የትዳር አጋሩን በዘነዘና መትቶ የገደለው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ

የዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያሥረዳው ተከሳሽ ታምራት ቦጋለ ሸጎ ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 4፡30 እስከ 6፡00 ባሉት ሰዓታት ውስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ጉርድ ሾላ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ “ለምን ለእራት ብር አልሰጠህኝም በሚል የትዳር አጋሩ ከሆነችው ሟች አመነች አብርሃም ጋር በተነሳ ጭቅጭቅ ሟች አመነች አብርሃምን የ4 ዓመት ዕድሜ ያላቸው መንታ ልጆቻቸው ፊት በቡና መውቀጫ ብረት ዘነዘና ጭንቅላትዋንና አንገትዋን ደጋግሞ በመምታት ከገደላት በኋላ ወደ ወላይታ ሰዶ በመሄድ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል፡፡

ዐቃቤ ሕግም ከፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን ተገቢውን ማስረጃ የማሰባሰብ ስራ ካከናወነ በኋላ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ጉዳይ ዓቃቤ ሕግ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 539/1/ሀ ስር በተደነገገው መሰረት በተከሳሽ ላይ የሰው ግድያ ወንጀል ክስ መስርቶ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቅርቧል፡፡

በመቀጠልም ተከሳሹ ዐቃቤ ህግ ባቀረበበት ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ጠይቆት ሙሉ በሙሉ ያላመነ በመሆኑ እንደካደ ተቆጥሮ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ፤ የሰነድ ማስረጃዎቹም እንታዩ ተደርጓል፡፡ በዚሁም መሰረት ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን የተሰጠ ቢሆንም ተከሳሽ መከላከያ ማስረጃ እንደሌለው ለፍ/ቤቱ በመግለፁ ፍ/ቤቱ በቀረበው የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ መሰረት ተከሳሽ በወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ ስር ጥፋተኛ ሲል ፍርድ በመስጠት ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ከዚህ የክስ መዝገብ ላይ መማር ያለብን ጉዳይ በቀላሉ ተነጋግረን ልናልፋቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ስሜታችንን መቆጣጠር ሳንችል ስንቀር እራሳችንን ለእስር ሌሎችንም ለጉዳት መዳረጋችን ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ጸጸቱ ከባድ ነውና ከድርጊት በፊት ማሰቡ ይጠቅማል፡፡

Related posts:

"መስከረም አበራ የአማራ ክልልን ከፌደራል መንግስት ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት እየሰራች ነው" ሲል ፖሊስ ገለፀMay 23, 2022
የጉምሩክ የታክስ ኢንተለጀንስ ባለሙያ ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
ሀሰተኛ ሰነዶችን በመገልገል ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበትMay 20, 2022
ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት መኖር እና የሚያስከትለው ውጤትMay 17, 2022
በዳኝነት ስርአቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነMay 12, 2022
ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘችው የመሬት ልማት መኔጅመንት ባለሙያ ክስ ተመሰረተባትMay 11, 2022
የደህንነት ሰራተኛ ነኝ በማለት ወንጀሎችን ሲፈፅም የነበረው ተከሳሽ በፅኑ እስራትና ገንዘብ ተቀጣMay 11, 2022
ከሳኡዲ ተመላሾች መካከል ወንጀል የፈጸሙ ላይ ምርመራ ሊጀመር ነው- የሰው ንግድ አንዱ ነውMay 9, 2022
በኢድአልፈጥር በዓል የጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረው ፖሊስ ፍርድ ቤት ቀረበMay 4, 2022
የከተማ መሬትን በወረራ ለመያዝ ጥብቅ ደን በጨፈጨፉ 97 ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተApril 26, 2022
የመኪና ሌቦቹ ተፈረደባቸውApril 15, 2022

Leave a Reply