Site icon ETHIO12.COM

«የቁንጥጫ ዲፕሎማሲ» የዲፕሎማሲው መንገድ መቀየር !

ምዕራብውያን የአቢይ አህመድ አስተዳደርን እስከ ቅርብ ጊዜ ታዛዥ መንግስት Yes Sir State አድርገው ቆጥረውታል። የአንዳንድ መንግስታት የበታች ሹማምንት ከዚህም አልፈው የመንግስት ቅየራ regime change ሀሳባቸውን ምንም ግድ ሳይላቸው መጻፍ ሁሉ ጀምረው ነበር። ለዚህ መነሻቸው የፖሊሲ አጥኚዎቻቸው አቢይ አህመድ ኦሮሚያም ፣ አማራም ክልሎች ውስጥ ይኼ ነው የሚባል ህዝባዊ መሰረት የለውም የሚለው ድምዳሜ ነው። ያለፈው ምርጫ ዕጢያቸውን ዱብ ቢያደርገውም የቆየ ትንተናቸውን ባፈርኩ አይመልሰኝ ሊሄዱበት ይሞክራሉ።

የአቢይ አህመድ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የውጭ ጉዳይ አያያዙ ላይ ለውጥ እያመጣ ሄዷል። በሰለጠነ ዲፕሎማሲ መገናኘቱ እንዳለ ሆኖ ጥፊን በጥፊ የመመለስ ፖለቲካ ተጀምሯል። ይህ ሂደት የተጀመረው የቀድሞውን ፉላንዳዊው የአውሮፓ ህብረት ልዑክን ዳግም አልቀበልም በማለት ነው። በእርሳቸው ምትክ የመጡት አዲሷ የህብረቱ ልዑክም ኢትዮጵያ ለመግባት ለቀናት ደጅ ጠንተዋል።

ይህ ብቻ ሳይሆን መንግስት አንዳንድ ግብረሰናይ ነን የሚሉ ድርጅቶች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ የቁንጥጫ ዲፕሎማሲ መጀመሩን ያመላክታል። አዲሱ የ UNOCHA አስተዳዳሪ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተቀራርበን እንሰራለን ፣ አሉታዊ ግንኙነት አንሻም ያሉት መንግስት ድርጅታቸው ላይ ሰይፉን እንደሚያሳርፍ በማያወላዳ ቋንቋ ስለተነገራቸው ነው።

የዲፕሎማሲ ማንገዱ ትልቅ ሚስማር የተመታው ትናንት ወደ ሀገራቸው በተመለሱት ሳማንታ ፓወር ላይ ነው። ብዙዎች ሴትዮዋን አቢይ አላናገራቸውም ይላሉ ነገር ግን ደመቀ መኮንንም የእርሳቸው ምክትል ሬድዋን ሁሴንም ሊያናግሯቸው አልፈቀዱም። ሳማንታ ገና ከአሜሪካ እንደተነሱ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ቅጣት ይጠብቃታል የሚል ዛቻ አስነግረው ነው የመጡት። ዝለል ስንለው የት ድረስ ? የሚል ታዛዥ መንግስት አዲስአበባ ላይ አለ ብለው አምነው ነበር። ያ የሆነላቸው አይመስልም። ከሁሉም ከሁሉም ሴትዮዋ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ በቅጡ ተረድተዋል። ለዚህም ነው ” ኢትዮጵያውያን ለአንድ ወገን የምናደላ ይመስላቸዋል ” ሲሉ መግለጫቸው ላይ ተናግረው ህዝብን ለማረጋጋት የሞከሩት።

መንግስት እየወሰደ ያለው ደፋር ዲፕሎማሲ assertive diplomacy እሰየው የሚባል ነው። ነገር ግን ከውጭ መንግስታት ጋር ያለን ግንኙነት መሬት ላይ ባለው እውነት እንደሚወሰን መዘንጋት አያሻም። በቅድሚያ የህወሃትን ግስጋሴ ገትቶ ሰዎቹን ከዕብሪታቸው ማውጣት ይገባል። ህዝብ እያሳየ ያለውን አንድነት ወደ ተጫባጭ ተግባር መቀየር ወደፊት የሚመጡ ጫናዎችን በጋራ ለመቋቋም መስራትም ግድ ይላል።

Via – Samson Michailovich

Exit mobile version