ETHIO12.COM

ሰለሞን ባረጋ- “ኢትዮጵያ ድል ማስመዝገቧን ትቀጥላለች”አብይ አሕመድ

አትሌት ሰለሞን በለሊትና በማለዳ በትደረጉ አኩሪ የማጣሪያ ወጤቶች ታጅቦ በስተመጨረሻ ባካሄደው የአስር ሺህ ሜትር ውድድር አበራ። ሰለሞን በቶኪዮ የመጀመሪያውን ወርቅ በመውሰድ ልዩ አትሌት ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ደስታቸውን ገልጸዋል።

አፍታ ሳይቆዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ 10ሺሜትር ሩጫ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ እንኳን ደስ አለን።ለቀሩት ተወዳዳሪዎቻችንም መልካም ዕድል እመኛለሁ።ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች በማለፍ ድል ማስመዝገቧን ትቀጥላለች!” ሲሉ ደስታቸውንና በደስታቸው ውስጥ ያለችውን ታላቅ አገር በማሳየት ገልጸዋል።

ሰለሞን ዛሬ አስር ሺህ የውርቅ ሜዳሊያ ለአገሩ፣ ለግሉም ታሪካዊ ድል ሲያስመዘግብ፣ ኡጋንዳ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ አበአንድ ውድድር ሁለት ሜዳሊያ ማግኘቷ ለአገሪቱ ሚድያዎች ትልቅ የደስታ ዜና ሆኗል። ኢትዮጵያ አረንጓዴው ጎርፍ በሚባልበትና ከዛም በሁዋላ እስከ ቅርብ ጊዜ ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትሎ መግባት የተለመደና ሲያልቅ የልጆቻችንን የእርስ በርስ ውድድር ለማየት እንጂ ለውጤቱ ሙሉ እምነት ይዘን ውድድሩን ስንሳተፍ እንደነበርን ይታወሳል።

በ2004 በትምህርት ቤት ሩጫን ጀመረ በኋላም በ2005 ዘመን ዞን እና ክልል በመወከል ተሳትፎ በ2006 ደቡብ ፓሊስ ክለብን ተቀላቀለ። ሰለሞን ያደረጋቸው የውድድሮች ብዛት 65 ሲሆኑ 5000 ሜትርን ብቻ 25 ጊዜ ሮጧል። በአለም አቀፍ ውድድር ሀገሩን ዘጠኝ ጊዜ የወከለ ሲሆን በኦሎፒክ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ አሁን አገሩን ወክሏል። በሄንግሎ የኦሎፒክ ማጣሪያ የሮጠው 26.49.51 ሰአት 8 Jun 2021 ያስመዘገበው ሰአት 1ኛ ሆና የተመረጠበት የግል ፈጣን ሰዓቱ ነው። እንደሆነ ኢትዮ ራነር ግል ታሪኩን ቀንጭቦ ገልጿል።

ውድድሩ ከባድና የተያያዘ ቢሆንም ሰለሞን ከሁለቱ ዩጋንዳ አትሌቶች ልቆ ማሽነፉ ኢትዮጵያዊያንን አስፈንድቋል። ድል ላማዱ የሆነው አትሌታችን በስለሞን አብሪ ድል ተጀምሮ ኢትዮጵያ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ገብታለች።

Selemon Barega of Ethiopia wins the men’s 10,000m title. Photograph: Diego Azubel/EPA

በሴቶች የአምስት ሺህ ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ሰንበሬ ተፈሪና እጅጋየሁ ታዬ ከየምድባቸው ያለ ችግር ለፍጻሜ አልፈዋል።


Exit mobile version