ETHIO12.COM

በአዲስ አበባ ኤርትራዊያን ስደተኞች ትግራይ ስቃይ ላይ ላሉ “ለወገኖቻችን ዓለም ይድረስላቸው” ሲሉ ጥሪ አሰሙ

” የሰማ ዕረፍት” ሲሉ የትህነግ ሃይል የገደላቸውን ወገኖቻቸውን ምስል ይዘዋል። ህጻናት የተፈናቀሉ ስደተኞች ቢሆኑም የዓለሙ የስደተኞች ድርጅት አንዳችም ድጋፍ እንዳላደረገላቸው በጽሁፍ ያሳያሉ። ስደተኞች እንጂ ወንጀለኞች አለመሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት እንዲያይላቸው፣ እዲሰማ ደጁ ቆመዋል። የኤርትራ ተፈናቃይ ሰደተኞች።

አንድ ጠይው ሕጻን ማስክ አድርጋ ” እነዛ በትግራይ ካምፕ ያሉ ባስቸኳይ ወደ ሰላማዊ ስፋር ይዛወሩ” ስትል ትጠይቃለች። ከጎኗ ” እኛ ስደተኞች ነን። እኛም እንደ እናንተ ሰዎች ነን” ትላለች። በርካታ ልብ የሚነኩ መፈክሮች የያዙት የኤርትራ ስደተኞች በተባበሩት መንግስታት ቢሮ ደጅ ቆመው ” የህግ ያለ” ሲሉ ላየ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢለኔ ስዩም ” ዓለም ትህነግን ዝም አለው። ለለም፣ ለምን፣ ለምን…?” ሲሉ የጠየቁት ጥያቄ አግባብ መሆኑንን ይረዳል። ግን ለምን የኤርትራ ስደተኞች በዓለሙ የስደተኞች ካምፕ ስር ሆነው ሳለ ይገደላሉ? ይንገላታሉ? ይዘረፋሉ? ይፈናቀላሉ? በሚደርስባቸው ግፍ መጠንስ ስለምን ተቆርቋሪ አጡ? የቢለኔ ስዩም ብቻ ሳይሆን የሁሉም ጥያቄ ነው።

በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች በትግራይ ክልል ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና እንግልት በመቃወም ሠላማዊ ሠልፍ ሲያካሂዱ ያነሱት ጥያቄ ይህንኑ ” ለምን ዝም እንባላለን?” የሚለውን ነው። ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት መስሪያ ቤት ተገኝተው ላሰሙት ጩኸት የተሰጠው ምላሽ ምን እንደሆነ አልታወቀም።

በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የሚደረግ ጥቃት ይቁም’፣ ‘ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድምፃችንን ይስማ’፣ እና ሌሎችንም መፈክሮች በመያዝ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትግራይ ክልል የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ከሚደርስባቸው ግፍና በደል እንዲታደጋቸውም ጥሪ አቅርበዋል።ስደተኞቹ ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ለመንግስታቱ የስደተኞች ድርጅት በደብዳቤና በአካል በመገኘት መልዕክት ብናስተላለፍም ምላሽ አላገኘንም ሲሉ ምሬታቸውን አሰምተዋል።

በትግራይ ክልል በሚገኙ ስደተኞች ላይ ግፍና እንግልቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ፣ ስደተኞች እየተገደሉና በየጫካው በሽሽት ላይ ያሉትም ለከፋ ችግር እየተጋለጡ በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉም ጠይቀዋል።

በሠላማዊ ሠልፉ ላይ አካል ጉዳተኞች፣ ሕፃናትና አዛውንት መሳተፋቸውን ኢዜአ ያተመው ምስል ያስረዳል። አሜሪካ በትናትናው ዕለት የኤርትራ ስደተኞች ጉዳይ እንደሚያሳስባት አምጣ፣ አምጣ ማስታወቋ አይዘነጋም።

Exit mobile version