Site icon ETHIO12.COM

በትግራይ ያሉ የዪኒቨርሲ ተማሪዎች ወደ ሰመራ እየገቡ ነው

በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች አፋር ክልል ሰመራ ከተማ መግባት መጀመራቸው አል ዐይን አማርኛ ያነጋገራቸው የሰመራ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡የተማሪዎች ወላጆች ከሰሞኑ ልጆቻቸው ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመለሱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል መውጣት ከጀመረ እና የተናጠል ተኩስ አቁም ከታወጀ በኋላ ትግራይ ክልል ባሉ ዮኒቨርሲቲዎች ልጆች ያሏቸውን ወላጆች ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ በትግራይ ክልል ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል 325 የሚሆኑት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ አቀባበል እንደተደረገላቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሰመራ ከተማ የሥራ ኃላፊ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ሰመራ የገቡት ተማሪዎች ወደ የቤተሰቦቻቸው እየተሸኙ መሆኑ የስራ ኃለፊው ተናግረዋል፡፡በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ልጆች ያሏቸው ወላጆች፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ልጆቻቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻችላቸው ከሰሞኑ በሰልፍ ጠይቀው ነበር፡፡ትግራይ ክልል ባለው ግጭት ሳቢያ ስጋት ያደረባቸው ወላጆች ከተመድ በተጨማሪ፤ መንግስት በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ባሉ በተማሪዎቹ ዙሪያ እልባት እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ነበር፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ት/ምሚኒስቴር በወቅቱ “ከየዩኒቨርስቲዎቹ አመራሮች እና ከዓለም አቀፍ ተራድኦ ተቋማት ጋር በመሆን ጉዳዩን እየሰራበት ይገኛል፡፡ በተደረገው ጥረትም የዩኒቨርቲዎችን አመራር ለማግኘት የተቻለ ሲሆን ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ያሉም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል” ሲል ለወላጆች ጥያቄ መልስ መስጠቱ ይታወሳል፡፡Via #alainamharic

Exit mobile version