Site icon ETHIO12.COM

በ12 ዓመቱ ታዳጊ ላይ የግብረ-ሶዶም ጥቃት ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ።

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ኢሳያስ ካሳ ገብሩ የተበላው ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀፅ 631/1/ለ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ

ጥቅምት 29/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው “32 ክበብ ጀርባ ”ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የ12 ዓመቱን ታዳጊ በማስገደድ የግብረ-ሶዶም ጥቃት ወንጀል የፈፀመበት በመሆኑ በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል ።

የዐቃቤ ህግን ክስ የተመለከተው የፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ለተከሳሽ ክሱ ተነቦለት የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን ሙሉ በሙሉ ያላመነ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ የሰው እና የሰነድ ማስጃዎቹን አቅርቦ አሰምቷል፡፡ በዚሁም መሰረትም ፍርድ ቤቱ እንዲከላከል የሰጠውን ብይን ተከትሎ ተከሳሹ የዐቃቤ ህግን ማስራጃዎች ማስተባበል ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር የጥፋተኝነት ውሳኔ ሊተላለፍበት ችሏል፡፡

በስተመጨረሻም ግራ ቀኝ ያቀረቡትን የቅጣት አስተያየቶች ከግምት አስገብቶ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ያርማል ሌሎች አጥፊዎችንም ያርማል በማለት በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

Via – ዐቃቤ ህግን

Exit mobile version