Site icon ETHIO12.COM

የአፍሪካ ህብረት 220 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ለአባል ሀገራቱ ማሰራጨት ጀመረ

የአፍሪካ ህብረት ከባለፈው ሐሙስ ጀምሮ 220 ሚሊየን ዶዝ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ- 19 ክትባት ለአባል ሀገራቱ እያሰራጨ ነው፡፡ በቀጣይም ህብረቱ ተጨማሪ 180 ሚሊየን ዶዝ ክትባት የማሰራጨት አቅም አለው ነው የተባለው፡፡
ስርጭቱ እውን እንዲሆን በአፍሪካ ህብረት ከኮቪድ-19 መከላከል ጋር ተያይዞ ስማቸው የሚነሳው የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡

ስርጭቱ የሚከናወነውም በፈረንጆቹ መጋቢት 2021 አባል ሀገራቱ ከ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ጋር ባደረጉት የግዢ ስምምነት መሰረት መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ክትባቱ የተመረጠው አንድ ጊዜ ብቻ የሚወሰድ እና ለአገልግሎት አሰጣጥም ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ በመሆኑ ነው፡፡

በተጨማሪም ክትባቱ ረጅም የአገልግሎት ጊዜ ማብቂያ ያለው እና የአፍሪካን የአየር ንብረት መቋቋም የሚችል እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡

በፈረንጆቹ ሐምሌ ወር 6 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶዝ ክትባት ለአባል ሀገራቱ ማከፋፈል የተጀመረ ሲሆን ÷ እስከ ታህሳስ መጨረሻም 50 ሚሊየን ክትባት ለአባል ሀገራቱ እንደሚሰራጭ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ ÷ ሲጂቲ ኤን -FBC

Exit mobile version