የሲሚንቶ እጥረት በዓመት ጊዜ ውስጥ ይፈታል

መንግስት የሲሚንቶ እጥረትን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመፍታት የሚያስችል ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

መንግስት የሲሚንቶ እጥረትን በዘላቂነት ለመፍታት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስራ እያከናወነ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወከዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል፡፡

የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትን ለመፍታት መንግስት የቀየሰው ዘዴ ካለ ተብለው ከምክር ቤት አባላት ለተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ ፣የሲሚንቶ እጥረት ከፍተኛ መሆኑን በማስረገጥ ይህም በግንባታ ኢንዱስትሪው ላይ ጫና መፍጠሩን አስረድተዋል፡፡እጥረቱ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ጎልቶ የሚታይ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

እንደ ህዳሴው ግድብ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የሚወስዱት ከፍተኛ መጠን ያለው ሲሚንቶ ለእጥረቱ ዋናኛ ከሚሆኑት መንስኤዎች እንደሚጠቀሱም ጠቅላይ ሚንስት ዐቢ

በሀገሪቱ የመንገድ ግንባታ መዘግየት ችግርን ለመፍታት በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ነው-

በሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እየተጓተተ የመጣውን የመንገድ ግንባታ ለመፍታት በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ክልሎችም የመንገድ ፕሮጀክቶችን ክትትል የሚያደርጉት በጀት እስኪያዝ ድርስ እንጂ የመንገዶች ግንባታ ሂደትን በመከታተል ረገድ ሰፊ ክፍተት መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል፡፡ ለመንገዶች ግንባታ በጀት ከተያዘ በኋላ ለካሳ ክፍያ በሚል በርካታ ገንዘብ እንደሚባክንም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ መጠን የካሳ ክፍያዎች ፕሮጀክቶችን በሚያስተጓጉል መልኩ መሆን እንዳሌለባቸውም ገልጸዋል፡፡ በሀገራችን የቱሪዝም ከፍተኛ ዕምቅ ሃብት ያለበት በመሆኑ ይሄንኑ በአግባቡ የማስተዋወቅ ችግሮችን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከቱሪዝም አኳያ በአደረጃጀት ዙሪያ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥናት እየተካሄደ መሆኑም አንስተዋል፡፡

“የኢትዮጵያ ልማት፣ ሰላም፣ ነፃነት እና አንድነት የሚረጋገጠው በዋናነት በኢትዮጵያውያን ነው”-

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ልማት፣ ሰላም፣ነፃነትና አንድነት የሚረጋገጠው በዋናነት በኢትዮጵያውያን ነው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ ባለው ተለዋዋጭ ሁኔታ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ እይታን መፈተሽ ያስፈልጋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “እኛ በምናውቀው ነገር ላይ የሚዋሸን ሚዲያን በማናውቀው ነገር ማመን ስለማንችል የምናነበው፣ የምንሰማውን ነገር ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ማሰላሰል ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡

“ድህነት፣ ነፃነትና ዲፕሎማሲ ብርቃችን አይደለም፤ ብርቃችን ብልጽግና ነው፤ አገራት በምናውቀው ነገር ላይ ጊዜ ከሚያባክኑ የማናውቀው ላይ ቢያግዙን ይሻላል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “እውነተኛ ወዳጅ አገር በልማትና በኢንቨስትመንት ላይ ያግዘናል” ብለዋል፡፡ የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ

Leave a Reply

%d bloggers like this: