል በስድስቱ ቀን ጦርነት ከግብፅ የነጠቀችውንና በኋላም ያስፋፋችውን የሲናይ ግዛት ለግብፅ መለሰች። ፕሬዝዳንት ሳዳት የኖቤል የሰላም ሽልማት (1978) አሸናፊ ሆኑ፡፡ ከሶስት በኋላ ዓመታት በኋላ (October 6, 1981) በካይሮ በአንድ የሠልፍ ስነ-ስርዓት ላይ በህዝብ ፊት መድረክ ላይ ተቀምጠው እያሉ ተተኩሶባቸው ተገደሉ። በተመሳሳይ ስሌት ሰኔ 16 ቀን በመስቀል አደባባይ የተከሰተውን እናስታውሳለን።

በኤርትራና በኢትዮጵያ የተፈጸመው የዕርቅ ሂደትን ሰላም መምጣቱ ያላስደሰታቸው አሜሪካ እና የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች (አውሮፓ ሕብረት) በህዋሃት በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እየፈጠሩ መሆኑን እያየነው ነው። ቢሆንላቸው ጠ/ሚሩን ለማስወገድ ወይም አደጋ ላይ ለመጣል የሚችሉትን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ እናውቃለን። አፍሪካ ውስጥ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እና አንድነት እንዲጠናከር አይፈለግም። በአፍሪካ ምድር የቅኝ አገዛዝ ዘመን ካበቃ በኋላ ሃያ ዘጠኝ ሰላም ወዳድና ለሃገራቸው ህዝብ የቆሙ መሪዎች በአሜሪካና ሌሎች ውጪ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ተገድለዋል።

Exit mobile version